E-LMIS - ብቁ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


🌏✨በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS አገልግሎቶች ላይ ማለትም በውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት፣ በሃር ውስጥ በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎት፣ በባዮሜትሪክስ ምዝገባ፣ ተደራጅቶ በምስራት ዙሪያ፣ በሞያ ስልጠና፣ በሳይኮሜትሪክ ምዘና እና አጠቃላይ ባሉት አገልግሎቶች ላይ አስተያየት፣ ጥያቄ እና ጥቆማ ካላችሁ ☎️በ9138 አጭር የስልክ መስመር ማቅረብ ይችላሉ። በውጪ ሃገር ስራ ስምሪት ከኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘም ያልዎትን ጥቆማ ወይም ቅሬታ በዚሁ አጭር የስልክ መስመር ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
☎️9138


🌏✨ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የሥልጠና መድረክ በጋምቤላ!!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS ልዩ የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ በጋምቤላ ክልል ተካሄደ።

በሥልጠናው ላይ በE-LMIS ማይክሮ ሰርቪዞች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን የኦንላይን ኢንተርፕራይዝ ምዝገባ (ለአዲስ እና ለነባር) እንዲሁም ማደራጀትን በተመለከተ፣ ሉሲ ገበያ (የአከፋፈልና የሽያጭ ስርዓቱን) በተመለከተ፣ የሳይኮሜትሪ ምዘናን እና ኢ-ለርኒንግን በተመለከተ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰቷል።

በተጨማሪም በከተማዋ በሚገኘው የኦፕኖ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በባዮሜትሪክስ የታገዘ የምዝገባ ሂደትን በተመለከተ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ሲኦሲ ሮል አጠቃቀም እና ለ4 የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት (OSSC) የአዲስ ኢንተርፕራይዞች አመዘጋገብ ስልጠና መስጠት ተችሏል። ሥልጠናው በቀጣይ ለሚሰሩ ሥራዎች ጠንካራ ሃይልን ከመፍጠር አንፃር ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ይሆናል።

በዚህ ልዩ የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ትልቅ ትብብር ላደረጉልን ለሞያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ኦቶንግ ኦጅሉ እና ለመላው ባለሞያዎች ላሳያችሁት ትብብር እና ተነሳሽነት ምስጋናችን የላቀ ነው።

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1


✨🌏የምስራች!
በኦሮሚያ ክልል ለሰልጣኞች እና ስራ ፈላጊዎች በሳኮሜትሪ የታገዘ የኢንተርፕሪዝ ምስረታ መርሃ ግብር በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀመረ!!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS የለማው የሳኮሜትሪክ ምዘና ስርዓት በኢንተርፕራይዝ ለመደራጀት ፍላጎት ያላቸውን ስራ ፈላጊዎች እና ሰልጣኞችን ውስጣቸው ያለውን ዝንባሌ፣ ተሰጥኦ እና ብቃት ለይተው እንዲያውቁ እንዲሁም በአካባቢያቸው ከሚገኘው ጸጋ ጋር በማስተሳሰር ወደ ተለያዩ ዘርፎች እዲሰማሩ የሚያግዝ አገልግሎት ነው፡፡

የዚሁ አካል የሆነው እና በኦሮሚያ  ክልል አዳማ የተካሄደው  የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ከ2000 በላይ ሰልጣኞችን እና ስራ ፈላጊ ወጣቶች ያለውን እምቅ ችሎታ እና ዝንባሌ ለመለየት አንዲያግዛቸው የሰይኮሜትሪ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምዘና በይፋ ተጀሯል፡፡ ይህ የሳይኮሜትሪ ምዘና በማካሄድ ወጣቶች ያላቸው እምቅ ችሎት እና ፍላጎት እንዲለዩ በማድረግ ተሰጥኦዋቸውን መሰረት ባደረገ የስራ ዘርፎች እዲሰማሩ የሚረዳ ነው፡፡

በተጨማሪም ይህ ስርዓት በአከባቢው ያለውን የተለየ ጸጋ መሰረት ባደረጉ የስራ መስኮችን በመለየት ወጣቶች ካላቸው ዝንባሌ ጋር በማስተሳሰር የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትን የሚያግዝ ነው፡፡
በመረሃ ግብሩ በአጠቃላይ 20ሺህ ሚሆኑ ዜጎችን የስራ ስምሪት በስርዓቱ ለማገግ እቅድ ተይዟል፡፡

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et


🌏✨በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በተቀላጠፈ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በባዮሜትሪከስ የታገዘ ምዝገባ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክም ምዝገባው በተቀላጠፈ መልኩ ቀጥሏል። እንደሚታወቀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደ ሃገር ያላቸው ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ጉልህ መሆኑ ይታወሳል። በአዳማም ኢንዱስትሪ ፓርክም ውስጥ የሚገኘውን የሰው ሃይል በE-LMIS ላይ በማስመዝገብ የሰራተኞችን ማንኛውንም ከሥራ ጋር የተገናኙ መረጃዎች በአንድ ቋት በማስገባት እንደ ሴክተር ከሰራተኛ አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ችግሮች ቁልፍ መፍትሔር በማበጀት ዘርፉን በተሻለ መልኩ ለመምራት እና ለማስተዳደር ያስችላል።

