ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡

ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናትየማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ጾመ ነነዌ ነገ የካቲት 03/2017 ዓ.ም
(feb, 10/2025 G.C) ይገባል፡፡


የነነዌ ሰዎችና እኛ

ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡

ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡

የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡

(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)


#ለመቄዶንያ_በቀጥታ

"ሰውን ለመዳት ሰው መሆን በቂ ነው!"

በሰይፉ የዩቲዩብ ቻናል👇
https://bit.ly/2VgLrdM

በመቄዶንያ የዩቲዩብ ቻናል👇
https://youtube.com/@Mekedonia

CBE & Telebirr 7979
CBE 1000 415056 447

Zelle/CashApp👉 240-938-2992

GoFundMe:
https://gofund.me/1592e065


በአሁኑ ጊዜ እጅግ ውድ በሆኑ ዕብነ በረዶች አብያተ ክርስቲያናትን የሚያንጹ ብዙ ወገኖች አሉ። ግድግዳውን እያንዳንዱ ምሰሶ በውድ ዕቃዎች ያጌጠ ነው። የወርቅ ቅብም ይቀባል። መሰዊያው በከበረ ድንጋይ ይለበጣል። በዚህ ቅዱስ መቅደስ የሚጠቀመው ሰው ግን ትኩረት አልተሰጠውም። ነገር ግን እውነተኛ የሆነው የክርስቶስ አገልጋይ ገብቶ ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጥበት የሚያደርጉ እጅግ ጥቂቶች ናቸው።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
 
ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !
እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣

አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን።

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤ በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤ በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . .ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


(EOTC Broadcasting Service Agency)


የጠዋት ቁርስ ተጋበዙ

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!


ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፡፡ ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡

(የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጆታ ማገዝ የሚፈልግ በውስጥ ማናገር ይችላል)
@natansolo


"ስለ ሰርግ ቀን" የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ወጣቶች ትዳራቸው፥ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኾንላቸው ከፈለጉ ከኹሉም አስቀድመው ሊያደርጉት የሚገባቸው ልክ እንደ ቃና ዘገሊላው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጋቸው ዕለት እንዲገኝ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰርጋቸውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ማከናወን ማለት ነው፡፡

ሊቁም ይህን አስመልከቶ ሲናገር እንደዚህ ይላል፡- “ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በመገኘትና ጸጋውን በመስጠት ሰርግን ቀድሷል፡፡ ሌሎች ይረባል ይጠቅማል ብለው ካመጡት ስጦታ ይልቅ ከፍ ያለ ስጦታ ይዞ በመምጣት ይኸውም ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ ሰርግን አክብሯል፡፡ … ስለዚህ የዲያብሎስ ትርኢትን በማምጣት ጌታችን ያከበረውን ሰርግ አናቃልል፡፡ ወደ ትዳር የሚገቡ ሰዎችም በቃና ዘገሊላ በተደረገው መልኩ ያግቡ፡፡ በመካከላቸው ክርስቶስ እንዲገኝ ያድርጉ፡፡ ‘ይህንንስ እንዴት ሊያደርጉ ይችላሉ? ጌታችን ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በአካል እንደ ተገኘ ዛሬም መገኘት ይችላልን?’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ አዎ! ካህናትን ይጥሩ፡፡ ጌታችን ‘እናንተን የተቀበለ እኔን ይቀበላል’ በማለት ተናግሯልና (ማቴ 10፥40)፡፡

እንደዚህ በማድረግ ዲያብሎስን ያርቁት፦
➛ ጸያፍ ዘፈኖችን፣
➛ ርኵሳን ሙዚቃዎችን፣
➛ ሥርዐት የለሽ ውዝዋዜዎችን፣
➛ አሳፋሪ ንግግሮችን፣
➛ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣
➛ ወሰን የለሽ ሁካታዎችንና ሳቆችን፣

እንደዚሁም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነውርን የተሞሉ ድርጊቶችን ያርቁ፡፡ ከእነዚህ ይልቅ የክርስቶስ አገልጋዮችን ይጥሩ፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋቸው ይገኛል፤ ይታደማልም፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ የተወሰደ)

10k 0 143 275

አገልግሎቱን ለማስቀጠል የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጆታ ማገዝ የሚፈልግ በውስጥ ማናገር ይችላል
@natansolo


