ማንኛውም ሰው፦
1. ትላንትን የሚያውቅ፣
2. ዛሬን የተረዳ
3. ነገን የሚያይ ሊሆን ይገባል።
በነገራችን ላይ ከሰው ጋር የፈለገ ብትጣሉ ጉዳይ ተኮር ሆኖ ጉዳዩን መሞገት እንጂ ግለሰብን አትሳደቡ። ቢሰድባችሁ እንኳ አትመልሱለት። ይህ ሁለት ጥቅም አለው።
፩. በታረቃችሁ ጊዜ አትጸጸቱም
፪. በእግዚአብሔር ፊት አታፍሩም
ስለዚህ ዕርቅ ሊኖር ስለሚችል መሰዳደብ ስለሚያቀል ስድብን ትቶ ጉዳይን መሞገት መልካም ነው። በተለይ ፖለቲከኞች ነገን አስባችሁ ሥሩ። አንዳንዶቻችሁ በዛሬ ሞቅታ ብዙ ነገር ትናገሩና ነገን ፈርታችሁ እንድትኖሩ ትገደዳላችሁ። ሥልጣንም፣ ገንዘብም ሁሉም ያልፋሉ። ቋሚ አይደሉም። ስለዚህ ነገ የሚያሳፍራችሁን
ነገር ዛሬ ላይ አትሥሩ።
ሌላው ሁሉም ሰው መዘንጋት የሌለበት ሞትን ነው። ሁላችንም አንድ ቀን እንሞታለን። የሰው ሕይወት በሞት የሚያበቃ አይደለም። ከሞት በኋላ ትንሣኤ አለ። ነገር ግን ምድር ላይ በሠራነው ሥራ መሠረት ደግ ከሠራን በዘለዓለማዊ ደስታ፣ ክፉ ከሠራን በዘለዓለማዊ ሰቆቃ እንኖራለን። ዛሬ በምንሠራው ሥራ፣ በምንናገረው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንጠየቅበታለን። በእርሱ ፊት እንዳናፍር ትክክለኛውን ነገር እናድርግ።
© በትረ ማርያም አበባው
ፎቶ፦ ጎንደር ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን