ተሰጥዖ ዘሰሙነ ህማማት
በሰሙነ ህማማት ከሰኞ-አርብ እየሰገድን ተሰጥዖ የምንቀበላቸ(በቃል የምንላቸው)
- ለከ ሀይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለአለም
( ለአንተ ሀይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለአለሙ ገንዘብ ነው)
- አማኑኤል አምላክየ ለከ ሀይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ አለም
( ፈጣሪየ አማኑኤል ሆይ ሀይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለአለም የአንተ ነው)
- ኦ እግዚዕየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ሀይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ አለም
( ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሀይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለአንተ ይገባል)
- ሀይልየ ወፀወንየ ዉእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት እስከ ይእቴ መንግሥት ሀይል ወስብሐት ለአለም ድረስ ብቻ
( ሀይሌና አምባየ መጠጊያየ እርሱ ጌታ ነው ረዳቴ ሆኖኛልና በምስጋና እንዲ እላለሁ አባታችን ሆይ እስከ ሀይል ክብር ምስጋና አሜን ድረስ ብቻ)
ካህናት:-
ፀልዩ በእንተ ፅንዕ ዛቲ መካን ወኮሎን መካናት እንተ አበዊና ቅዱሳን ወገዳማት አዕሩግ አለ የህድሩ ዉስቴቶን ዕቀበት ዝንቱ አለም በምልዑ ከመይዕቀበሙ እግዚእ እምኮሉ እኩይ ወይስረይ ለነ ሀጣዉኢነ።
ህዝብ:-
እግዚኦ ተሰሀለነ
ካህናት:-
ስለዚች ቦታ መፅናት በቅዱሳን አባቶች ስም ስለሚጠሩም ቦታዎችና ገዳማት በዉስጣቸዉም ስለሚኖሩ ሽማግሌዎች በጠቅላላው ስለዚህ አለም መጠበቅ ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃቸዉ ዘንድ የእኛንም ሀጢያት ያስተስርይ ዘንድ ፀልዩ
ህዝብ:-
አቤቱ ይቅር በለን
ከላይ ያለውን አይነት ፀሎት በግዕዝ ወይም በአማርኛ በሚፀለይበት ጊዜ በመሀል በመሃል እግዚኦ ተሰሀለነ ወይም አቤቱ ይቅር በለን እያልን እንሰግዳለን 22 ጊዜ ይባላል።
በመቀጠል:-
ኪርያላይሶን ኪርያላሶን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን ታኦስ ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን ሚስያስ ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይናን ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይናን ኪርያላይሶን
ከዚህ በሗላ ኪርያላይሶን ብቻ በመቀባበል በተናጠል 20 ጊዜ ይባላል።
ምንጭ:- ግብረ ህማማት
በህማማት ጊዜ የሚባሉ ግን ትርጉማቸውን የማናውቃቸው የፀሎት ቃላቶች፦
ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
#እብኖዲ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
#ታኦስ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
#ማስያስ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
#ትስቡጣ፦
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር