💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 78 💙
▶️፩. 2ኛ ዜና መዋ.23፥6 ላይ የብሉይ ሌዋውያን ቅዱሳን ናቸው ከተባለ አሁንስ በሐዲስ ኪዳን ያሉት ካህናት ቅዱሳን ናቸው መባል አይቻልም?
✔️መልስ፦ እነርሱ ቅዱሳን ናቸው ማለት የተለዩ ናቸው ማለት ነው። ቀደሰ-ለየ በሚለው ነው የሚተረጎም። ሌዋውያን ቤተ መቅደስን ለማገልገል የተመረጡ ስለሆኑ ቅዱሳን ተብለዋል። በዚህ አግባብ የሐዲስ ኪዳን ካህናትም ከሌላው ምእመን እግዚአብሔርን በክህነት ለማገልገል የተለዩ ስለሆኑ ቅዱሳን ልንላቸው እንችላለን። ምሥጢሩ ለአገልግሎት መለየትን ያመለክታል።
▶️፪. 2ኛ ዜና መዋ.23፥7 ላይ ሌዋውያን እንዴት የጦር መሣሪያ ሊይዙ ይችላሉ?
✔️መልስ፦ ካህን ጦር ይዞ መግጠም የማይችል በሐዲስ ኪዳን ነው እንጂ በብሉይ ኪዳን ጦር መያዝ አይከለከሉም ነበረ። እንዲያውም አንዳንድ ካህናት ክፉ ሰዎችን በጦር ወግተውም ይገድሉ ነበር። ለምሳሌ ፊንሐስ ያልተገባ ሥራ የሠሩ ሰዎችን ገድሏል። በመግደሉም ኃጢአት አልሆነበትም። እንዲያውም እግዚአብሔር ተደስቶበታል። አሁን በሐዲስ ኪዳን ግን ካህን ጦር ይዞ መግጠምና መግደል አይገባውም። አሁን ካህን ሰው ቢገድል ክህነቱ ይሻራል።
▶️፫. 2ኛ ዜና መዋ.23፥14 ላይ በእግዚአብሔር ቤት መገደል እና ከዚያ ውጪ መገደል ያው መገደል አይደለም እንዴ? ለምን የተለየ ሆኖ ተቀመጠ?
✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ቤት የተባለው ቤተመቅደስ ቅዱስ ቦታ ስለሆነ በቤተመቅደስ ደማቸው እንዳይፈስ ከቤተመቅደስ አስወጥተው ገድለዋቸዋል።
▶️፬. 2ኛ ዜና መዋ.21፥20 ላይ ኢዮራም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የ32 ዓመት ጎልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም 8 ዓመት ነገሠ ይላል። ከዚያ 2ኛ ዜና መዋ.22፥2 ላይ ልጁ አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው 42 ዓመት ነበረ ይላል፡
እንዴት ነው አባትየው በ40 ዓመቱ ሲያርፍ ልጁ 42 የሆነው የነገሠው ወዲያው እንዳረፈ ነውና።
✔️መልስ፦ የቅጂ ስሕተት ነው እንጂ 2ኛ ዜና መዋ.22፥2 አካዝያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው 42 ሳይሆን 22 ነው። ግእዙ በትክክል ገልጾታል። "ከዊኖ ወልደ ዕሥራ ወክልኤቱ ዓመት ወነግሠ አካዝያስ። ወአሐተ ዓመተ ነግሠ በኢየሩሳሌም። ወስማ ለእሙ ጎቶልያ ወለተ ዘምሪ" እንዲል።
▶️፭. ኢዮራም ወንድሞቹን የገደለበት ምክንያት ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ሌሎች ወንድሞቹ ከእርሱ የተሻሉ ስለነበሩ መንግሥቴን ይቀናቀኑኛል ብሎ ሰግቶ ገድሏቸዋል።
▶️፮. አካዝያስ ሁሉም እህት እና ወንድሞቹ ተገድለው አይደል እሱ የነገሠው? ኢዩ የትኞቹን ወንድሞቹን ነው የገደላቸው?
✔️መልስ፦ የአካዝያስ ሁሉም እህት ወንድሞቹ ተገድለው ነበረ። የወንድሞቹና የእህቶቹ ልጆች ግን እንደተገደሉ አልተገለጸም ነበር። ስለዚህ ኢዩ የገደላቸው አካዝያስንና የአካዝያስን የወንድሞቹን ልጆች ነው።
▶️፯. "በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ ነገር ግን በፍጹም ልብ አይደለም" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.25፥2)። ሁለቱን ሐሳቦች ልዩነታቸውን ቢያብራሩልን።
✔️መልስ፦ በእግዚአብሔር ፊት ቅን አድርጓል። ነገር ግን በፍጹም ልቡ አልነበረም። ይህም ከዚሁ ምዕራፍ ቁጥር 14 ላይ እንደተገለጸው ቆይቶ ጣዖት ስላመለከ ነው።
▶️፰. 2ኛ ዜና መዋ.24፥25 ኢዮአስን የገዛ ባሪያዎቹ ስለ ካህኑ ስለ ኢዮአዳ ልጅ ደም ተበቅለው በአልጋው ላይ ገደሉት ይላል። 2ኛ ዜና መዋ.25፥3 ላይ ደግሞ አሜስያስ አባቱን የገደሉትን ባርያዎች ገደለ ይላል። አባቱም በግፍ ስለሆነ የካህኑን ልጅ ደም ያፈሰሰው እነሱም ልክ ነበሩ ማለት አንችልም? ማን ነው ቅን ፍርድን ያደረገው? በዚያውም ላይ ዝቅ ብሎ እንደ እግዚአብሔር ሕግ ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጅ ማንም በማንም ኃጢአት አይሙት ብሎ እንዳዘዘ ልጆቻቸውን ግን አልገደለም ይላል። 2ኛ ዜና መዋ.21፥14 ግን ንጉሡ ኢዮራም ስለ በደለ እግዚያብሔር ሕዝብህንና ልጆችህን ያለህን ንብረት ሁሉ በታላቅ መቅሠፍት ይቀሥፋል ይላል። ሁለቱ እንዴት ነው የሚታረቀው?
✔️መልስ፦ የኢዮአስ መሞቱ ፍትሓዊ ነው። የባርያዎቹ ኢዮአስን መግደል ግን ፍትሓዊ አይደለም። ዳኛ ሳይሆኑ የሞት ፍርድ ፈርደውበታልና። አሜስያስ ንጉሥ ዳኛ እንደመሆኑ የአባቱን ገዳዮች መግደሉ ፍትሓዊ ያሰኘዋል። 2ኛ ዜና መዋ.21፥14 ላይ ልጆቹም የተቀሠፉት እግዚአብሔር ባወቀ ሞት ይገባቸው ስለነበረ ነው። እንጂ በአባት ኃጢአት ልጅ አይገደልም።
© በትረ ማርያም አበባው
🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።