Update‼️
በአዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ‼️
በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃው አመልክቷል። በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ አስታውቋል።
በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎቹ ገልፀዋል። ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።
ከሰሞኑ የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል ያለው ዩኒቨርሲቲው፣ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱንም ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች ተናግረዋል።
=============🎉🎉🎉
ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማድረግ በቀላሉ መረጃ ይከታተሉ👇👇
@alluexams