ተቅዋ የሱና እና የተውሒድ ቻናል


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ
ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው።
ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ
ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ
አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ
አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ ያርገን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በአንድ ዘገባ ያ ልጅ አድጎ ሰባት ልጆችን መውለዱንና ልጆቹ ሁሉ ቁርዓንን የሀፈዙ የሸመዱ እንደነበሩ ተጠቅሷል።
ኡሙ ሱለይምን ረድየላሁ አንሁ የተመለከተ አስደናቂ ታሪክ አለ።አንድ የሆነ ሰው ወደ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይመጣና ድሀ እንደሆነ በመግለፅ ምግብ እንዲሰጡት ይጠይቃቸዋል።ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ባለቤቶቻቸውን ለእንግዳው የሚሆን ምግብ ካላቸው ይሰጡት ዘንድ ላኩባቸው ሆኖም ግን የሁሉም መልስ እርሶን በሀቅ ላይ በላከው ጌታ ይሁንብን ከውሀ በስተቀር የሚላስ የሚቀመስ ነገር የለም።ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

ወደ ተከታዮቻቸው ዞረው ይህን እንግዳ የሚያስተናግድልኝ ማነው አላህ ይዘንለትና በማለት በግልፅ ጠየቋቸው።አቡ ጦልሀ አል አንሷሪ ረድየላሁ አንሁ በዚህ ጊዜ ወደ ቤት ይዞት ሄደ ከዚያም ባለቤቱን ኡሙ ሱለይምን ረድየላሁ አንሃ እንግዳችንን የምናስተናግድበት አዳች ነገር ይኖራልን!? በማለት ጠየቃት።ከልጆቻችን ምግብ በስተቀር አንዳች ነገር የለም በማለት መልስ ሰጠችው።እነሱን በሆነ ዘዴ እንዲተኙ አድርጊና ምግቡን አቅርቢ ከዚያም መብራቱን በራሱ ጊዜ የጠፋ እንዲመስል አድርገሽ አጥፊው በማለት አዘዛት። በዚህ አይነት እንግዳው ሰው እነርሱም አብረውት እየተመገቡ እነደሆነ በማሰብ በጨለማ እስኪጠግብ ድረስ ምግቡን ከበላ በኋላ በሰላም ተኝቶ አደረ። እነሱም ልጆቻቸውም ግን ምንም ሳይቀምሱ አነጉ።እንደነጋም አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ወደ መስጂድ ሲሄድ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉት:- አላህ ባለፈ ምሽት እንግዳችሁን ለማስተናገድ የፈፀማችሁትን ድርጊት ወዶላችኋል።በማለት አሞካሹት

ኡሙ ሱለይም ረድየላሁ አንሃ እንደ ሌሎቹ ሴቶች ሁሉ በተለያዩ ጦርነቶች ተሳትፋለች በሁነይን ዘመቻ ሙስሊሞችን በማበረታታት የተጠሙትን በማጠጣት እና የቆሰሉትን በመንከባከብ ትልቅ ሚና ተጫውታለች።በዚያ ዘመቻ ኡሙ ሱለይም ረድየላሁ አንሃ ጩቤ ይዛ በመታየቷ አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ለነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይህን በማንሳት ስሞታ አቀረበ።

በዚህም ጊዜ እርሷ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን የያዝኩት ራሴን ለመከላከል ነው። አንድ አጋሪ ወደ ቢቀርብ ሆዱን እተረትረዋለሁ አለች። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀሳቧን ደገፉ በዚህ ጊዜም እርሷን በአድናቆት ነበር የሚያዩዋት እቤቷ ሲገቡም እንዲህ ይላሉ ጀነት በገባሁ ጊዜ የሚንኮሻኮሾ ድምፅ ሰማሁ እኔም ማነው በማለት ጠየቅሁ ይች የአነስ ኢብን ማሊክ እናት ሩመይሳ ቢንት ሚልሀን ናት ተባልኩኝ በማለት በጀነት ያበስሯት ነበር። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
የእኛን እናት ድንቅ ተምሳሌት ኡሙ ሱለይም አላህ ይዘንላት


ኡሙ ሱለይም ቢንት ሚልሀን ረድየላሁ አንሃ
ሙሉ ስሟ ሩመይሳ ኡሙ ሱለይም ቢንት ሚልሀን ኢብን ኻሊድ ኢብን ዘይድ አንነጃር ነው። የአክስቷን ልጅ ማሊክ ኢብን አነድርን አግብታ ነበር።

መጀመሪያ ላይ ኢስላምን ከተቀበሉት ሰዎች ውስጥ ነው የምትመደበው ምንም እንኳን ባለቤቷ ማሊክ ኢስላም ለመቀበል አሻፈረኝ ቢልና እሷንም ከሀይማኖቷ ለመመለስ ትልቅ ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም።

ከባለቤቷ ጋር ያላቸው ግንኙነት በምትከተለው እምነት የተነሳ ይህን የመሰለ መልክ እየያዘ ቢሄድም ኡሙ ሱለይም ልጇን አነስን የእምነት ምስክርነትን ወይም ሽሀዳን እንዲይዝ ቀስ እያለች ታለማምደው ጀመር አነስ ኢብን ማሊክን ታላቁን ሶሀባ ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ ጌታ እንደሌለ እና ሙሀመድ ነብይና መልክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ ይላል አነስ በትንሽ ኮልታፋ አፉ ።አባትዬ በዚህ ጊዜ ልጄን አታበላሽብኝ በማለት ይደነፋል።እሷ ደግሞ ረጋብላ እያበላሽሁት ሳይሆን መከተል ያለበት እምነት እያስተማርኩት ነው በማለት ትናገራለች።

ማሊክ እየተፈፀመ ባለው ነገር ሁሉ በየጊዜው የበለጠ እየተናደደ እና ሀይማኖቱን እያጠበቀ በሄደ ቁጥር እቤቱ ውስጥ የተፈጠረው ጉዳይ እየተመቸው ባለመሄዱ ቤቱንና ትዳሩን ጥሎ ለሁልጊዜውም ላይመለስ ሄደ። ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነበር ከጥላቶቹ በአንዱ ህይወቱ ያለፈችው። ኡሙ ሱለይም ረድየላሁ አንሃ ከዚያ ቡሀላ አባቱ የሞተበትን ልጇን በማሳደጉ ተግባር ላይ አተኩራ ህይወቷን ትገፋ ጀመር።ከዚያም ልጇ ከፍ ሲል ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቢያገለግል ደስተኛ እንደምትሆን በመግለፅ ወስዳ አበረከተችላቸው።

ቆየት ብሎም አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ የጋብቻ ሀሳብ አቀረበላት።ለጋብቻዋ ጥሎሽ ወይም መኸር የሚሆን ውድ ስጦታ አዘጋጀ ይሁን እንጂ እሱ አጋሪ በመሆኑ ጋብቻውን ውድቅ አደረገች።ትህትና በተሞላበት አቀራረብ እንዲህ አለችው።አቡ ጦልሀ ሆይ እንደ አንተ አይነቱ ሰው የትዳር ጥያቄ አንስቶ እቢ አይባልም ሆኖም ግን አንተ አጋሪ ስትሆን እኔ ደግሞ ሙስሊም በመሆኔ ከአንተ ጋር በትዳር ልተሳሰር አልችልም።

አጋሪ የሆነ ወንድ እንዳገባ ሀይማኖቴ አይፈቅድልኝም።እኔ ያንተ ሙስሊም መሆን እንጂ ሌላ ነገር አደለም የምፈልገው አለችው።በዚህ ጊዜ አቡ ጦልሀ ወደ እዛ የሚመራኝ ማነው አላት ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ናቸው ነበር መልሷ።በዚያ ጊዜ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ተደመጡ አቡ ጦልሀ በአይኖቹ መካከል የኢስላም ምልክት ያለበት ሆኖ ወደ እናንተ ይመጣል።አቡ ጦልሀ በአነጋገሯ በጣም ተደንቆ ይበልጥ እየወደዳህ ሄደ።የእምነት ምስክርነት ቃሉን ሽሀዳ እንደሰጠም ወዲያው አገባት። ኡሙ ሱለይም ረድየላሁ አንሃ ምን አይነት ውድ የሆነ ጥሎሽ ነው የቀረበላት እርሷ በእርግጥም ኢስላምን ሽሀዳን ጥሎሽ አድርጋ ባሏ ኢስላምን ከተቀበለ ሌላ ጥሎሽ እንደማትፈልግ በመግለፅ ጋብቻዋን የፈፀመች ብቸኛ ሴት ናት።መኸራን በሽሀዳ ያደረገች ምርጥና ድንቅ እንስት💎

