የሥራ ማስታወቂያ!
Agri-MSMEs Development for Jobs (AMD4J) በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶችና ወጣቶች የሚመሩትን ቢዝነስ እና ኢንተርፕርነርሽፕ እድገትና ምርታማነት በተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የንግድ እድገት ድጋፍ እና የተጠናከረ ኢንተርፕርነርሽፕ ለማበረታታት እየሰራ ባለው ፕሮጀክት በፕሮጀክት ኮኦርድኔተር፣ በፕሮክሩትመንት ኦፊሰር፣ በፕሮጀክት ፋይናንስ ኦፊሰር እና በአካውንቲንግ ክለርክ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
በተጠቀሰው የሥራ መደብ ለመወዳዳር በቅድሚያ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS ተመዝግቦ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመሥጠት የሠራተኛነት መለያ ቁጥር የያዘ መሆን ይጠበቅበታል።
1. ለፕሮጀክት ኮኦርድኔተር
መስፈርት
-በዴቨሎፕመንት ኮርሶች ወይም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም በተዛማጅ ሞያዎች ማስተርስ ዲግሪ ያለው።
-በትንሹ የ10 አመት የስራ ልምድ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በፕሮጀክት አስተባባሪነት፣ በኢንተርፕራይዝ ዴቨሎፕመንት ወይም MSME ላይ በአጋዥነት ያለው
2. በፕሮክሩመንት ኦፊሰር
መስፈርት
- ማስተርስ በፕሮክሩመንት ወይም በሰፕላይ ማኔጅመንት ፊልድ
- የሥራ ልምድ በትንሹ የ6 አመት የሥራ ልምድ ያለው
መስፈርት ለፕሮጀክት ፋይናንስ ኦፊሰር
-ማስተርስ ዲግሪ በአካውንቲንግ ወይም አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ ወይም ፋይናንስ እና ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም ቢዝነስ ማኔጅመንት
- በትንሹ የ8 አመት የሥራ ልምድ ያለው
3. ለአካውንቲንግ ክለርክ
መስፈርት
- በአካውንቲንግ ዲግሪ ያለው
- በትንሹ የ4 አመት የሥራ ልምድ ያለው
ደሞዝ:- በመስሪያቤቱ የደሞዝ ስኬል መሰረት
የሥራ ቦታ:- በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በፕሮጀክት ትግበራ ክፍል ውስጥ
ፃታ:- አይለይም ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
ተፈላጊ ሰራተኛ:- አንድ
ሥራው በኮንትራት ለ12ወራት የሚቆይ ሲሆን እንደ ሠራተኛው የሥራ ችሎታ እና ብቁነት የሚሻሻል ይሆናል።
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ማስረጃችሁን እስካን አድርጋችሁ ከታች በተቀመጠው ኢሜል ማስገባት ትችላላችሁ።
yseid85@yahoo.com/tseget26@gmail.comይህንን የሥራ ማስታወቂያ እና መሰል ተጨማሪ የሥራ እድሎችን ለመጎብኘት
lmis.gov.et ይጎብኙ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!