ጭፍን ፍርጃ ይቅር!
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ
ራሳቸውን ብቻ በማዳመጥ ለነገሮች ብያኔ የሚሰጡ ሰዎች ሲገጥሟችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ራሳቸው ጠይቀው ራሳቸው ይመስልሳሉ፤ እንዳገኟችሁ ሲነግሯችሁ "ተረድቼሃለሁ" ይሏችኋል፤ ግን እኮ የተረዷችሁ በራሳቸው ጫማ ቆመው ነው። ተፈጥሯችን (ሰውነት) በራሱ ሌሎችን ለማዳመጥ የተሰጠ (committed የሆነ) አይደለም። በኃጥአት የወደቅነው የራሳችንን እውነት በራሳችን መንገድ ልንገነባ ስንሞክር እንደሆነ አንዘንጋ። ጠይቀው የጥያቄአቸውን ምላሽ ከእናንተ ማግኘቱ ወራት ሲፈጅባቸው ራሳቸው የሚመልሱ ሰዎች አልገጠሟችሁም?
እኔም ራሴን ብቻ በማዳመጥ ያሳዘንኋችሁና የፈረድሁባችሁ ወዳጆቼ ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እለምናችኋለሁ። ከእናንተ ብቻ ለመስማት መታገስ የነበረብኝን የዝምታችሁን gap ለመሙላት ብዬ ለራሴ በሰጠሁት ምላሽ ላበላሸኋቸው ግኑኝነቶች ኃላፊነት እወስዳለሁ፤ በቀጣዩ ዓመት ሰዎችን በተሻለ መልኩ ለማዳመጥ ቃል እገባለሁ። ሳትሰሙኝና ልቤን ሳታገኙ ራሳችሁ ጠይቃችሁ ለራሳችሁ መልሳችሁ የፈረዳችሁብኝ እናንተም በሌላው ላይ እንዲህ ከማድረግ ተቆጠቡ፤ ለረጅም ዓመታት በሂደት የተሠራው ማንነቴን በጥቂት ሰዓታት ግምታችሁ ድምዳሜ ስትሰጡ ድጋሚ እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ!
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