የማን ልደት ነው?
(ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ)/ መንፈሳዊ መጽሐፍት / መንፈሳዊ ወግ / መንፈሳዊ ግጥም ሚሚዬ ልደቷ እየተቃረበ መምጣቱ ተደጋግሞ ተነግሯታል። የዘንድሮዉ ለየት ባለ ሁኔታ በትልቅ ድግስ እንደሚከበርላት ስለተነገራት ደስታዋ ወሰን አልነበረዉም። ወሬዋም አሳቧም እርሱዉ ሆኗል። ቤተሰብም ዝግጅቱን አጧጡፎታል። እንዳይደርስ የለም ከብዙ ጥበቃ በኋላ ‘የሚሚዬ ልደት’ ቀን ደረሰ! በማለዳ የቀሰቀሳት የዝግጅቱ ግርግር ሲሆን ይህ ሁሉ ለእርሷ መሆኑ ገርሟት በደስታ ከአልጋዋ ዘልላ ወረደች። እኩ...