✨✨✨በ'ነሱ ቤት
✨✨✨✨✨✨ክፍል ሁለት
✨✨✨የሦስቱን ጓደኛሞች ወሬ በመገረም የሚሰማው አስተናጋጅ ጥጉን ይዞ መቅረቱን ያስተዋለው የስራ ባልደረባው " ሰሚር ኧረ ነቃ በል እዛጋር ከስተመር ገብቷል "ብሎት ሲያልፍ ነው ። ሰሚር በአስተናጋጅነት ብዙ ቦታ ቢረግጥም የተለያዩ ከስተመሮችን ቢያይም ቢያጋጥሙትም ። እንደነ ሰመረ ያለ ወጣት ግን ገጥሞት አያውቅም ። ሲያወሩ ሰው አለ የለም የማይሉ ወሬያቸው፣ ማህበረሰቡ ከለመደው ስርሃት ውጪ መሆኑ ፣አለባበሳቸው የጫማቸው በእጃቸው የሚያሽከረክሯት የመኪና ቁልፋቸው በአጠቃላይ ፅድት ካለ ውጫዊ ውበታቸው ያለገደብ የሚወጣ ቃላቸው ልክ አለመሆን ተሰምቶት ፡ እነሱ በገቡ ቁጥር በነሱ ዙሪያ ፈዞ መቅረቱን ተላምዷል ፡ከነሱ የሚወደው የሚሰጡት ቲፕ ብዛቱ ዋው ,,,,,,
ሰሚር ባልደረባው ከጠቆመበት ቦታ ሊሄድ ሲዘጋጅ ጌታ ነህ ጠራው ....
"አቤት ምን ይምጣ "አለው እጁን ወደዋላ አድርጎ በክብር ። ጌታነህ ዝም ብሎ ወሬውን እያወራ አስጠበቀው ሰሚር በትህግስት ጠበቀው
"እስኪ ልጁን አታቁመው ምን ፈልገህ ነው የጠራኽው "አለው ሰመረ የሰሚር ሁኔታ ትንሽ ነካ አርጎት
"እእ እ አስተናጋጅ ስምህ ማነው ?"አለው ጓደኞቹ እኩል ሳቁ
"እናንተ አታስካኩ "አለ እና ወደሰሚር መለስ ብሎ
"ስምህን መጠየቄ ክፋት አለው እንዴ "
"ኧረ የለውም ፡ስሜ ሰሚር ጅላሉ ሚፍተሃ"ይባላል
"እ ሰሚር ብቻ ይበቃል ከዋላ ያሉትን ተዋቸው "አለ ጌታነህ ኮስተር ብሎ። ጓደኞቹ አኮሰታተሩ በቀልድ የታጀበ መሆኑን ስለሚያውቁ ተሳሳቁ
"ያው የዋላው ከሌለ የለም የፊቱ ብለን ነው "አለ ሰሚር እንደመቀለድ ብሎ
"እ እሱ መፈክር ላይ ነው !አሁን እሱን ተወውና ማነህ ሰሚር እዛ ፊት ለፊት ያለችው ኮስሞ ቤት ትታይሃለች "
አለው። እነሱ ከተቀመጡበት ሬስቶራንት አስባልት ተሻግሮ ያለች አነስተኛ ኮስሞ እየጠቆመው
"እ አዎ ትታየኛለች ሳሪና ኮስሞቲክስ አይደል "አለው
"አዎ እዛ ሱቅ በር ላይ ለተቀመጠችው ሴት ይሄን ስጣት "ብሎ ስልክ ቁጥሩን የያዘ ካርድ ሰጠው ሰሚር ትንሽ ግር አለው ስራዬ መልህክት ማመላለስ አይደለም ኤጭ አለ በሆዱ
"እ ስለላኩ ቅር አይልህም አይደል "
"እሺ ያው ማናጀሩ ካየ የት ነህ እንዳይል ነው እንጂ..."
