፯
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ እውነተኛ ጾም፤ ስለ ሐሜት...በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦
የእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ምን ከመነገር ያለፈ እንደ ኾነ፣ እንደ ምን ወሰን እንደሌለው፣ እንደ ምን ከምንም ዓይነት አገላለጽ የራቀ እንደ ኾነ ርግጥ ነው! እዚህ ላይ የተሰደበው ሰውም ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ [ሰውነት] እንዳለውም እውነት ነው፡፡ የተሰደበውም በንግሥናው ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ይህም ቢኾን እርሱ ፊት ለፊት ቆሞ ወይም እያየ ወይም እየሰማ አይደለም፤ “ምንም እንዲህ ቢኾንም ግን እነዚህን ግብራት የፈጸሙ ስዎች በፍጹም ምሕረትን አላገኙም፡፡
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንደዚህ ያለ ነገር በፍጹም አይነገርም፤ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እንዲህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የማይችልና የሰው ቋንቋ መናገር የማይችለው ልዩነት አለና፡፡ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት ያውም ቀኑን ሙሉ ከፊት ለፊት እያለ፣ እያየና እየሰማ ይሰደባል፡፡ እንዲህ ፊት ለፊት፣ እኔው ራሴ በዓይኔ እያየሁና በጆሮዬ እየሰማሁ ተሰደብሁ ብሎ ግን መብረቅ አይልክም፤ ባሕር ተነዋውጻ ምድርን እንድትከድናትና ስዎችን ኹሉ እንድታስጥማቸው አያዝዝም፤ ምድር ተከፍታ የሚሳደቡትን ኹሉ እንድትውጣቸው አያደርግም፡፡ ከዚህ ይልቅ ዝም ይላል፤ ይታገሣል፤ አልፎ ተርፎም የሰደቡት ሰዎች ንስሐ ከገቡና ከእንግዲህ ወዲህ እርሱን ላለመስደብ ቃል ከገቡ እንዲሁ ምሕረቱን ይለግሳቸዋል! በእውነት ያለ ሐሰት፡- “መኑ ይነግር ኃይለ እግዚአብሔር፥ ወይገብር ከመ ይስማዕ ኵሎ ስብሐቲሁ" - "የእግዚአብሔርን ኃይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ኹሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?" ብሎ አሰምቶ የመናገር ጊዜው አሁን ነው (መዝ.105፥2)፡፡
አርአያ እግዚአብሔርን የጣሉ ብቻ ሳይኾኑ በእግራቸው የረገጡ ሰዎች ብዛታቸው ምን ያህል ነው? ባለ ዕዳን ስታንቅ፣ ያለውን ኹሉ ገፍፈህ ስትወስድበት፣ እንደዚሁም በምድር ላይ ስትጎትተው አርአያ እግዚአብሔርን በእግርህ እየረገጥህ ነው፡፡ ይህን ልታውቅ ከወደድህ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ያለውን አድምጥ፦ “ወንድ በሚጸልይበት ጊዜ ሊከናነብ አይገባውም፣ የእግዚአብሔር አርአያውና ክብሩ ነውና" (1ኛ ቆሮ.11፥7)። ዳግመኛም እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ያለውን ስማ፦ “ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” (ዘፍ. 1፥26)፡፡ “ሰውስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አይደለም" ብለህ ከተናገርህ እንዲህ መናገርህ ምን ትርጉም አለው? ምክንያቱም ከነሐስ የተሠራው ሐውልትም ከንጉሡ ጋር አንድ አይደለም፣ ነገር ግን እርሱን [ሐውልቱን] የናቁ ሰዎች ከቅጣት አላመለጡም፡፡ ስለዚህ በሰው ልጅ ዘንድም እንደዚህ ነው፧ ስዎች ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ባይኾኑም [በእርግጥም አይደሉምና] አርአያው ተብለው ግን ተጠርተዋል፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ስለ ተቀበሉት ክብር ሊከበሩ ግድ ነው፡፡
አንተ ግን ስለ ጥቂት ወርቅ ብለህ ከእግርህ በታች ረግጠሃቸዋል፤ ጉሮሮአቸውን አንቀሃቸዋል፤ በምድር ላይ ጎትተሃቸዋል፡፡ ምንም ይህን ኹሉ ብታደርግም ግን [ከእግዚአብሔር ዘንድ] ቅጣትህን እስከ ዛሬ ድረስ አልተቀበልህም!
የዚያን ጊዜም ፈጥኖ ምሕረቱና ቸርነቱ ይደረግልን! ይህን አስቀድሜ የምናገረውና የምመሰክረውም፥ ይህ ደመና አልፎ ሳለ እኛ ግን አሁንም እንደዚህ ባለ ግድየለሽነት የምንቆይ ከኾነ አሁን ከምንፈራቸው በላይ እጅግ ጽኑዓን መከራዎችን እንደምንቀበል ርግጥ ስለ ኾነ ነው፡፡ የንጉሡ ቊጣ የእናንተን ግድየለሽነት ያህል አያስፈራኝምና፡፡
በእውነት ያለሐሰት በሕይወታችን ኹሉ ልንለወጥ ያስፈልገናል እንጂ፤ ከክፋት መራቅ ብቻ ሳይኾን መልካም ምግባርንም ዘወትር ልንሠራ ይገባናል እንጂ ምሕረትን ለማግኘት ብለን ለኹለት ወይም ለሦስት ቀናት የምናደርገው ምሕላ በቂ አይደለም፡፡
በደዌ ዘሥጋ የታመሙ ሰዎች ኹልጊዜ ጤንነታቸውን ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦችን ካልተመገቡና እንቅስቃሴዎችን ካላደረጉ በቀር ለኹሉት ወይም ለሦስት ቀናት ብቻ የሚያደርጉት ዕረፍት ምንም ረብ ጥቅም አይሰጣቸውም፤ በኃጢአት ያሉ ሰዎችም ኹልጊዜ ራሳቸውን ካልገዙ በቀርለኹለት ወይም ለሦስት ቀናት ብቻ መሻሻላቸው ምንም አይጠቅማቸውም፡፡ እንደተባለው ገላዉን የታጠበ ሰው መልሶ በጭቃ ቢንከባለል ምንም ጥቅም እንደማያገኝ ኹሉ፥ ለሦስት ቀናት ንስሐ የገባ ሰውም ከዚያ በኋላ ወደ ቀድሞ ኹኔታው ከተመለሰ ምንም ጠቀሜታን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ እንዲህ አናድርግ፡፡ .....
ይቀጥላል....
(ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 79-96 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)