ኢስላምን እንደተቀበለና የእምነቱን አስተምሮቶች እንዳወቀ አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ፍፁም አስተሳሰቡ ተለወጠ።ነፍሱም በጣሙን በእምነቱ ፍቅር ተነካች የኢስላምን ስነምግባር መመሪያዎች እና እሴቶች በጣም አድናቂ ሆነ በዚያ ደረጃ እንዲደርስ ያደረገው ልክ እንደ ሌሎቹ ሶሀቦች የእምነቱን ትምህርታዊ ስልጠና ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እጅ ያገኝ ስለነበር ነው።

አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ሀብት ከነበራቸው ሰዎች አንዱ ነበር።ከነበረው ሀብት ሁሉ ትልቅ ግምት የሚሰጣት አንድ ምንጭ ያላት የአትክልት ስፍራ ነበረችው።ይህ በእንዲህ እያለ አላህ የሚከተለውን የቁርዓን አንቀፅ አወረደ።

لَن تَنَالُوا الْبِرَّ حَتَّىٰ تُنفِقُوا مِمَّا تُحِبُّونَ ۚ وَمَا تُنفِقُوا مِن شَيْءٍ فَإِنَّ اللَّهَ بِهِ عَلِيمٌ

የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ በጎን ሥራ (ዋጋውን) አታገኙም፡፡ ከምንም ነገር ብትለግሱ አላህ ያውቀዋል፡፡

ሱረቱል ኢምራን አንቀፅ "92"

በዚህ ጊዜ አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ወደ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሄዶ የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህ የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ በጎን ስራ ዋጋን አታገኙም ብሏል።እኔ በጣም የምወዳት በይሩሀ የምትባል ምንጭ ያለባት የአትክልት ስፍራ አለችኝ ስለሆነም እሷን የአላህ ምንዳ የምከጅል ሆኜ አበርክቻለሁ እርሶ ለፈለጉት ሰው ያከፋፍሉት አላቸው። ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉ ጎሽ ጎሽ በጣም ጥሩ ያ ትልቅና የተባረከ ንብረት ነው ይህን ሁለት ጊዜ ደጋገሙት እንደማስበው ለስጋ ዘመዶችህ ብታከፋፍለው መልካም ነው አሉት።አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ በተነገረው መሰረት ለስጋ ዘመዶቹ አከፋፈላት። ቡኻሪ ዘግበውታል

አንድ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ሆነ አቡ ጦልሀ እና ኡሙ ሱለይም የሁለቱንም ስራ አላህ ይውደድላቸውና አቡ ኡመይር ብለው ስም ያወጡለት አንድ ልጅ ነበራቸው ልጁ ለሁለቱም የደስታ እና የፍስሀ ምንጭ ሆኖላቸው ነበር።አላህ በፈለገ ጊዜ ለሰዎች የሰጣቸውን ፀጋ ይወስዳል ይህም ፈተና መሆኑ ነው።እናም አቡ ኡመይር ሞተ አባትየው ስለ ልጁ መሞት ምንም ያወቀው ነገር አልነበረም።ኡሙ ሱለይም የልጁን ማረፍ እንዳወቀች በልብስ ከሸፈነችው በኋላ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን💦 እኛ የአላህ ነን ወደ እርሱም ተመላሾች ነን በማለት ሀዘኗን በትዕግስት ዋጥ አደረገችው።

ከዚያም በልጁ ላይ የደረሰውን ነገር ለአቡ ጦልሀ ማንም ሰው እንዳይናገር ቤተሰቦቿን አስጠነቀቀች ።አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ወደ ቤት እንደተመለሰ ባለቤቱ ደስተኛ መሆኗን አስተዋለ ስለ ልጁ ሲጠይቃትም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ አሁን ፀጥ ብሏል አለችው።ፆመኛ ነበርና የሚያፈጥርበት አቅርባለት ከተመገበ በኋላ ራሷን አበጃጅታና ተቆነጃጅታ እንዲሁም ሽቶ ተቀብታ ወደ እርሱ ቀረበች። በጣም የምታምር ሆና ሲመለከታትም ወደ ፍቅር ጨዋታ ተዘነበለ።

