ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ትለኛለች እንዴ ጭራሽ?
የቱን እጇን😳 እኮ የቱን
ይሄ የሚያንቅ የሚገለውን?
ይሄ የልጆቿን ራስ የሚፎክተውን?
ባዶ ጭንቅላት የሚያደማውን?
እኮ ይሄን እጅ
ይሄ ላንዱ ፍርፍር ላንዱ ጥፍር ሚያጎርሰውን? እኮ ይሄ ሴት ልጇን አንቆ ገድሎ ፍትህ ፍትህ ስትባል አፍ ላይ የምትጭነውን?
ድረሽልን ስትባል አልሰማሁም ለማለት ጆሮዋ ላይ የምታደርገውን?
እኮ ይሄን እጇን እጅ ብላ ትዘረጋለች? ጉድ!
የገዛ ልጆቿን ገድላ ገንዛ ቀብራ ገደሉብኝኮ ብላ የምትጠቁምበትን ይሄን እጅ እጅ ብላ ዘረጋችው? ምን ልታገኝ? በየቱ ግብሯ የቱን ቸሮታውን ፈልጋ?
ምን ልትቀበልበት እጅ አለኝ ብላ ዘረጋችው? ማፈሪያዋን ቁማር አስይዛ ተበላችው እንዴ? ዘንድሮኮ እንኳን ዜጎቿ እሷም ልቧ ሸፍቷል። (እንደሚወራውማ DV ሞልታለች ነው አሉ የሚባለው።) ልጆችሽን ለማን ጥለሽ ሲሏት ሲጀመር እድሌ ጠማማ ነው አይወጣልኝም እንዲሁ ዝምብየ ነው ትላለች አሉ። ድንገት ቢቀናሽስ ሲሏትም "ፈጣሪ አለ የተገባልኝ ቃል ለልጆቼም ይበቃል።" ትላለች ደግሞ።
እግዜሩን ሲርበን በግ መድረሻ ሲጠፋን እረኛ እያረግን ጸሎት አደበላልቀንበት በየት በኩል። ስጠን ብለነው ሊሰጠን ሲሰናዳ ይሄስ ከእኔ ይራቅ እንላለን የጠዋት ጸሎታችን እንኳን መሽቶ አርፍደንም አንደግመው (እሱንም ከጸለይን!) ቡና መሀል "ኧረ ፈጣሪዬ አንዲት ሴት ልጅ ጨምረኝ ባክህ" ያልነውን ሁሉ ቆጥረንኮ ነው ቀን ማታ ለመንኩት ለመንኩት ስንል የምንውለው። ከደረስንበት ደብር ካደረስነው ጸሎት በላይ እንዴት እንዳደረስን የምንናገርበት መንገድ ብዙ ነው። ጠይቄ ነሳኝ ለማለት መጣደፍ ፣ መቸኮል። ለመፍረድ፤ ለመንቀፍ ፤ ለመመዘን ፤ ለመተረክ ፤ ለማፌዝ ፤ ለማጣጣል ስንራወጥ ስንቱን ሳትነው። ስንቶቹን ለቀልዳችን ማሳመሪያ ስንል ፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ለመሳብ ለማስደነቅ ስንል ፣ ይሄ እንዴት መጣለት ለመባል ስንል ስንቶቹን አደናቀፍን? ለስንቱ የመውደቂያ ሰበብ እንቅፋቱን ራሱን ሆንን??
እጆቻችን የጨበጡት ተስፋ ስንዘረጋው እንባ ሆኖ የፈሰሰብን ፣ ከሩቅ ያለምነው ብርሃን የማይደረስበት ጨለማ የሆነብን እኛን....... እኮ እኛን ይዛ እጇን ዘረጋች?
ማንን አቅፈሽበት ብትባልስ ምን ልትል?
ከእዚህ እጅሽ የበሉት ጠገቡልሽ ወይ?
በእዚህ እጅ የተዳሰሱት ተመቻቸው ወይ?
በእዚህ እጅ የተባበሉት ተስማማቸው ወይ ብትባልስ? በእዚህ እጅ መንገድ የተጠቆሙት የት ደረሱ ብትባልስ? ተወው በቃ ትቼዋለሁ ብላ ያን ጥፊም ዳበሳም የሚችለውን 'አድሎኣም' እጇን አትሰበስብም?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ይለኛል እንዴ ይሄም? እኮ ይሄ እጅ? ይሄ እጅም እጅ ሆኖ ሰውን በአምሳሉ የፈጠረ አምላክ ፊት የሚቀርብ መስዋዕት ነው? ያን ሁሉ የሰራ እጅ እንኳን ፈጣሪ ደጅ ሰይጣን ጓሮ ቢገኝ ሰይጣን ራሱ "በስመ አብ" አይልም?
ምን አረገችህ ይሄን ያህል አትበለኝ! እጇን ዘረጋች ስልህኮ ተራራው ተነስቶ ወንዙ መንገድ ስቶ ተነጥፎ አይደለም። ወፎች መስመር ይዘው ዋልያዎች ተሰልፈውም አይደለ። የሀገር እጅኮ የእኛ እጅ ጥርቅም ነው። ይሄን እጅ እርስ በእርስ ለመተያየትስ አንፀየፈውምና ነው? እኮ!
ይሄን እጅ ይዘን አምነን ዘርግተነው አይደል ለእንባችን መታበሻ ፣ ለቁስላችን መሻሪያ ፍለጋ የምናንጋጥጠው። ጉደኛ እጆች ጉደኛ ፍጥረቶች!
ገዳይም ሟችም አቤቱ አቤቱ የሚል ጩኸት እኩል ቢያሰሙስ? የተበደለ ፍትህን ፤ የበደለ ምህረትን እኩል በአንድ እጅ ሲልኩስ? ፍቅርን ስጠን ብሎ ቤተሰብ በበተነ እጅ መለመን የት ሊያደርስ?
መዘርጋቱንኮ ትዘርጋ ግን ትታጠበው። ሲጀመርስ በክፋት ጭቃ ፣ በነገር ደም ተለውሶ እጇ በጥላቻና በበቀል ሞልቷ ትንሽ በረከት እሱንም በእሷ ስራ ሳይሆን በእሱ በፈጣሪ ቸርነት ቢያድላት በምኗ ልትይዘው?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ትለኛለች እንዴ ደሞ? ይሄን እጅ የኔንና ያንቺን እጅ ተማምናኮ ነው የምትዘረጋው። ይታይሽ እንግዲህ በእኔና በአንቺ እጅኮ ነው በረከት የሚጠበቀው...
እኔ እጅ ላይ ያለው ምንድን ነው? ቅናት ምቀኝነት ክፋት ሴሰኝነት አንቺ እጅጋ ያለውስ ቂም ጥላቻ የበላይነት ስሜት ድንቁርና በቀል እና ይሄ እጅ እንደ ንጹህ እንደታጠነ ክቡር እቃ እንደተባረከ ስጦታ እጅ አለኝ ብላ ትዘርጋው?
እኮ ይሄን እጅ!
እኮ የኔን እጅ!
እኮ ያንቺን የአንተን እጅ!
እኮ የእኛን እጅ!
አልቀረብንም!
በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19