ለማሳወቅ ያህል፦

ሰላም የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተሰቦች

ዓመታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ከህዋዌ ተንቀሳቃሽ ሞደም ጋር በአንድ ወንድሜ አማካኝነት በስጦታ ተበርክቶልኝ በዚህ ቻናል የተለያዩ ቅዱሳን አበው በተለይም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጽሑፎችን ስንለቅ እና ስንማማር ከርመናል።

አሁን ላይ ከነገ ጥር 27/2017 ዓም ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ስለሚያልቅ በየዕለቱ የምናስተላልፈው ጽሑፍ እንደባለፉት ጊዜያት በየእለቱ ላይኾን ስለሚችል ከወዲኹ ይቅርታ እየጠየቅን፥ የኢንተርኔት አክሰስ ሲገኝ ግን አጋጣሚውን በመጠቀም የተለመደውን አገልግሎት የምንሰጥ ይሆናል።

@natansolo


ባሎች ለሚስቶቻቸው ሊያሳዩአቸው የሚገባ
           ፍቅር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሚስትህ ለአንተ ትገዛልህ ዘንድ ትሻለህን? ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት አንተም እንዲሁ ለሚስትህ አድርግላት፡፡ ሕይወትህን ስለ ርሷ አሳልፈህ መስጠት ካለብህ ስለርሷ ሕይወትህን አሳልፈህ ስጥ፤ መከራም መቀበል ካለብህ መከራን ለመቀበል አትሰቀቅ፡፡

አንተ ይህን ብትፈጽመው ስንኳ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ካደረገላት ጋር ሲነጻጸር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንተ ይህን ያደረግኸው ከአንተ ጋር ፈጽማ ለተዛመደችህ ለአንዲት ሴት ነው፡፡ “እርሱ ግን ከእርሱ ለተመለሰችውና ለጠላቸው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡” ርሱ ከርሱ የተመለሰችውንና የጠላችውን እንዲሁም ያቃለለችውን ገንዘቡ ሲያደርጋት በማስፈራራት፣ በማስገደድ ወይም ይህን በመሳሰሉ ነገሮች አልነበረም፤ ነገር ግን ኀዘን ባልተቀላቀለበት ፍጹም በሆነ ፍቅር በመሆን ነበር፡፡ አንተም ለሚስትህ እንዲሁ አድርግላት አዎን! ምናልባት ሚስትህ አንተን ልታመናጭቅህ፣ ልትንቅህ፣ ልታፌዝብህም ትችላለች፤ ቢሆንም ግን አንተ ለርሷ ካለህ አርቆ አሳቢነት ንጹሕ ፍቅርና ኀዘኔታ የተነሣ ልትታገሣት ይገባሃል፡፡

ከሰው ሁሉ ጋር ተስማምቶ ለመኖርም ከእነዚህ የተሻሉ ነገሮች ፈጽሞ አናገኝም፡፡ በተለይም ለባልና ለሚስት፡፡ አንድ ሰው አገልጋይ ባሪያውን በማስፈራራት ለመግዛት ቢሞክር ለጥቂት ጊዜአት ሊገዛለት ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ባሪያ እንዲህ ዓይነት አገዛዝ ስለማይመቸው ከእርሱ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው የሕይወቱን አጋር፣ የልጆቹን እናት፣ የደስታው ሁሉ ምንጭ የሆነችውን ሚስቱን በፍቅርና በፍጹም አክብሮት እንጂ ልክ እንደ ባሪያ በፍርሃት ሰንሰለት በማሰር ወይም በማስጨነቅ ርሷን ሊገዛት መሞከር አይገባውም፤ ሚስት በባልዋ ምክንያት የምትሸበር ከሆነ አንድነታቸው ምን ዓይነት አንድነት ነው? ከባሪያ ጋር እንደ መኖር ከሚስት ጋር መቀመጥ ለባል የሚፈጥርለት ምን ዓይነት ደስታ  ነው? አዎን ይልቁኑ አንተ ስለ ርሷ ስትል ብዙ መከራዎችን መቀበል ሲገባህ በተቃራኒው በቁጣ ርሷን በማስጨነቅና በማሸበር ታስፈራራታለህን? ክርስቶስ እንዲህ አላደረገም፡፡

“በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ አንዲቀድሳት ስለ ርሷ (ስለ ቤተ ክርስቲያን) ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ቤተ ክርስቲያን (እኛ) አስቀድማ ንጽሕት አልነበረችም፤ ጉድፍ ነበረባት፤ መልከ ጥፉም ነበረች፡፡ ስለዚህም ለእርሱ የተገባች አልነበረችም፡፡ አንተ እንደ ቤተ ክርስቲያን የሆነችውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ አትመርጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ የተለየችውን ያህል ከአንተ ፈጽማ የማትስማማውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ ወደ አንተ አታቀርባትም፡፡ እርሱ ግን እጅግ መልከ ጥፉ ብትሆንም አልጠላትም፣ አልተጸየፋትም፣ ስለ መልከ ጥፉነቷ የተጻፈውን መስማት ትፈልጋለህን? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ርሷ ምን እንደሚል ስማ “ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ” (ኤፌ.፭፡፰) አላት፤ የገጽታዋን መጥቆር ትመለከታለህን? ከጨለማስ የበረታ ጥቁረት ምን አለ? የአመሏን መክፋት ደግሞ ስማ “በክፋትና በምቀኝነት” ይልና “የምንኖር” ይላል፤ ስለ ነውሮቿ ደግሞ “የማንታዘዝና የምንስት ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ” ይላታል (ቲቶ.፫፡፫)፡፡

ነገር ግን ለርሷ ስለተደረገላት በጎነት ምን ማለት ይቻለኛል? ርሷ ስንፍናን የተሞላችና ክፉ አንደበት የነበራት እንዲሁም በነውሮቿ ሁሉ ያደፈች ብትሆንም እነዚህ ሁሉ ጠባዮቿ ከርሷ አላራቀውም፡፡ ነገር ግን ልክ የደስ ደስ እንዳላት ልጃገረድ በአፍቃሪም ዘንድ ለምትወደድ ውብ ሴት እንደሚደረገው ርሱ ስለ ርሷ ራሱን አሳልፎ የሰጠ አይደለምን? ይህንንም በማድነቅ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለጽድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት ስንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኛል” ይልና “ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና”(ሮሜ.፭፥፯-፰) ብሎአል፡፡ በዚህ መልክ ርሷ ለርሱ  ትሆን ዘንድ አቀረባት፤ በመንፈሳዊ ውበትም አስጌጣት፤ ንጽሕት አደረጋት፤ ስለ ርሷም ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ስንኳ የጨከነ ሆነ፡፡

(የትዳር አንድምታ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ገጽ 17-19 - በመምህር ሽመልስ መርጊያ)

12.2k 0 261 8 172

“ላገቡት” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ባልና ሚስት አንድ መኾናቸውን ብዙ ጊዜ ስለ ተማራችሁት እርሱን አልደግምላችሁም፡፡ ከዚህ ተነሥቼ ግን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦ ከሰውነታችሁ ውስጥ አንዱ ሕዋስ ቢታመም ቆርጣችሁ ትጥሉታላችሁን? ከሕመሙ ይፈወስ ዘንድ የምትጥሩ አይደላችሁምን? ለትዳር አጋራችሁም እንደዚህ መኾን አለባችሁ፡፡ እንደዉም'ኮ፥ ከሰውነታችሁ ሕዋስ ውስጥ ያለው በሽታ አንዳንዴ ላይድን ይችላል፡፡ የትዳር አጋራችሁ ግን፥ ምንም ክፉ ቢኾንም ሊለወጥ ይችላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚኖረው አንዳንዱ ችግር ለምሳሌ ልምሾ እጅ ወይም እግር ሥራ መሥራትን ሊከለክለን፣ በሌላዉ የሰውነታችን ክፍል ላይ ጫና ሊያሳድርብን ይችላል፤ ነገር ግን ይበልጥ እንክብካቤ እናደርግለታለን እንጂ ቆርጠን አንጥለዉም፡፡ ታዲያ መዳን ለማይችለው ሰውነታችን ይህን ያህል እንብካቤ እያደረግንለት ሳለ፥ የመዳን (የመለወጥ) ዕድል ያለው አካላችንን (ባለ ትዳራችንን) መቁረጥ (መፍታት) እንደ አማራጭ ማስቀመጣችን እንዴት ብናብድ ነው?

21.9k 1 298 9 229

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ

“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)

11.8k 0 271 4 192

አንድ ደቂቃ ወስደው ያንብቡት ድንቅ ምክር ነው
(ለሌሎች ያጋሩት)

በሠርጉ ዋዜማ እናት ወንድ ልጇን ምን አለችው?


የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ!

አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት አንተ የማትረባ ስለው በጣም ተሸማቀቀ ወደ እኔ እየተመለከተ እንዴት እንደሱ ትያለሽ ? ሲለኝ ቀበል አድርጌ አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር።

ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ!

ካቋረጥኩበት ልቀጥል...... ልክ ብቻየን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ .. ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት እርሱም ተቀበለኝ .. ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ።

አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን። በደንብ አድምጣት ጋሻና መከታ ሁናት በጭንቅ ግዜ ከጎኗሁን ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሓሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር።

ልጄ.. . አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዟቸው ነበር አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ጨው አልጨመርኩም ነበር በጣም አፈርኩኝ አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍላጎቱ ጨምረው ተመገቡ።

እንግዶችም በሄዱ ግዜ ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ስለዋሸው ይቅር በለኝ አለ።

ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት።

ልጄ.. . ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ.. .ወሲብ ጥሩ ነገር ነው።ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል እኔ ግን እስከዚህ እሆናለው... አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት።

አስቸጋሪ ግዜያት ይመጣል አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር  ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ክፍል ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ግን አልተቃወምኩም ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት ምን ሆነሻል? አለኝ ምንም አልኩት ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነት ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት።

ልጄ.. .ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ብልህ ሁን።

እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ፀልዩበት ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር ።

በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው አንተ ምርጥ ልጄ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ሁሌም የእርሱን እርዳታ እሻ!!

(Anani Moti)

11k 0 263 4 267

ተወዳጆች ሆይ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጥቶ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነውን? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነውና፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡

ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

10.4k 0 136 1 192

"እስኪ ከእኔ ጋር ሆናችሁ ቅዱስ ዳዊት ምን ያህል እግዚአብሔርን ከልቡ ይወደው እንደነበር እናስተውል። ቀን ቀን ያስባቸው ዘንድ ግድ የሚሉት የመሪዎች፣ የአዛዦች፣ የመንግሥታቱ፣ የሕዝቡ፣ የሠራዊቱና ስለ ጦርነት ውሎዎቹ፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ፖለቲካውና በቤቱ ውስጥ ወይም ከቤቱ ውጪ ወይም በጎረቤቶቹ ዘንድ ስላለው ችግር ማውጣት ማውረዱ ልቡን ከፍለው ይወስዱበታል።

በዕረፍት ጊዜው እያንዳንዱ ሰው ለመኝታው የሚጠቀምበትን ሰዓት እርሱ ደግሞ ለንስሐ ለጸሎትና ዕንባውን ለማፍሰስ ይጠቀምበታል፡፡ እንዲህ ያለ ተግባሩን የሚፈጽመው ዛሬን አድርጎ ነገን ሳያደርግ አይደለም። ወይም ደግሞ ሁለት ወይም ሦስት ሌሊት በማለፍ አይደለም፤ በእያንዳንዷ ሌሊት እንጂ፡፡ «ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣ መኝታዬንም በዕንባዬ አርሳለሁ።» የሚለው ቃል የዕንባውን ብዛትና ዕንባው አለማቋረጡን ይገልጽልናል፡፡

እያንዳንዱ ፀጥ ባለ ዕረፍት ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ እርሱ ግን እግዚአብሔርን ብቻውን አግኝቶ ለዕንቅልፍ ባልተከደኑ ዓይኖቹ ያለቀስና ያዘነ የግል ኃጢአቶቹን ይነግረዋል፡፡ አንተም ብትሆን እንዲህ ዓይነቱን አልጋ ለራስህ ታበጅ ዘንድ ይገባሃል። በወርቅና ብር ተከበህ መተኛት ከሰዎች ቅናትን ከአርያም ደግሞ ቁጣን ይቀሰቅስብሃል፡፡ እንደ ዳዊት ያለ ዕንባ ግን የሲዖልን እሳት ያጠፋል፡፡

