🔥#ከአማራ_ፋኖ_በጎጃም_የተሰጠ_መረጃ‼️
‘’’’””””””””””””””””””””””””””””””””””""""
በዘመቻ መቶ ተራሮች መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም የተማረከው የ6ኛ ዕዝ 75ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ያሬድ ኪሮስ ሰብአዊ መብቱ እና ክብሩ ተጠብቆ በአማራ ፋኖ በጎጃም የምርኮኞች ጣቢያ የቆዬ መሆኑ ይታወቃል::
ሆኖም ጠላት በርካታ ምርኮኞችን እና ሲቪሊያንን በድሮን ጥቃት ከጨፈጨፈበት ክስተት ለጥቂት የተረፈው ምርኮኛዉ ኮሎኔል ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ባልታወቀ ሁኔታ ከነበረበት ቦታ መጥፋቱ ተረጋግጧል::
በዚህ ያልተገባ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም በሚል የተጠረጠሩ አመራር እና አባላት ላይ ድርጅታችን ምርመራ የጀመረ ሲሆን እስከ ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባለው የምርመራ ሂደት 12 (አስራ ሁለት) የድርጅታችን አመራርና አባላት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እንደቀጠለ ነው።
የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ተገቢ የእርምት እርምጃ እንደምንወስድ እያሳወቅን ጉዳዩንም ለህዝብ እና ለሰራዊታችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
©አስረስ ማረ