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q


🌏✨በውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት የስልጠና አሰጣጥ ላይ የተሰጠ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ስልጠና፣ ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ከተስተካከለው የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት የስልጠና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለማሰልጠኛ ተቋማት እና ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሰጥ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ልዩ የሥልጠና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫውም ላይ አጠቃላይ ስለ E-LMIS አገልግሎቶችና ስርዓቱ ለሃገር ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን አንድ ሰልጣኝ እንዴት በሲስተሙ ላይ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችል፣ ስርዓቱ ላይ ከተመዘገበም በኋላ የሥልጠና ምዝገባ ማድረግ እንደሚገባው እንዲሁም 21 ቀን የስልጠና ግዜውን ካጠናቀቀ በኋላ ሲኦሲ (COC) ምዘና ማካሄድ እንደሚገባው ከሲኦሲ ምዘናውም በኋላ ብቁ የሆኑትን በሲስተሙ በተሰጣቸው አክሰስ መሠረት እንዴት ማስተላለፍ እንደሚችሉ ከዚህ ቀደም የነበረውን ክፍተት ለመሙላት የተነሱ ጥያቄዎችን ግልፅ በማድረግ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት የስራ አካሄድ ላይ ልዩ ውይይቶች ተደርገዋል።

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/


🌏✨በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው ‹‹የአፍሪካ  የሥራ ፈጠራ ፎረም›› ላይ ስለ E-LMIS የተደረገ የተደረገ ገለፃ!                                                 

በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በቆዳ እና ጨርቃ ጭርቅ፣ በእደጥበብና በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ የተሰማሩ 55 ኢንተርፕራይዞች የተሳተፉ ሲሆን የኢንተርፕራይዞችን ምርቶች ማስተዋወቅ እና ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር መፍጠር የኤግዚብሽኑ ዋና ዓላማ ነበረ።

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማውም የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS  በEnterprise development system ኦንላይን  ኢንተርፕራይዞች ቢመዘገቡ ስለሚያገኟቸው አገልግሎቶች ብሎም በሉሲ ገበያ ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ ምርቶቻቸውን ማስተዋወቅ እና መገበያየት የሚችሉበት ከዛም በላይ በፎረሙ ላይ ከነበሩት Ae  Trade Group አማካኝነት ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው የአፍሪካዊያን የመገበያያ ፕላትፎርም (ሶኮኩ አፍሪካ) በትስስር ለመስራት ባሳዩት ፍላጎት መሰረት ምርቶቻቸውን በአፍሪካ ገበያ በሰፊው ማስተዋወቅ የሚያስችል ስርዓት ሲሆን በተጨማሪም መንግስታዊ ድጋፎችን እንደ የማምረቻ ቦታ፣ የፋይናንስ ድጋፍ እና የብድር አገልግሎት እንዲሁም ሥልጠና ሊያገኙ የሚችሉበትን ልዩ ዕድልን ያመቻቸ ስለመሆኑ በፎረሙ ላይ ስልጠናና ውይይት ተደርጓል።

በመሆኑም ተሳታፊ ኢንተርፕራይዞቹም ባገኙት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስርዓቱ ለሃገርም ሆነ ለኢንተርፕራይዞች ያለውን ትልቅ ፋይዳ መረዳት ችለዋል። አብዛኞቹም በቀረበላቸው ሰፊ ዕድል ለመጠቀም ፍቃደኝነት አሳይተው ስርዓቱ ላይ እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ :https://lmis.gov.et


🌏✨በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ ተጀመረ!

በሥራና ክህሎት ሚኒሰትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በሃገር ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራቸው የሚገኙ ሰራተኞችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ በዚህም መሠረት የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክም ላይ ምዝገባው በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሃገራችን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ከሚያበረክቱ ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው። የኢንዱስትሪ ፓርኩ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ዜጎችን በማሰማራት ለብዙዎች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል። በመሆኑም በስሩ የሚሰሩትን ሰራተኞች በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በበለጸገው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በባዮሜትሪክስ የታገዘ ምዝገባ በማድረግ የሁሉንም ሰራተኞች የት/ት ዝግጅት፣ የስራ ልምድ፣ ያላቸውን ክህሎት እንዲሁም የሰራተኞቻቸውን ማንኛውም ከስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች በአንድ ቋት ስር ማግኘት ተችሏል። ይህም እንደ ሴክተር ከሰራተኛ አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ችግሮች ቁልፍ መፍትሄ በመሆን ዘርፉን በተሻለ መንገድ ለመምራት እና ለማስተዳደር የሚያስችል አቅምን ይሰጣል።

💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et
👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836
📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/

💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1

📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q



Показано 8 последних публикаций.