አዝ:- መልካሙን የአምላኬን ፊት በጽኑ እፈልጋለሁ
ማልጄ በማለዳ ወደእርሱ እመጣለሁ
መንፈሱን እየሞላ ዘይቱን ይቀባኛል
ነፍሱን ስለ እኔ የሰጠው ኢየሱስ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ይወደኛል ጌታ ይወደኛል (፫x)
ነፍሱን የሰጠው ስለእኔ የታደገኝ ከኩነኔ
ምህረቱን ያበዛልኝ የቆመልኝም ከጐኔ
ነፍሴ ታምናው ረክታለች በጸጋው ብዛት ቆማለች
ያንን አስፈሪ ጨለማ ከአምላኳ ጋር ተሻግራለች
ያኔ በመስቀል ሲሰቃይ እንደሚወደኝ ገብቶኛል
ሞት ቢመጣ በመከራ ከእርሱ ጋራ ይመቸኛል
ይመቸኛል (፬x)
አዝ:- መልካሙን የአምላኬን ፊት በጽኑ እፈልጋለሁ
ማልጄ በማለዳ ወደእርሱ እመጣለሁ
መንፈሱን እየሞላ ዘይቱን ይቀባኛል
ነፍሱን ስለ እኔ የሰጠው ኢየሱስ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ይወደኛል ጌታ ይወደኛል (፫x)
የፍቅሩ ጥልቀት ሲገባኝ ልቤን ሰጠሁ እንዲገዛኝ
ይንገሥብኝ ወድጃለሁ አምላኬ ነህ ብዬዋለሁ
ዋላ ውሃን እንደምትሻ እኔም ዘወትር እጠማዋለሁ
በነፍሴ ወደማደሪያው ወደ እርሱ እገሰግሳለሁ
የሚለየኝ ማነው ከእርሱ በፍቅሩ ገመድ አስሮኛል
ሞት ቢመጣ በመከራ ከእርሱ ጋራ ይመቸኛል
ይመቸኛል (፬x)
አዝ:- መልካሙን የአምላኬን ፊት በጽኑ እፈልጋለሁ
ማልጄ በማለዳ ወደእርሱ እመጣለሁ
መንፈሱን እየሞላ ዘይቱን ይቀባኛል
ነፍሱን ስለ እኔ የሰጠው ኢየሱስ ይወደኛል
ይወደኛል (፬x) ይወደኛል ጌታ ይወደኛል (፫x)