⭐የፈጠራቸው ድሮኖች በስሙ የተሰየሙለት የቱርክ ቀኝ እጅ ።
.........................
✅️ሴልሱክ ባይራክታር ይባላል ፡ እአአ በ1979 ሳሪየር በምትባል ከተማ ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ሆኖ ቱርክ ውስጥ ተወለደ ። ባይራክታር የመጀመሪያ ዲግሪውን ኢስታንቡል ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ እንዳጠናቀቀ. .. ባገኘው የነፃ ትምህርት እድል ተጠቅሞ ወደ አሜሪካ ፔንሲልቫንያ አቀና ።
✅️በአሜሪካን ቆይታው የሁለተኛ ዲግሪውን እንዳገኘም ወደ ሀገሩ ተመልሶ ፡ የመኪና መለዋወጫዎችን ለማምረት ተብሎ በአባቱ በተቋቋመውና ፡ በኋላም ከቱርክ መንግስት ጋር በጥምረት በሚሰራ የኤሮስፔስ ካምፓኒ ስራ ጀመረ ።
.................................
" ዛሬ ላይ መስራት የጀመርናቸው እጅግ ዘመናዊ ድሮኖችን ለመስራት ብዙ ደረጃዎችን ማለፍ ነበረብን ፡ መጀመሪያ አካባቢ በግል ገንዘባችን ከኪሳችን እያወጣን የሰራናቸው ድሮኖች ከ15 ኪ/ሜ በላይ ርቀው መሄድ ካለመቻላቸው በተጨማሪ ብዙዎቹ ወድቀውብናል ። ሆኖም ህልማችን ሀያላን ሀገራት ከሚያመርቱት የሚበልጥ ድሮን መስራት ነበረና ፡ ያንን ህልማችንን ነው ያሳካነው " ይላል ፡
.......................
✅️ቱርክ ወደዚህ ምጡቅ ቴክኖሎጂ ከተሸጋገረች አስርት አመታት ባያልፋትም አሁን ላይ ግን የድሮን ቴክኖሎጂን ደረጃ እላይ ሰቅላዋለች ። በተለይ እንደ .....
🚀 Bayraktar TB1 ...🚀Bayraktar TB2 ..........🚀 Bayraktar TB3 .........🚀 Bayraktar Kızılelma ............ እና . .🚀 Bayraktar Akıncı አይነት ዘመናዊ ድሮኖቿ የታዘዙትን ኢላማ ወደፍፁማዊነት በሚጠጋ መልኩ ለማውደም መቻላቸው ብቻ ሳይሆን ፡ ራሳቸውን ከራዳር እይታ ሰውረው ፡ ሊተኮስባቸው ከሚችለው ፀረ አውሮፕላን ሚሳይል አምልጠው ካስፈለገም ፡ የሚተኩስባቸውን ፀረ ሚሳይል ደስሰው ከተሳካ ተልእኮ ጋር ወደ ማዘዣ ጣቢያቸው መመለስ የሚችሉ ናቸው ።
........................
✅️ሀገር የተማረ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ሀገሩን የሚያስታውስ ፡ በተማርኩት ትምህርት ፡ በእውቀቴ ሀገሬን ከታላላቅ ሀገራት ተርታ እንዴት ላሰልፍ ? የሚል ትውልድ ትፈልጋለች ። ሴልሱክ ባይራክታር ይህን መሳይ ህልም ስለያዘ ነው ተአምር በሚባል መልኩ ፡ የሀገሩን ስም ያስጠራው ።
...............................
ዛሬ አውሮፓውያን ሳይቀር ለመግዛት ሰልፍ የሚይዙለትን ድሮን የፈጠረው ሴልሱክ ባይራክታር ፡ እነዚህን ድሮኖች የሚያመርተው ከቱርክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ነው ። ይህ ኩባንያ በሴልኩክ ባይራክታር አባት. . የትናንሽ የመኪና መለዋወጫዎችን ለማምረት ሲባል የተቋቋመ ሲሆን ፡ በሂደት ራሱን አሳድጎ ትልቅ የኤሮስፔስ ኩባንያ ሆኖ ፡ ዛሬ ላይ ከመንግስት ጋር በጋራ እየሰሩ ሀገራቸውን ለማሳደግ ሌት ተቀን ይጥራሉ ።
..............................
⭐የግል ኩባንያ ስለሆነ ፡ በሚል ፡ ሀብታቸውን በውጭ ባንክ ስለማስቀመጥ. አያስቡም. . ራስወዳድ ሆነው የራስን ጥቅም በማሳደድ ምትክ ለቱርክ ታላቅነት ይተጋሉ ። በዚህ ሰው ፈጠራ ፡ በቤተሰቡ ኩባንያ ፡ የቱርክ መንግስት ጥረት አንድላይ ተደምሮ ፡ ዛሬ ላይ ሀገራቸው ቱርክ በአለም ካሉ ከአሜሪካና ቻይና ቀጥሎ ሶስተኛዋ የዘመናዊ ድሮን አምራች ሀገር አድርጓታል ።
...........
የ42 አመቱ ጎልማሳ ሴልሱክ ባይራክታር ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ካለው ቅርበት የተነሳ ፡ ሱመያ ኤርዶጋን የተባለች ልጃቸውን ድረውለት ፡ አንድ ልጅ ወልደዋል ።