⛔️በትዳራቸው ጉዳይ ላይ በባሏ ላይ የምትጮኽ ሚስት በተመለከተ ሸሪዓው ምን ይላል?
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሂመሁላህ፤ ይህ ጥያቄ ቀርቦላቸው ቀጣዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
መልስ፡ ለዚች ሚስት በባሏ ላይ ድመጿን ከፍ ማድረጓ መጥፎ ስነምግባር ነው እንላለን።
ይህ የሆነበት ምክንያት ባልየው የበላይ ጠባቂዋ(ቀውዋማ) እና ተንከባካቢዋ ነው። ስለዚህ እሱን አክብራ በትህትና መናገር አለባት። ይህን ማድረግ በመካከላቸው የትዳራቸው እድሜ የመራዘም ዕድሉ ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል። እናም በሁለት የትዳር አጋሮች ቅርርብ በመካከላቸው እንዲኖር ያደርጋል። ባልየውም ከእርሷ ጋር በመልካም መስተጋብር ሊኗኗር ይገባል። መልካም መስተጋብር ሁለቱም በጋራ ሊያስገኙት የሚገባ ነገር ነው። አላህ አዘወጀለ እንዲህ ይላል፦
وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِن كَرِهۡتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰۤ أَن تَكۡرَهُوا۟ شَیۡـࣰٔا وَیَجۡعَلَ ٱللَّهُ فِیهِ خَیۡرࣰا كَثِیرࣰا
(ሚሰቶቻችሁን) በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ኸይር ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡ (አንኒሳእ:19)
እኔ ለዚች ሚስት የምመክረው ለራሷስትል በባልዋ ጉዳይ አላህን እንድትፈራ እና በእሱ ላይ ድምጿን ከፍ እንዳታደርግ (እንዳትጮህ) ነው። በተለይ ባሏ በእርጋታ እና ድምፁን እየቀነሰ እያናገራት ከሆነ። ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ እንድትፈራ እመክራለሁ።”
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

فتاوى نور على الدرب الشريط رقم [312]
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru