💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 158 💙
▶️፩. "ትውልድ ይኼዳል። ትውልድም ይመጣል። ምድር ግን ለዘለዓለም ነው" ይላል (መክ.1፥4)። ምድር ያለው ምንን ነው?
✔️መልስ፦ ምድር ያላት ይህችን የምንኖርባትን መሬት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘለዓለማዊነት በሁለት ይተረጎማል። አንደኛው ብዙ ዘመንን ዘለዓለም ይለዋል። ሌላኛው ፍጻሜ የሌለውን ነገር ዘለዓለም ይለዋል። ከዚህ ምድር ግን ለዘለዓለም ነው ሲል ሰው ሰባ ሰማንያ ዓመት ብቻ ኖሮ ሲሞት ምድር ግን ብዙ ዘመን ትኖራለች ማለት ነው።
▶️፪. "ለማልቀስ ጊዜ አለው። ለመሣቅም ጊዜ አለው። ዋይ ለማለት ጊዜ አለው። ለመዝፈንም ጊዜ አለው" ይላል (መክ.3፥4)። ለመዝፈንም ሲል ለመዘመር ማለት ነው?
✔️መልስ፦ መጻሕፍት መዝሙርን ዘፈን እያሉ የሚገልጹበት መንገድ አለ። ከዚህ ለልቅሶ ጊዜ አለው ማለቱ ሰው ተቸግሮ፣ መከራ ደርሶበት የሚያለቅስበት ጊዜ አለ ማለት ነው። ለመዝፈንም ጊዜ አለው ማለት ሰው ደስ ብሎት የሚያመሰግንበት ጊዜም አለ ማለት ነው እንጂ ዘፈን ጽድቅ የሚሆንበት ጊዜ አለ ለማለት አይደለም።
▶️፫. "ለመውደድ ጊዜ አለው። ለመጥላትም ጊዜ አለው። ለጦርነት ጊዜ አለው። ለሰላምም ጊዜ አለው" ይላል (መክ.3፥8)። ለመጥላትም ጊዜ አለው የተባለው ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ለመጥላት ጊዜ አለው ማለት እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በበደላቸው ምክንያት የሚጠላበት ጊዜ አለ ማለት ነው። ይህም እግዚአብሔር በባሕርይው ጥላቻ ኖሮበት የሚጠላቸው ሆኖ አይደለም። እርሱ በባሕርይው ፍቅር ነውና። በበደላቸው ምክንያት ይፈርድባቸዋል ለማለት ነው።
▶️፬. መክ.2፥14 ላይ "የጠቢብ ዓይኖች በራሱ ላይ ናቸው" ሲል ምን ማለት ነው? ቢብራራ።
✔️መልስ፦ የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው ማለት የራሱን በደል እየመረመረ፣ ንስሓ እየገባ ይኖራል ማለት ነው። እንዲሁም በራስ ያለ ዓይን ወደ ሰማይ እንደሚመለከት ጠቢብ ሰውም ሰማያዊ ነገርን ይመለከታል ማለት ነው።
▶️፭. መክ.5፥18 ላይ "ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው። ይህ ዕድል ፈንታው ነውና" ይላል። ካልተሳሳትኩ ከዚህ በፊት እንደተማማርነው ዕድል ፈንታ የሚባል ነገር በሃይማኖት እንደሌለ አይተናል። ወይስ ዕድል እና ዕድል ፈንታ ይለያያሉን? ይህ ክፍለ ንባብ እንዴት ይተረጎማል?
✔️መልስ፦ እድልና እድል ፈንታ ልዩነት የላቸውም። ከዚህ ቀድም እድል ፈንታ የለም ያልነው ሥነ ምግባርን መሠረት ባደረገ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሚሠራው ሥራ መሠረትነት ገነትን ይወርሳል ወይም ወደ ሲኦል ይገባል እንጂ በእድል አይገባም ማለታችን ነበር። ድኅነት በእድል ሳይሆን ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን በምንሠራው ሥራ እና በእግዚአብሔር ቸርነት የሚደረግ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ከዚህ ከመጽሐፈ መክብብ እድል ፋንታ ብሎ የገለጸው ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን በሠራነው ሥራ ምክንያት የሚደርስብን ወይም የሚደርሰን ውጤቱ ነው። ለምሳሌ ለኃጥኣን እድል ፋንታቸው ገሀነመ እሳት ናት ስንል በምድር በሠሩት ክፉ ሥራቸው ምክንያት ገሀነም ይገባሉ ማለታችን ነውና።
▶️፮. "ከፀሐይ በታች በሚደከምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድን ነው?" ይላል (መክ.1፥3)። ይህን ጥያቄ መልሼ ልጠይቅ። አንድ ክርስቲያን ከፀሐይ በታች ትርፉ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ከፀሐይ በታች በዚህ ምድር ሳለን የመኖራችን ትልቁ ትርፍ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የሚያበቃ ሥራን መሥራት ነው። በዚህች ምድር መኖርን ለዘለዓለማዊው ሕይወት ዝግጅት ለማድረግ ካልተጠቀምንበት ትርፉ ኪሳራ ነው።
