ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው.....(ምሳ 22፥6)
ጠቢቡ ሰለሞን በጥንቱ እንደተገነዘበው ልጅ በልጅነት ያየውን መንገድ ነው በስተርጅናውም የሚሄደው! ልጅ በልጅነት ካልተገራ ካደገ በኋላ በምንም አይስተካከልም። የልጅነት ጊዜ ልክ በከፍተኛ ሙቀት ወደ ፈሳሽነት እንደተቀየረ ብረት ነው። አንጥረኛ ብረትን እንደፈለገ የሚያዘው በፈለገው መልኩ የሚቀርጸው በዚሁ ጊዜ ነው። ልጅም እንዲሁ ነው! ምናልባት ዛሬ እያየን ያለነው እፍረት ያልፈጠረበት ፣ የእውነት እና የሐሰት ድንበር የጠፋበት ፣ ግብረ ገባዊነት ያልፈጠረበት ይህ ትውልድ የተፈጠረው በአንድ ዘመን በተፈጠረ ስህተት መሆኑን እናምን ይሆን? ወላጅ በተሳሳተ መንገድ ልጅን ለመቆጣጠር ሞከረ ልጅ የወላጅን ደካማ ጎን ተጠቀመ። “Men fall in private long before they fall in public” እንዲል JC Ryle ምቹ ጊዜና ቦታ ሲጠብቅ የነበረው ድብቁ ማንነት በየሚዲያው ጋሃድ ወጣ! በሆነ አጋጣሚ ወላጅና ልጆች ተሸዋውደናል! ከርዕሴ ጋር ከሄደልኝ በመልካም ምግባር ምሳሌ የሚሆን አንድ ታሪክ ላንሳ። ይህ ታሪክ ሰለሞን ጥላሁን እና ሥምረት ግብረማርያም “ደማቆቹ፡ ጸሓያተ ሌሊት” በሚል ርእስ ስለኢትዮጵያውያን ደማቆች ከጻፉት ውስጥ ስለዶ/ር ጀምበር ካወጉን የተጨለፈ ነው(ይህ ታሪክ በግምት ከዛሬ ከ60-70 አመት ገደማ በፊት የሆነ መሆኑን አንባቢ ልብ ይሏል)።
ይህቺ ልጅ ብላቴና አዱኛ(ሀብት) በተሟላበት በእርሷ ቤተ ሰብና በለምኖ አዳሪ በአቡሌ መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት ዘወትር እንድታሰላስልና እንዲሁም “ድኽነት ምንድነው?” በማለት ራሷን ደጋግማ እንድትጠይቅ ያደርጋት ነበር። አቡሌ ልጂቱ እየመራችው ጎዳና በመውጣት እጁን ዘርግቶ ምጽዋት ይጠይቃል እንጂ ቀኖች ሁሉ ለእርሱ እኩል የተሳኩ አልነበሩም።[...] ገብርኤል፣ ማርያምና ሚካኤል በማይውሉባቸው ቀናት ግን እጆቹ ሣንቲም፣ ኮረጆቹም ፍርፋሪ ይራባሉ። በነዚህ ቀናትም ልጅቱ ጠጋ ብላ፣ “አቡሌ ዛሬ ቀናህ?” ትለዋለች። አቡሌም ግራ እጁን ልጅቱ ትከሻ ላይ እያደረገ፣ “ዛሬ አልቀናኝም!” ይላታል። የአቡሌ የቀን ሙሉ ልመና ባዶ መሆኑን ስታስብ ልጂት ታዝናለች፣ ትተክዛለችም።
አንድ ሐሳብ መጥቶላት ጮኽ ብላ ጠራችው፤ “አቡሌ” እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰድዳ ሣንቲሞች እየፈለገች።
“አቤት ጀንበር!” አለ አቡሌ
“እንካ!”
“ምን?” አቡሌ ከጥያቄው ጋር እጁን ወደ ፊት ዘረጋ። ቀኑን ሙሉ ደክሞ ያላገኛቸው ሣንቲሞች የእጁን መዳፍ ሞሉት።
“ከየት አመጣሽው?”
“እናቴ የሰጠችኝ የኪስ ገንዘብ ነው፤ ያዘው! እኔ ብገዛበት ከረሜላ ነው። ለአንተ ግን ራት መቅመሻ ይሆንልሃል።”
አቡሌ በማያየው ዐይኑ ይህቺን ልበ ብርሃንና አስተዋይ ልጅ ያያት መሰል። በሳል አስተሳሰቧን አእምሮዋ ውስጥ ገብቶ ገመገመው።
“እግዚአብሔር ይስጥሽ! እግዚአብሔር ለፍሬ ያብቃሽ! ወገኖችሽን የምትጠቅሚ ልጅ ሁኚ!” ብሎ መረቃት፤ ለእርሷ መስጠት የሚችለው ምርቃት ብቻ ነበርና።
እናት ከተማሪ ቤት የመጣችውን ልጃቸውን በጨዋታ እየተቀበሏት ነው።
“ጀንበር!” በማለት ተጣሩ
“አቤት!”
“የሰጠሁሽን የኪስ ሣንቲም ምን አደረግሽበት?”
“ዛሬ አቡሌ አልቀናውም ነበርና ለእርሱ ሰጠሁት።”
እናት ዕድሜዋን ቀድማ የበሰለች ልጃቸውን አተኩረው እያዩ፣ “ጎሽ የኔ ልጅ! ደግ አድርገሻል! እንኳን ሰጠሽ” አሏት። ልጅቱም “ለካ ከረሜላ ከመብላት ይልቅ ለአቡሌ ሣንቲም መስጠት ያስመሰግናል!” ስትል አወራች ከራሷ ጋር። አውርታም አልቀረችም፤ የድኾች አለኝታ እንደሆነች በዚሁ ገፋችበት እንጂ።
[....]
ያቺ የአቡሌ መሪና ረዳት የነበረችው ባለ ራእይ ልጅ ዛሬ፣ አንቱ የተባለች ትልቅ ሰው ሆናለች። አንቱታው ከዕድሜ መብሰል ጋር ብቻ የመጣ አይደለም። በታልቅ ትምህርት ታግዞ፣ የድኾች ረዳትና ጠበቃ በመሆን የተገኘ ስም እንጂ፤ ይህቺ የቀድሞ የአቡሌ መሪ በአሁን ሰዓት “በሙኩ በተቀነባበረ ዘዴ የከተማ ልማት ፕሮጀክት” መሥራች፣ አስተባባሪና ርዳታ አሰባሳቢ የሆኑት ዶክተር ጀምበር ተፈራ ናቸው።
“በተክለ ሃይማኖት በመርካቶ ጓሮ
ጀንደር ስታበራ ተሻሽለ ኑሮ”*
"ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” ምሳ 22፥6
አማኑኤል አ.
*ደማቆቹ፡ ጸሓያተ ሌሊት ሰለሞን ጥላሁን እና ሥምረት ግብረማርያም(ገጽ 284-6)
©መንፈሳዊ መጽሐፍት