"ችግር የለም ለሚፈጠርብህ ነገር ይሄም ስራነው ብሎ ካስቀየመህማ ከኔጋር ነው ፀቡ "አለው
"እሺ እሰጣታለው "
"ጎበዝ ልጅቷ ስለተመቸችኝ ነው እና መደወልሽን እንዳትረሺ ከቻልሽ አሁን ደውዩ በላት "አለው
ሰመረና እንየው እየተያዩ መሳቅ ጀመሩ
"ምንድነው የሚያስቃቹ !"
"አይ ከመቼው እዛማዶ አይተህ ነው እንዴዴዴዴዴ😀"
"ቆይቷል ካየዋት ሁሌም ፊትለፊት የምቀመጠው ለምን ይመስልሃል የሞዴሏን እንቅስቃሴ በትኩረት ተመልክቼ ተሳክቶልሻል ልላት ነው እና ዛሬ ትኬት ተቆርጦላታል ዌል ካም ቱ ጌታነህ ተብላለች "አለ ወፈር ያለ ሰውነቱን ወደዋላ እየለጠጠ
"በጣም ጥሩ ግን ኤልሳ ምን ሆናብህ ነው ገና ሳምንት ሳይሞላቹ "አለ ሰመረ
"ኤልሳ ባክህ ስሟም አይመቸኝም በዛላይ አንድ ቦታ መቸከል መዛግ ነው ኪኪኪኪኪ አይመስልህም "
"ልክ ነህ ብሮ ይመችህ እዛጋር ያየኽውን አይተነው አሁን ገብቶኛል የሆነ ቦታላይ የተከማቸ ሀብት አላት እሱን ልትቀራመት ነው ካካካካካካ ኧረ ምኑን ሰጣት ኧረምኑን ሰጣት ኪኪኪኪ"እንየው እየሳቀም እየዘፈነም ነበር
"የተረገምክ እኔ ኮ ከዚጋር ቁንጅናዋ ጎልቶ አይታይ እላለው ።ለካ የጎላ አይተ ነው "ብሎ ሰመረ አስባልቱን ተሻግሮ ለመሄድ የሚጣደፈውን ሰሚርን አየው ። ሰሚር መኪኖቹ ውር ውር ሲሉ እንደመቆም ብሎ አሳለፈ ከላይ አንዲት ገና አስራ ስድስት አመት መግቢያው ላይ የሆነች ልጅ መጥታ አጠገቡ ቆመች ለመሻገር ፈልጋ መኪኖቹ ማቆሚያም የላቸው ልጅቷ በጣም የተጣደፈች ትመስላለች አንዱን መኪና እንዳሳለፈች ለመሻገር ስትፈጥን ሰሚር ጮሆ ከመኪናው መንጭቆ አወጣት ልጅቷ ደነገጠች ሰሚር ተቆጣት ከስር ጫማዋ ግንጥል ማለቱን ስታይ ልጅቷ ተሳቀቀች ሁኔታዋ አንድ ቀጠሮ እንዳለበት ሰው ነው ባላት መጠን መልበሷ ያስታውቃል ያደረገችው ጫማ የጓደኛዋ ነው ትንሽ ተረከዝ አለው ይሄንን ጫማ እንድታውሳት መለመኗን ስታስታውስ ዕንባ በአይኗ ላይ ወረዛ ጫማዋን አንስታ ወደዋላ ተመለሰች ፡ሰሚር መልህክቱን አድርሶ ሲመለስ ወደ ዋላ ተመልሳ ጫማዋን በአንድ እጇ እንደያዘች ያቀረቀረችውን ልጅ ተጠጋትና ። "እናት ምነው ጫማው ነው ያሳዘነሽ ሞተሽ እኮ ነበር "አላት
"ብሞት ይሻለኛል ከዚ ሁሉ "አለች
"እንዴ ይሄን ያህል ጫማ እኮ የሚገዛ ነገር ነው አንቺ ግን በሚሊዮኖች አትገኝም "አላት ለማፅናናት
"አሁን ምን ላደርግ ነው የቀጠሮ ሰአት እያለፈብኝ ነው"
"አይዞሽ ትንሽ ሄድ ብለሽ ጫማ የሚሠሩ ሰዎች ፈልጊ "አላት እንዲ እያወሩ ሳለ ሰመረ መጥቶ ተቀላቀላቸው