እርካታ እንዳገኘ በተገነዘበች ጊዜ ፀጥታውን በመስበር እንዲህ አለችው። አቡ ጦልሀ ሆይ አንድ ሰው ለሌላኛው ሰው የሆነ ንብረት በውሰት ቢሰጠውና ያንን የሰጠውን ንብረት ደግሞ በፈለገ ጊዜ አምጣ ቢለው ያንን ንብረት አልሰጥም ብሎ ያንገራግራልን!?አለችው ፈፅም ማድረግ የለበትም አላት አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ልጃችን ከአላህ የተሰጠ ንብረት ነበር አሁን ደግሞ ወስዶታል💦 አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ በዚህ ጊዜ በንዴት ቱግ ብሎ ታዲያ እንዲህ እስከምሆን ድረስ ለምን ይሆን ዝም ያልሽኝ በማለት ሚስቱ ላይ ጮኸባት እሷ ግን እኛ የአላህ ነን ወደ እርሱም ተመላሾች ነን ከማለት በስተቀር ምንም አይነት ቃል አልተነፈሰችም ነበር።

ሲነጋ አቡ ጦልሀ ረድየላሁ አንሁ ወደ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሄዶ ሚስቱ ያደረገችውን ነገር ሁሉ ዘርዝሮ ስሞታውን አቀረበ።ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለፈውን ምሽታችሁን አላህ ይባርክላችሁ አሉ።በዚያች ለሊት ግንኙነትም ኡሙ ሱለይም ረድየላሁ አንሃ ፀነሰች በወለደች ጊዜም ልጇን ወደ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስትልከው ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተምር በአፋቸው አላምጠው በህፃኑ አፍ ላይ አደረጉለት ከዚያም አብዱላህ በማለት ስም አወጡለት። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል


ሸይኽ ሰዕዲይ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ:-

"የወጣትነቱን ግዜ የተጠቀመና (የስራው) መዝገብ ከመጠቅለሉ በፊት   በተውበትና (ወደጌታው) በመመለስ የተቻኩለን ባሪያ አላህ ይዘንለት"

【አል ፈዋኪሁ ሸሂያህ 217】

ወንድሜ -ወጣትነትም ያልፋል
_ሀይልም ይደክማል
_ገንዘብም ያልቃል
ስለዚህ ኋላ ከመፀፀትና ከመለደም በፊት ወደጌታችን እንመለስ

=https://t.me/tdarna_islam


Репост из: ተቅዋ የሱና ቻናል
"የፍቅር  መጀመሪያው  ትዳር  ሲሆን

መጨረሻው  ደግሞ  ጀነት  ነው"

አላህ  ፍቅር  እስከ  ጀነት  ይወፍቀን!!

በችግርም በደስታም ግዜ ሳንነጣጠል
አብረን ተያይዘን  ተሳስበ፣ን ተዛዝነን ፣ተዋደን
ዱኒያን   የምንሾልካት ያድርገን በጀነተል ፊርዶወስም በአንድ ላይ ይሰብስበን አሚን!!

=https://t.me/abuluqmanibnidris


ሚስት ከአጅነቢይ ወንድ በራቀችና ለትዳራ ታመኝ በሆነች ቁጥር ለትዳራ ና ለባሏ ያለት ፍቅርና እንክብካቤ ዞትር እያጨመራ ይሄዳል።

ልክ እንደዛው ከአጂነቢይ ወንድ በምንም አይነት ምክንያት በተቀረበች ቁጥር ለትዳራና ለባሏ ያለት እንክብካቤ ና ፍቅር እያቀነሳ ይሄዳል አልፎም ወደ ፍቺ ይወስዳታል ስላዚህ ሚስት ሆይ ምርጫዉ የረስሽ ነው




Репост из: ተቅዋ የሱና ቻናል
ሷሊህ የሆኑ ሰዎች ከወንጀል ነፃ አይምሰሉህ!
ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ:—
"ሷሊህ የሆኑ ሰዎች ከወንጀል የነፁ ይመስሉሃልን!? (አይደሉም) ነገር ግን እነሱ (ወንጀልን ሲፈፅሙ) ገሀድ ከማውጣት ስለደበቁ፣ መሀርታን ሰለለመኑ እና በወንጀል ላይ ስላልዘወተሩ ፣ ወንጀል ስለመስራታቸው ምክንያትን ከመደርደር ጥፋታቸውን ስላመኑና ፀያፍ ነገር ከፈፀሙ በኋላ መልካምን ሰለሚያሰከትሉ እንጂ::"
ከሰለፎች አንዱ:— (አንተ ከዲንህ ጋር እንዴት ነህ?) ተብለው ተጠየቁ:—
እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ:—

(ኢማኔን ወንጀሎቼ እየበጣጠሱት እኔም በኢስቲግፋር እየጠጋገንኩተ አለሁ።) አለ ይባላል።
ውዶቼ:— እኛም ከወንጀል የፀዳን አይደለንም እና ኢስቲግፋር የኢማናችን መጠገኛ ይሁነን።


እህቴ ሆይ ጥብቅ ሁኚ!!

የንጉሱ ሚስት ዩሱፍን በመፈተን
አላገኘችውም። ነገር ግን የሹዐይብ
ልጅ ሐያእ በማድረጓ
ሙሳን ማግኘት
ችላለች!! ሀያእ ይኑርሽ እህቴ!!


➧ታላቁ ዓሊም ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ አላህ ይማራቸውና እዲህ ይላሉ‼️

➺ አንተ እኮ ልትበላና ልትጠጣ አይደለም የተፈጠርከው። ህንፃ ዎችን ልትገነባ ፣ ዛፎችን ልትተክል ፣ ወንዞችን ልትሰነጥቅ ፣ ለወሲባዊ ግንኙነት ወይም ለሌላ አልተፈጠርክም። በፍፁም! አንተ የተፈጠርከው ጌታህን እንድታመልክ ነው ። አንተ የተፈጠርከው በትዛዙ ላይ እንድትፀና እና መልክተኛውን ﷺ እንድትከተል ነው ። የተፈጠርከው ለዚህ ነው ። በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ አላህን ለመታዘዝ ፣ እሱን ከማመፅም ለመራቅ እንድትታገዝበት ነው የተፈጠረው ። እንጂ ለስሜትህ እንድትታገዝበት አይደለም የተፈጠረው ።[ አል ፈተዋ ፡ 7/98]


☑️ ኢልም (እውቀት) ማለት
🔹የቀልብ ምግብ
🔹የቀልብ መጠጥ
🔹የቀልብ መድሀኒት
🔹የቀልብ ህይወት ሲሆን
🔹በአጠቃላይ የቀልብ መስተካከልም ሆነ መበላሸት በእውቀቱ ልክ
የተመሰረተ ይሆናል።

☑️ ቀልብ ህያው የሚሆነውና የሚለመልመው በእውቀት ሲሆን። የሚደርቀውና የሚሞተው ደግሞ ለእውቀት በመራቁ ይሆናል

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


Репост из: ተቅዋ የሱና ቻናል
ሸይኽ_ዓብዱረዛቅ_አልበድር ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሸይጧን ማለት ልክ እንደ መንገድ ቆራጭ (ሽፍታ) አይነት ነው። አንድ ባሪያ ወደ አላህ መጓዝ በፈለገ ጊዜ መንገድ ቆራጭ በመሆን እንዳይሄድ ያደርገዋል። ለዚህም ነው ለከፊል ሰለፎች፦ አይሁዶችና ነሳራዎች እኛ (በሸይጧን) አንወሰወስም ይላሉ ሲባሉ፦ እውነታቸው ነው ሸይጧን ባዶ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል? ያሉት።»

📚 ۞ أَحاديثُ إِصلاَحِ القُلوبِ【23】۞


⛔️በትዳራቸው ጉዳይ ላይ በባሏ ላይ የምትጮኽ ሚስት በተመለከተ ሸሪዓው ምን ይላል?

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሂመሁላህይህ ጥያቄ ቀርቦላቸው ቀጣዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
መልስ፡ ለዚች ሚስት በባሏ ላይ ድመጿን ከፍ ማድረጓ መጥፎ ስነምግባር ነው እንላለን።
ይህ የሆነበት ምክንያት ባልየው የበላይ ጠባቂዋ(ቀውዋማ) እና ተንከባካቢዋ ነው። ስለዚህ እሱን አክብራ በትህትና መናገር አለባት። ይህን ማድረግ በመካከላቸው የትዳራቸው እድሜ የመራዘም  ዕድሉ ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል። እናም በሁለት የትዳር አጋሮች ቅርርብ በመካከላቸው እንዲኖር ያደርጋል። ባልየውም ከእርሷ ጋር በመልካም መስተጋብር ሊኗኗር ይገባል። መልካም መስተጋብር ሁለቱም በጋራ ሊያስገኙት የሚገባ ነገር ነው። አላህ አዘወጀለ እንዲህ ይላል፦

وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِن كَرِهۡتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰۤ أَن تَكۡرَهُوا۟ شَیۡـࣰٔا وَیَجۡعَلَ ٱللَّهُ فِیهِ خَیۡرࣰا كَثِیرࣰا
(ሚሰቶቻችሁን) በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ኸይር ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡ (አንኒሳእ:19)
እኔ ለዚች ሚስት የምመክረው ለራሷስትል በባልዋ ጉዳይ አላህን እንድትፈራ እና በእሱ ላይ ድምጿን ከፍ እንዳታደርግ (እንዳትጮህ) ነው። በተለይ ባሏ በእርጋታ  እና ድምፁን እየቀነሰ እያናገራት ከሆነ። ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ እንድትፈራ እመክራለሁ።”

فتاوى نور على الدرب الشريط رقم [312]


=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


ባልና ሚስት በፍች በሚለያዩ ጊዜ ህፃናት ልጆችን መበቃቀያ ማድረግ አይገባም። አንዳንድ ወንዶች ጨቅላ ህጻንን ከእናት በመንጠቅ መበቀያ ያደርጋሉ። እንደዚሁም አንዳንድ ሴቶች ልጁን አስታቅፌ ህይወትን ፈተና አደርግበታለሁ በሚል አጉል እሳቤ የአብራካቸውን ክፋይ ልክ እንደማይረባ ቁስ ገፍተው ይሰጣሉ። እዚህ መሀል ላይ ልጆች ብዙ ግፍና መከራ ያስተናግዳሉ።
በመጀመሪያ አብሮ መኖር ያልሆነላቸው ጥንዶች እንደ ጠላት ሊተያዩ አይገባም። በመሀላቸው የማይበጠስ ገመድ አለ፣ ኢስላም። ቢለያዩም እህቱ ነች፤ ወንድሟ ነው። ልጅ ሲኖር ደግሞ የማይቆረጥ ዝምድና ተፈጥሯል። የልጇ አባት ለሴቷ፣ የልጁ እናት ለወንዱ ተራ ሰዎች አይደሉም። ልጆች ለኛ ቅርብ እስከሆኑ ድረስ የነሱ ቅርብ ሰዎች ለኛም ቅርቦች ናቸው። ከዚህም አልፎ አብረው በትዳር የኖሩበትንም ዘመን መርሳት አይገባም። "ምንስ ቢሆን አብረን በአንድ መአድ በልተናል'ኮ!" ይላል ያገራችን ሰው። ልጅ እስከማፈራት የደረሰ ህይወት ሲያሳልፉ ደግሞ ይለያል።
﴿وَلا تَنْسَوُا الْفَضْلَ بَيْنَكُمْ﴾
ወደ ጀመርኩት ነጥብ ስመለስ መለያየት ከገጠመን ፈፅሞ ልጆቻችን መበቃቀያ ልናደርጋቸው አይገባም። እንዲያውም በተቻለ መጠን በወላጆች መለያየት የተነሳ የሚገጥማቸውን ማንኛውንም አይነት ጎዶሎ በመመካከር ለመሙላት መጣር ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


