▶️፰. ምሳ.6፥16 ላይ "እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው። ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች" ይላል። ስድስት ነገሮች እና ሰባትንም የተባሉ ምን ምን ናቸው?
✔️መልስ፦ ከቁጥር 17 ጀምሮ የጠቀሳቸው ናቸው። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ፦ ከፍ ዝቅ እያደረገ የሚያይ ዐይን
2ኛ፦ ሐሰተኛ አንደበት
3ኛ፦ የጻድቁን ደም የሚያፈስ እጅ
4ኛ፦ ክፉ ሐሳብን የምታስብ ልቡና
5ኛ፦ ክፉ ነገር ለማድረግ የሚሄድ እግር
6ኛ፦ በሐሰት የሚመሰክር ሰው
7ኛ፦ በወንድሞች መካከል ጸብን የሚያመጣ
▶️፱. ምሳ.8፥30 ላይ "የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርኹ። ዕለት ዕለት ደስ አሠኘው ነበር። በፊቱም ዅልጊዜ ደስ ይለኝ ነበር" ይላል። እኔ ያለው ማን ነው?
✔️መልስ፦ ከዚህ እኔ እያለች የምትናገረዋ ተናጋሪ ጥበብ ናት።
▶️፲. "እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና። ስለ ነፍሱ ርኩሰትም ይደቅቃልና" ይላል (መዝ.6፥16)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ይህ የተነገረ ስለ ክፉ ሰው ነው። ክፉ ሰው እግዚአብሔር የሚጠላውን ሥራ ይሠራል ማለት ነው። ስለነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና ማለት ክፉ ሰው በሚሠራው ክፉ ሥራ ራሱ ይጎዳል ማለት ነው።
▶️፲፩. "የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው" ይላል (ምሳ.6፥26)። እስከ አንዲት እንጀራ ነው ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ እስከ አንዲት እንጀራ ናት ማለት አመንዝራ ሴትን መውደድ አንዲት እንጀራን እስከ ማሳጣት ያደርሳል ማለት ነው። አመንዝራ ሴት ሀብትን ትበዘብዛለች ማለት ነው።
▶️፲፪. ምሳ.7፥16 "በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ። የግብፅንም ሽመልመሌ ለሀፍ" ይላል። ሽመልመሌ ለሀፍ ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሸመልመሌ ለሐፍ የሚለው የልብስ ዓይነት ነው። የተዝጎረጎረ ልብስ ማለት ነው።
▶️፲፫. ምሳ.9፣7 ላይ "ክፉዎችን የሚያስተምር ለራሱ ውርደትን ይቀበላል። ኃጥኣንንም የሚገሥጽ ራሱን ያዋርዳል" ሲል ክፉዎችንና ኃጥኣንን መገሠጽ አይገባም ማለት ነው?
✔️መልስ፦ አይደለም። ክፉዎችን ሰዎች ከክፋታቸው እንዲመለሱ ማስተማርና መገሠጽ አስፈላጊ ነው። እነዚህን ለማስተማር የተዘጋጀ ሰው ግን ሥጋዊ ውርደት ይገጥመዋል ማለት ሊንቁት፣ ሊዘልፉት፣ ሊያቃልሉት ይችላሉ። በነፍሱ ግን ክብርን ያገኝበታል ለማለት ነው። በተጨማሪም በተደጋጋሚ ተመክሮ አልመለስ ያለን ሰው መራቅ እንደሚገባ የሚያመለክት ቃል ነው።
▶️፲፬. ምሳ.፯፥፲፩ ላይ "ሁከተኛና አበያ ናት" ይላል። ሁከተኛ እና አበያ ማለት ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሁከተኛ ማለት በጥባጭ ማለት ነው። አበያ ማለት ደግሞ ሰነፍ ማለት ነው። ክፉና አመንዝራ ሴት ሰነፍና በጥባጭ ናት ማለት ነው።
▶️፲፭. "ሌባ በተራበ ጊዜ ነፍሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም" ይላል (መዝ.6፥30)። ሌባውን ሰዎች ቢሰርቅ አይንቁትም ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ አይንቁትም የተባለው አንጻራዊ ንቀት ነው። ሌባ ከአመንዝራ ይሻላል ማለቱ ነው። ይኸውም የሰረቀ የሚበላው ቢያጣ ነው ብለው ሰዎች ያስቡለታል ለማለት ነው እንጂ ሁለቱም ገሀነም የሚያስገቡ ክፉ ሥራዎች ናቸው። እጅ ከፍንጅ ሲያዝ የሰረቀውን ሰባት እጥፍ እንዲከፍል ቀጥሎ ቁጥር 31 ላይ ተገልጿልና። ስለዚህ በአንጻር ተናገረ እንጂ ሌብነትም ማመንዘርም ሁለቱም ታላላቅ ኃጢአቶች ስለሆኑ መጠንቀቅ ይገባናል። ብንቸገር እንኳ መለመን እንጂ መስረቅ አይገባንም።
▶️፲፮. "የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል። የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሠኛል" ይላል (መዝ.9፥17)። ምሥጢሩ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ የተጠማ ሰው ውሃ ሰርቆ ሲጠጣ ደስ ይለዋል። ማለት ጥሙን ያስወግድበታል። በዚህ ጊዜ ምሥጢሩን በጥንቃቄ መረዳት አስፈላጊ ነው። ከዚህ ደስ ያሰኛል ያለው ጥሙን ስላራቀለትና ስለሚያርቅለት እንጂ በመሰረቁ አይደለም። ስርቆት ታላቅ ኃጢአት ነውና። የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል መባሉ የተራበ ሰው በልቶት ከረኀቡ ይላቀቃልና ረኀቡን በማስለቀቁ የተነገረ ነው።
▶️፲፯. ምሳ.6፥5 ላይ "እንደ ወፍ ከጭራ ወጥመድ" ሲል የጭራ ወጥመድ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ የጭራ ወጥመድ ማለት ከጭራ የሚሠራ ወጥመድ ማለት ነው። ጭራውን ጎንጉነው ወይም ፈትለው ወፍን ለመያዝ ያጠምዱታልና ስለዚህ የተነገረ ነው።
▶️፲፰. መዝ.6፥12 ላይ "በዐይኑ ይጠቅሳል፣ በእግሩ ይናገራል፣ በጣቱ ጥቅሻ ያመለክታል" ይላል። ትርጓሜው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ይህ ስለአመፀኛ ሰው የተነገረ ነው። አመፀኛ ሰው ክፉ ሥራን ለመሥራት በዐይኑ ይጠቅሳል ማለት ክፉ ነገርን በዐይኑ ጠቅሶ ያሳያል ማለት ነው። በእግሩ ይናገራል ማለት በእግሩ ጎሰም አድርጎ ያሳያል ማለት ነው ማሳየቱን መናገር ብሎት ነው። በጣቱ ጥቅሻ ያመለክታል አለ ክፉ ሥራን ያሳያል ማለት ነው።
▶️፲፱. "በዐይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል። ደፍሮ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል" ይላል (ምሳ.10፥10)። በዐይን መጥቀስ ኀጢአት ነው?
✔️መልስ፦ በዐይን መጥቀስ ብቻውን ኃጢአት አይደለም ኃጢአትም አይሆንም። ነገር ግን ለክፉ ነገር በዐይን መጥቀስ ኃጢአት ይሆናል። ከዚህ ምዕራፍ የተገለጸውም ለክፉ ነገር መጥቀስ እንደማይገባ ነው።
▶️፳. "የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው" ይላል (ምሳ.10፥20)። የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው የተባለው ከምን አንጻር ነው?
✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ብር የተባለው የወረቀቱ ብር ሳይሆን የመዓድኑ ብር ነው። በተለምዶ ሁለተኛ ደረጃ የሆኑ ተሸላሚዎች የሚሸለሙት መዓድን ነው። ወርቅን በእሳት በማቅለጫ ሲፈትኑት ማለት ሲያቀልጡት ጥራቱ እየጨመረ እንደሚሄድ ሁሉ የጻድቅ ሰው ምላስም የተፈተነ ነው ማለት ሐሜትና ቧልት በጠቅላላ ክፉ ነገርን የማይናገር የጠራ ነው ማለት ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።