ሁኔታሁን ሁሉ ከርቀት እየተመለከቱ ነበር እና በዚች ልጅ ሁኔታ የአለባበስ ስርሃት እየተሳለቁ ነበር ይባስ ብሎ ጨማዋ ሲገነጠል የሚገርም ትርሂት ብለው ሲስቁ ነበር ።ሰመረ እስኪ ላናግራት ብሎ እያሾፈ ነበር የመጣው ።
"ስሚ ሚጣ ምንድነው እሱ "አለ ሰመረ በማላገጥ
"ሚጣ አይደለም ስሜ አብ ላካት ነው ስሜ"አለች በብስጭት እሷ አድጌ አለው ከዚ በዋላ በብቸኝነት ያሳደገችኝን ጉሊት ቸርቻሪ እናቴን አሳርፋታለው ብላ የተነሳች ናት ፡ ዛሬም እራስሽን ጠብቀሽ ፅድት ብለሽ ነይ አንድ ቡቲክ ቤት አስቀጥርሻለው ያላትን በፌስቡክ የምታውቀውን ሰው ለማግኘት ነው ጫማ ተውሳ ያለቻትን ጉርድ ቀሚስ ማታ በድንብ አጥባ ከጥቁር ቀሚስ ጋር ነጣያለቲሸርት ያስፈልጋል ስላለቻት ጓደኛዋ እሱንም ከሷ ወስዳ ነው እንግዲ ወደ ቀጠሮዋ የተጣደፈችው ግን እየረፈደባት ነው በዚ ጫማ የተነሳ ስለዚ ሆድ ብሷታል
ሰመረ ከጠይም ትንሽዬ ፊቷ የሚፈልቀውን ውበት ለአፍታምቢሆን ልብ ብሏል ግን ይበልጥ ትኩረቱን የሳበው ጫማው ነው በፍፁም ከሷጋር አይሄድም እንደተውሶ ጫማም ልኳ አይደለም ለሷ ግን ብርቋ ነው
"እኔ ሰመረ እባላለው አብላካት ጫማሽ ተሰብሯል ስለዚ ሌላ መግዛት ሊኖርብሽ ነው "አለ ሰመረ ድንገት አንዳች አይል ማንነቱን የተቆጣጠረው መሰለ
"ሌላ ጫማ መግዛት እሱን ማድረግ አልችልም "አለች የያዘችውን የጓደኛዋን ጫማ እያየች ሰመረ መሳቅ ፈለገ ይሄ ጫማ የተጣለ ነው የሚመስለው ስለእህቱ ቬሮኒካ አሰበ የጫማዎቿ መደርደሪያ ተብሎ አንድ ክፍል ሙሉ ተለቆላታል እዛ መደርደሪያ ላይ ደሞ ሁሉም ማለት ይቻላል ከውጪ የመጡ ብራንድ ያላቸው ጫማዎች ናቸው ።እዚጋር ደሞ የተጣለ ጫማ ይዛ ታለቃቅሳለች ለሰመረ ይሄ አልተዋጠለትም ።እየደበረው ጫማዋን ከእጇ ላይ ነጥቆ ወረወረው
"ወይኔ ምን ሆነህ ነው "ብላ ጮኽች
"በቃ አየሽ አንቺን እዚጋር አስቁሞ ከሚያናድድሽ ቢርቅ ይሻላል ብዬ ነው በቃ አሁን የለም አየሽ "አላት እየሳቀ እሱን ትታ ሌላኛውን ጫማ አውልቃ በእጇ ይዛ የወረወረባትን ጫማ ላታመጣ ስትንቀሳቀስ ።ሌላኛውንም ተቀብሎ ወረወረው ።ጓደኞቹ ባሉበት ሆነው ዛሬደሞ ምን እየሰራ ነው ብለው ያሽካካሉ ።ሰሚር የልጅቷን ሁኔታ ሲያይ ችግርን ጠንቅቆ ያውቀዋላና እህቱን አስቦ ውስጡ አዘነ ፡ የሱ ዘይነብ የሆነቦታላይ ተቸግራ ልክ እንዲ በችግሯ ስትሸማቀቅ ድንገት ታስቦት አይኑ ዕንባ አቆረ ........
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19