ይህ ልባዊ መልዕክታችን ነው!
እኛ በትግል ሜዳ ላይ የተግባር መስዕዋትነት እየከፈሉ ላሉ ፋኖ ወንድሞቻችን ትልቅ ክብር አለን፤ እኛ ብዙን ጊዜ የምንወቀስበት መሃል ሰፋሪ ናችሁ በሚል ነው። ለዚህ ትችትና ፍረጃ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በፋኖዎቻችን መካከል ያሉ ልዮነቶች በተለሳለሰ መልኩ በምክክር ይፈቱ ስለምንልና ፋኖዎቻችን ያለስም ስም ሲሰጣቸው በዚህም በዛም ጥብቅ ስለምንቆም ነው።
ምናልባትም በእስክንድር ነጋ ላይ ካቀረብነው ሃሳብ ውጭ ምናልባትም የፋኖ መሪዎቻችንና አባላቶች ስም ስናጠለሽ አንድም ሰው አንዲትም መስመር ፁሑፍ ሊያቀርብብን አይችልም። ምክንያታችን ደግሞ ልዮነቶች ላይ የሚዲያዎች ሚና ማጋጋል እንጅ ስንጥቆችን መድፈን አይደለም ብለን በፅኑ ስለማናም ነው።
ወደ ሰሞኑናዊ ጉዳይ ስንመጣም ዘመድኩን በቀለን መስመር ባለፈ መልኩ እንደሄድንበት ግልፅ ነው። ምክንያት - የእሱም አካሄድ defamation ላይ ያተኮረ እና ተቋማዊ መስመርን የጣሰ ግብታዊ አካሄድ ነው ብለን ስላመን ነበር።
ይህ አካሄዳችን አሸናፊና ተሸናፊ ለመፍጠር አይደለም። በተመሳሳይ ትናንትና ዛሬ ያጋራናቸው የአማራ ፋኖ በጎጃም መግለጫዎችም "አየህ ተሸነፍክ" ለማለትም አይደለም፤ በፍፁም። በሌላ በኩልም የዘመድኩንን ያለፉ አበርክቶዎችንም አፈር ለማስበላት አይደለም። ነገር ግን በትግሉ ላይ የሚኖረን ሚና እንደ ሚዲያ ሰው በልኬታው ልክ መሆን አለበት የሚል ፅኑ እምነት ስላለን ነው።
በጠላት ላይ አነጣጥረው የነበሩ አቅሞችን በሙሉ በትኖ፣ እርስበራስ ለመጠቃቃት መጠቀም ልክ ሊሆን አይችልም። አቅሞችን ሁላ ጠላትን ለማጥፋት በማሟጠጥ፣ ውስጣዊ ተቋማዊ አሰራሮች እየጎለበቱ ውስጣዊ ችግሮችን እያረሙ እንዲሄዱ ማድረግ ያስፈልጋል።
ምንም መካድ የማይቻለው ነገር የሚዲያዎች ፈትፋችነት በጋለው ትግላችን ላይ በረዶ ይዞ ቀርቦ ሊረሳ በማይቻል መልኩ ከጠላት በላይ አጥቅቶናል። እሱ ይቅርና (ለትግላችን አዎንታዊ አመለካከት ያለው ሁሉ) ምናልባትም ባለፉት ጥቂት ወራቶች በሚዲያው ሚናችን ምን ያክሉን ሰዓታችንን ጠላትን ለማጥቃት ተጠቀምንበት ብለን እራሳችን መጠየቁ ጥሩ ነው።
የሆነው ሆኖ ትግላችንን ከመጠበቅ አንጻር እንጅ በዘመድኩን በቀለ ላይ ግለሰባዊ ግጭት ውስጥ ገብተን አይደለም በእላፊ ቃላት ሁላ ስንወርፈው የሰነበትነው። ለትግላችን ቀናዒ አመለካከት እስካለህም ድረስ ይቅርታ እንጠይቅሃለን።
በነገራችን ላይ ትናንት ዶ/ር ጋሹ ክንዱን ወይም ከዛ በፊት ሌሎቹን ይቅርታ የጠየቅንበት ምክንያት ኢጎን በመግራትና ስብር በማለት ይበልጥ መሰባሰብን ካመጣልን በሚል ነው። የእልህ፣ የግትርነት እና "የማርያምን አታሸንፉኝም" አካሄድ ወገን ለምንለው እንደማይሆን መረዳት ያስፈልጋል። ይህ ምክራችን ለፋኖ መሪዎቻችንም ይሁንልን - ለወገን የተባለ ግለሰባዊ መሸነፍ፣ የወል አሸናፊነትን ያመጣል።