✔️ባንካችን አሐዱ:ባንክ ከፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለባንካችን ከፍተኛ አመራሮች ከመጋቢት 01-02/2017 ዓ.ም በድሪም ላይነር ሆቴል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል::
"ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል ርዕስ ሥልጠናውን እየሰጡ ያሉት የኮሚሽኑ ተወካይ ዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ ሲሆኑ፤ ከተሣታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነሥተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል::
የአሐዱ:ባንክ ተ/ዋ/ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገብሩ፤ ኢንዱስትሪው በሥነ-ምግባር እንዲመራ ለማስቻል ይህ ሥልጠና ሚናው የጎላ ነው:: የባንካችን ዕሴቶችም ለዚህ ሐሳብ በእጅጉ የሚስማሙና የሚመቹ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል:: አክለውም ከሥልጠናው የተገኘውን እውቀት እና ልምድ በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በመተግበር ውጤታማነታችንን ለማረጋገጥ መትጋት ይኖርብናል ብለዋል::
አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች
የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!Website|
Facebook|
Instagram|
LinkedIn|
YouTube #አሐዱባንክ #AhaduBank