በመውሊድ ዙሪያ ለበድሩ ሑሴን አሳሳች ንግግር የተሰጠ እርምት
~
መስከረም 26/2017
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


አንድ አዕራቢይ(ገጠሬ) ከኢማሙ ሻዕቢይ ጋር ይቀማመጣል ነገር ግን ዝምታን ያበዛ ነበር ፤
ሻእቢይ አንድ ቀን እንዲህ አሉት:-"አታወራምን?"
አእራቢዩም እንዲህ ሲል መለሰላቸው "ዝም እላለው ከመጥፎ ነገር እድናለሁ፣ አዳምጣለሁ እውቀት አገኛለሁ፤ የአንድ ሰው ከጆሮው ያለው ድርሻ ለራሱ ሲሆን በምላሱ ያለው ድርሻ ለሌላ ሰው ነው..."

እና ወዳጄ ከመናገርህ በፊት ማድመጥን ልመድ!!

ምንጭ ፦
📙((وفيات الأعيان)) لابن خلكان (3/14)


እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ አላህን ወደ ማውሳት ኺዱ መሸጥንም ተው ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው 
ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ አላህንም በብዙ አውሱ ልትድኑ ይከጀላልና
ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው ፡፡
[📚ሱረቱ አል-ጁሙዓህ 9-11] 
       


▪️ከትዳር አትሽሹ!!

🔻እህቶቼ ሆይ! ሚስቶቻቸውን የሚያሰቃዩ ባሎች እንዳሉ ሁሉ የሚንከባከቡም አሉና ከእናንተ የሚጠበቀው ከትዳር መሸሽ ሳይሆን አሏህ ሆይ! መልካሙን ወፍቀኝ ብሎ ዱዓ በማድረግ ወደትዳር መግባት ነው።
ኢንሻ አላህ አሰብ እያደረጋችሁ ወደ ሀላል ግቡ!!
አላህ በሀላል  ይሰትረን።።


አሳዛኝ እውነታ!!
ወንድሞቼና እህቶቼ ወደ አላህ እንመለስ!!!
ቁርአን አይነበብም! ሓዲስ ተዘንግቷል የዑለሞቻችን መፃህፍት ምልከታ ተነፍጓቸዋል! ሶሓቦች ታቢዒዮች ኢማሞቻችን ተረስተዋል መስጂዶቻችን ወጣቶችን ናፍቀዋል!
አላህን መፍራት ቀረ!!! والله! !!
በተቃራኒው— ምናምንቴ የግጥም መድብሎች ይኮመኮማሉ— ይሸመደዳሉ! የአዝማሪዎች ሰይጣናዊ ጩኸትና ማንቋረር ይደመጣል! የማያውቁንና የማይጠቅሙን ተጫዋቾችና ብልሹ አክተሮች ስማቸው ከነ ታሪካቸው ይሸመደዳል— የመኪኖቻቸቸው ስምና ብዛት ሳይቀር!
አላህ ይመልሰን! !


🍃የነቢዩ ተወዳጅ ልብስ ቀሚስ (ጀለቢያ)

ከዑሙ ሰለማ ) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦

﴿كان أحبَّ الثيابِ إلى رسولِ اللهِ ▫️ القميصُ﴾

“ተወዳጅ የረሱል ልብስ ቀሚስ ነበር።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 4025


🔖ወሳኝ መልእክት ለሴቶች

ብዙ ሴቶች ካገባሁ በኋላ ኢማኔ ደከመ፣ የኢባዳ ጥፍጥና አጣሁ… ሌላም ይላሉ።

ሚስጥሩ ወዲህ ነው። እሱም የባልሽ ሀቅ ስላልተወጣሽ ነው ሚሆነው። ባልሽ የማታከብሬ ፣ ትእዛዙን የምትጥሺ፣ አዛ ምታደርጊውና አሳንሰሽ ምትመለከቺው ከሆነ እንኳን የኢማን ጥፍጥና ማጣት ሌላም ነገር ይፈራልሻል።

ነብዩ እንዲህ ብለዋል።
(ሴት ልጅ የኢማን ጥፍጥና አታገኝም የባሏን ሀቅ በትክክል እስክታደርስ ድረስ።)

Показано 20 последних публикаций.