▶️፯. "ደግሞም ከፀሐይ በታች በጻድቅ ስፍራ ኃጥእ በኃጥእም ስፍራ ጻድቅ እንዳለ አየሁ" ይላል (መክ.3፥16)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ በዚህች ምድር በጻድቅ ስፍራ ማለት ጻድቃን በሚኖሩበትና በኖሩበት ቦታ ኃጥኣንም ይኖራሉ ማለት ነው። ኃጥኣን በሚኖሩበት ቦታም ጻድቃን ይኖራሉ ማለት ነው። ይህ የሚሆነው ግን ከፀሐይ በታች በዚህ ምድር ነው እንጂ በመንግሥተ ሰማያት ጻድቃን ብቻ ሲኖሩ፣ በገሀነም ኃጥኣን ብቻ ይኖራሉ።
▶️፰. መክ.1፥3 ላይ "እግዚአብሔር ይደክሙበት ዘንድ ክፉ ድካምን ለሰው ልጆች ሰጥቷልና" ይላል። ከዚህ ላይ 'ክፉ ድካም' የተባለ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ክፉ ድካም የተባለው በዚህ ምድር የምንደክመው ድካም ነው። የእግዚአብሔርን ሕጉን በማፍረሳችን፣ ክፉ ሥራን በመሥራታችን የመጣብን ስለሆነ ክፉ ድካም ብሎታል።
▶️፱. "ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል" ይላል (መክ.5፥3)። ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሰው ቀን ሲሠራ የዋለውን ማታ በሕልሙ የሚናገርበት ጊዜ መኖሩን የሚያመለክት ነው።
▶️፲. "ከሰማይም በታች የተደረገውን ዅሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋኹ። እግዚአብሔር ይደክሙባት ዘንድ ይህችን ለሰው ልጆች የሰጠ ክፉ ጥረት ናት" ይላል (መክ.1፥13)። ክፉ ጥረት የተባለችው ምንድን ናት?
✔️መልስ፦ ክፉ ጥረት ማለት ክፉ ድካም ማለት ነው። ጥረት የሚለው ጣረ ከሚለው አማርኛ የተገኘ ነው። ይኸውም በበደላችን ምክንያት የምንደክመው ድካም ነው። ምሥጢሩ ጥረህ ግረህ ብላ ከሚለው ጋር አንድ ነው።
▶️፲፩. "ጥበብንና እብደትን ሞኝነትንም ዐውቅ ዘንድ ልቤን ሰጠኹ። ይህም ደግሞ ነፋስን እንደ መከተል እንደ ኾነ አስተዋልኹ። በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛልና። ዕውቀትንም የሚጨምር ኀዘንን ይጨምራልና" ይላል (መክ.1፥17-18)። ነፋስን እንደ መከተል ነው ሲል ጥበብን ይጨምራል? በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛልና ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ነፋስን መከተል ከንቱ ድካም ነው። ነፋስን በመከተል የሚገኝ ጥቅምም ስለሌለ ትርፉ ድካም ብቻ ነው። በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛል ማለት ጠቢብ ሲያጠፋ የአዋቂ በዳይ ተብሎ ይፈረድበታል ማለት ነው። ጥበብን ያበዛ ሰው በጥበቡ ካልሠራበት ይጠየቅበታልና ነው። ወዘሰ የአምር ገቢሮታ ለሠናይት ወኢየገብራ ኃጢአተ ትከውኖ እንዲል።
▶️፲፪. "ለሰው ከሚበላና ከሚጠጣ በድካሙም ደስ ከሚለው በቀር የሚሻለው ነገር የለም። ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየኹ" ይላል (መክ.2፥24)። ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሰው ሲበላ፣ ሲጠጣ እና ደክሞ በሚያገኘው ገንዘብ ደስ ይለዋል ማለት ነው። ምግብ መጠጥ ከእግዚአብሔር ይገኛል። ሰው የፈለገ ቢደክም ረድኤተ እግዚአብሔር ካልተጨመረበት ምንም አያገኝምና ነው።
▶️፲፫. "ነገርን ዅሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው። እግዚአብሔርም ከጥንት ዠምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘለዓለምነትን በልቡ ሰጠው" ይላል (መክ.3፥11)። ዘለዓለምነትን በልቡ ሰጠው ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዳያውቅ እግዚአብሔር ለሰው ዘለዓለምነትን በልቡ ሰጠው ማለት ሰው እግዚአብሔርን በባሕርይው ለዘለዓለም አያውቀውም ማለት ነው።
▶️፲፬. "አኹን ያለው በፊት ነበረ። የሚኾነውም በፊት ኾኖ ነበር። እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል" ይላል (መክ.3፥15)። እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል ሲባል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ለሰው ምጽዋትን የሚሰጥን ሰው እግዚአብሔር ክብር በመሥጠት ይሻዋል ማለት ያከብረዋል ማለት ነው።