የዘፋኞች ሰማያተ መንግሥት
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ
#ጎበዙ (ወጣቱ)፦ ደወለ፣ አስከትሎም፦ "ዘፋኞች መንግሥተ ሰማያት አይገቡም (አይወርሱም) አይደል?"
#እኔ፦ አንተ ትገባለህ?
#ጎበዙ፦ "እንዴ፤ በቀጥታ መልስ እንጂ ባርኒ theology አታድርገው!"
#እኔ፦ እና የጠየቅኸኝ ሃሳብ እንደ መሬት መንቀጥቀጡ ጉዳይ Geology የሚመልሰው ነው? የጠየቅኸኝ መስማት የምትፈልገውን እንድነግርህ ከሆነ ቀጥዬ ለማውራት እቸገራለሁ።
#ጎበዙ፦ "እሺ፤ አንተ ገብተሃል/ወርሰሃል? አልኸኝ? እኔማ ገብቼ እኮ ነው ስለ'ነርሱ የጠየቅኩህ፤ በመንግሥቱ ያልሆነ ፍጥረታዊ ሰው ይህን ጥያቄ ይጠይቃል? አይመስለኝም።"
#እኔ፦ ኦውው! ከውስጥ ወደ ውጭ ነዋ ጥያቄው?
#ጎበዙ፦ "ይህን አጥተኸው አይደል መቼስ!"
#እኔ፦ እሺ፣ በእግዚአብሔር መንግሥትስ ተወርሰሃል?
#ጎበዙ፦ በርግጥ በጥቂቱ፤ ቢሆንም እርሱ በሂደት የሚቋጭ አይደል ባርኒ?
#እኔ፦ መቼ ነው የምትወረሰው? በመንግሥቱ ለመወረስ ምን አቅደሃል? በእነዚህ ጊዜያት ምን እየሠራህ ነው? ምናልባትም ከዘፋኞቹ ንጽረተ ዓለምና የሕይወት ፍልስፍና የአንተን ተግባራዊ ክርስትና የሚለየው ምንድነው? እንደ ማኅበረሰብ ስታስብስ ይህን እንዴት ታየዋለህ?
#ጎበዙ፦ "ኡ! ትንሽ አወሳሰብክብኝ! ስለ ጥቅሱ (አይወርሱም ስለሚለው) ብቻ አስረግጠህ እንድትነግረኝ ነበር አደዋወሌ (ከልጆች ጋር እያወራን)።"
#እኔ፦ መጽሐፍ ቅዱስ የጥቅሶች ስብስብ አይደለማ! እንደውም የአንተ በመንግሥቱ የመወረስ ጉዳይ ስንመክር (ስንጫወት) ስለ ዘፋኞቹም በሂደት እናወራለን ወንድ'ማለም። የእግዚአብሔርን መንግሥት ምንድነው? መውረስ/ መግባት ማለትስ ምን ማለት ነው? ሲቀጥል፦ "ይገባሉ አይገቡም!" ረጅም ከምናወራ እንዴት በወንጌሉ እንድረሳቸው? የሚለው ላይ እንምከር፤ ዘፋኞቹስ እነማናቸው? የሚለውንም እየለየን እያደር እንመክራለን፤ አትጨነቅ።
#ጎበዙ፦ አንተ ጋር ደውዬ ግን በቀጥታ ምላሽ የማገኘው መቼ ይሆን?
#እኔ፦ ምናልባት በቀጥታ ማሰብ ስጀምር (ፈገግን😊)፤ ደግሞ ቀጥታ ራሱ ምንድነው? በቃ በርታልኝ፤ እናወራለን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