ሌላ አልጋ ደግሞ ላሳይህን? ይህ አልጋ የያዕቆብ ነው። ለስውነቱ ባዶ መሬትን ለትራሱ ደግሞ ድንጋይን የተጠቀመበት አልጋ! ይህ በመሆኑም ያን መንፈሳዊ ድንጋይና ያቺን መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት የነበረችውን መሰላል ሊመለከት ችሏል፡፡ (ዘፍ 28፣ ከ1ኛ ቆሮ 10፥4 ጋር አዛምድ፡፡) በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ድንጋዮች ለክርስቶስ ምሳሌ ሆነው ተጠቅሰዋል፡፡ እኛም እንዲህ ያሉ ሕልሞች እናይ ዘንድ ሕሊናችንን እንደዚህ ባሉት አልጋዎች ላይ እናሳርፍ፡፡ ነገር ግን ከብር በተሠሩ አልጋዎች ላይ ብንተኛ ደስታን ብቻ ሳይሆን የምናጣው ችግርንም እንጋፈጣለን፡፡

እጅግ በጣም ቀዝቃዛ በሆነ እኩለ ሌሊት አንተ በአልጋህ ውስጥ ተኝተህ ሳለህ ድሀው ሰው ግን በጭድ ክምር ላይ በደጅህ ወድቆ በብርድ እየተንቀጠቀጠና በረሀብ እየተገረፈ ተዘርግቷል:: አንተ ከስዎች ሁሉ ልበ ደንዳና ብትሆን እንኳ ለዚህ ለድሀ የሚገባውን ሳታደርግለት ለራስህ አላስፈላጊ ምቾቶችን መፍቀድህ እርግጠኛ ነኝ ራስህን እንድትረግም ያደርግሃል። «የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያቆላልፍም።» (2ኛ ጢሞ. 2፥4) ተብሎ ተጽፏልና፡፡

አንተም መንፈሳዊ ወታደር ነህ፡፡ እንዲህ ያለ ወታደር ደግሞ በመሬት ላይ ይተኛል እንጂ ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ አይተኛም፤ እጅግ ያማረ ሽቶም ኣይቀባም፡፡ እንዲህ ያለው ተግባር በመድረክ ላይ እየተወኑ በግድ የለሽነት ከሚኖሩና ከጋለሞታ ሴቶች ጋር ጊዜያቸውን በማባከን የሚኖሩ የምግባረ ብልሹ ሰዎች ተግባር ነው፡፡ የእኛ ጥሩ መዓዛ ግን ሽቱ ሳይሆን መልካም ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡ በሽቱ መዓዛ ከሚመጣው ጠንቅ የበለጠ ነፍስን የሚያቆሽሽ ነገር አይኖርም፡፡ በአብዛኛው አፍአዊ (ውጪያዊ) መልካም መዓዛ የሰው ውስጣዊ ማንነት ማደፍና መቆሸሽ ምልክት ነው፡፡

ዲያብሎስ ነፍስን በራስ ወዳድነት ተዋግቶ ሲያሸንፋትና በታላቅ ከንቱነት ሲሞላት አስቀድሞ አቆሽሾት ወይም አጉድፎት ወይም አበልዞት የነበረውን ሰውነት በሽቶ ያጸዳዋል:: ልክ በጉንፋን እንደተያዙና ያለማቋረጥ በአፍንጫቸው የሚወጣውን ፈሳሽ ለማጽዳት ልብሳቸውን፣ እጆቻቸውንና ፊታቸውን እንደሚያጎድፉ ሁሉ እንዲህ ያለው የክፉ ስው ነፍስም ሰይጣን በሰውነቱ ላይ ያፈሰሰበትን ኃጢአት ለማጽዳት ይሞክራል፡፡ ሽቶ ሽቶ ከሚያውድ፣ ከጋለሞታ ጋር ወዳጅነት ከመሠረተ፣ የዳንኪረኛነት ሕይወትን ከሚመራ ሰው ማን ጨዋና መልካም ነገርን መጠበቅ ይችላል? እስቲ ነፍስህ መንፈሳዊ መዓዛን ትተንፍስና ለአንተም ሆነ ለወዳጆችህ ታላቅ በረከትን ታድላቸው፡፡"

(ሀብታምና ድሀ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሰበከው -ገጽ 21-23 አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው)

11.4k 0 116 4 153



አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ)

22.8k 1 196 7 159


11.3k 0 115 7 353

"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም።

እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡


ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"

15.3k 1 141 11 343

አበው ስለ #እመቤታችን_ዕረፍት እንዲህ አሉ፦

"ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች "ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ።"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

"ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው። በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ

"የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ

(በ Deacon Henok Haile የተሰበሰበ)

Показано 20 последних публикаций.