በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Цитаты


እንኳን ወደበእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም በደህና መጡ!
═══════ ══ ═══════

➛በዚ ቻናል ላይ ድንቅ ድንቅ ስራዎች ይቀረባሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


➛➛የምንችለውን ወይንስ የሚገባንን ➛➛

እጅግ አሰደናቂ እያታ ናት አድሚጧት!
➮ ከ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ኢዮብ ዮናስ ክሽን አርጎ አቅርቦታል!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ ለጌታችንና ለመዳሃኒታችን እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት የከተራ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

መልካም በዓል....


ህልምሽን አጫውቺኝ የተስተካከለ.pdf
54.9Мб
┈┈┈◦◎●◉ህልምሽን አጫውቺኝ◉●◎◦┈┈
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


┈┈┈◦◎●◉የገና ሥጦታ◉●◎◦┈┈

ከሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
#በኢዮብ_ዮናስ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስየልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

መልካም በዓል❤️
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​ዘመም ይላል እንጂ!

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ።

.
የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት ጉድጓድ ተምሶለት ሰብእና ሲቀበር፤ በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር።
.
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ

ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፤ አያስመኝም ነበር።
.
አዎ!
ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል

በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል።
ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት
ሽረት ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ፤ ተገርስሶ አይወድቅም።

➛ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛➛ያበደ ምሽት➛➛➛
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➮ እጅግ በጣም ገራሚ ወግ ናት አድምጧት!

ከበእውቀቱ ስዩም

➮አጣፍጦና አሳምሮ ያቀረበው እራሱ በእውቀቱ ስዩም ነው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛➛ዘፈን እና ዘፋኞች➛➛➛
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➮ እጅግ በጣም ጣፋጫ ወግ ናት አድምጧት!

ከበእውቀቱ ስዩም

➮አጣፍጦና አሳምሮ ያቀረበው እራሱ በእውቀቱ ስዩም ነው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​የጥቅምት መስክ ነኝ !!

ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ

በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን፣ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ

ካንጀት ይሁን ካንገት ፣ እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ ፣መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት፣አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ

ከላይ ተሰውሮ ፣ ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ፣ አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል፣ስሩ ከተማሰ!!

የጥቅምት መስክ ነኝ ፣አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው፣ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም፣እኔው ነኝ የማውቀው።


➲ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​በምድር ላይ ለአንተ ካንተ የባሰ ጠላት ያለ እንዳይመሰልህ። ራስህን ካላሸነፍክ አሸናፊ መሆን አትችልም። አንዳንድ ጊዜ የምታደርገው ነገር ራስህን እያወደመ ካንተ በተቃራኒ ሆኖ ያሰቃየሃል። አንዳንድ ጊዜ ራስህን ራስህ በገነባኽው
እስር ቤት ታሳሪ ታደርገዋለህ። ከዛም ጠባቂው አንተ ተጠባቂውም አንተ ትሆናለህ። አንድ አንድ ጊዜ
የሚያበሽቅህ፣ የሚያስፈራራ፣ የሚያሸማቅቅህ ድምጽ ከራስህ ወደራስ
ይወረወራል። አትችልም፣ አታደርግም፣ ፈሪ ነህ ፣ ተስጦ የለህም እያለህ ከሰው ሁሉ የበታች ያደርግሃል።
ይህን
በውስጥህ ያለውን ሃይል ለማሸነፍ ለራስህ በራስህ ውስጥ ጠበቃ ቁምለት። ከራስህ ጋር ታገል። ራስህን ከራስህ ጋር
አስማማው እና አለም ሁሉ ከአንተ ጋር
ለመስማማት አጁን ይዘረጋል።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​꧁​​❷⓿❶7 ~~❷⓿❶7꧂

②⓪①7🌻እንኳን አደረሳቹ 🌻

አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና፤ የፍቅርና፤ የብልፀግና እንዲሁም የእንድነትናየማስተዋል ፤የመቻቻል፤ችግራችንን፤ በጋር የምንቀርፍበት፤ ብሩህ ፤ተስፍ ፤የምንስንቅበት፤ ዓመት ያድርግልን።

ከበእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም አዘጋጅ ክፍል!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦2017✦
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢

@bewketuseyum~ @bewketuseyum
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟




​​በእያንዳንዱ የምንጓዝበት መንገድ ፈጣሪ አለ ስንቆም ስንተኛ ስንነሳ ሁሉንም እንቅስቃሴያችንን የሚቆጣጠርልን እርሱ ነው ታድያ ለምንድነው የምንፈራው? ለምንድነው ብቻዬን ነኝ የምንለው ለምንድነው ደጋፊ ያጣን እንደሆንን የምናስበው ?

በምታደርገው ነገር በሙሉ ማንም ሰው ባይደግፍህ ነገርግን ፈጣሪ ከጎንህ እንደሆነ ካመንክ ከሁሉ በላይ የሆነው ካንተ ጋር ነውና በፍፁም አትፍራ ! ✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​ልጅ ሆኜ እናቴ ሽንኩርት ስትከትፍ አብሬያት መሆን እወድ ነበር። አንዳንዴ ታዲያ እኔም እንደሷ ለመላጥ አስቤ ሳላውቀው ሽንኩርቱን ልጬ ልጬ የመጨረሻዋ ላይ ስደርስ፣ ልገልጸው የማልችል የተለየ ደስታ ይሰማኝና ውጤቱን ይዤ ወደናቴ እሮጥ ነበር።

እሷ ግን እንደጥፋት ስለምትቆጥረው ከደረሰችብኝ ትከለክለኝ ነበር፤ እጄን ላመል ጥብስ አድርጋ። እሷ ያስተማረችኝ ትክክለኛው ሙያ ደረቁን የውጭ ሽፋን ልጦ የቀረውን መክተፍ ነው።

አሁን አሁን ከሽንኩርት ይልቅ ሰውን ልጦ እስከውስጡ ማየት የተለየ ደስታንና መደነቅን ይፈጥርብኛል። ሳስበው ሰውም እንደሽንኩርት ሳይሆን አይቀርም።

በተለይ የኛ ሕዝብ ተልጦ ውስጡ ያልታየ ምስጢር ነው፣ ነገር ግን ሁሌም ከላይ ከላዩ ብቻ ተልጦ እየተከተፈ በሕይወት ድስት ውስጥ የሚጨመር።

የፈረንጅ ሽንኩርት ሲልጡት ቀላልና ዐይንንም እንደሚያቃጥለው እንዳበሻው ሽንኩርት አለመሆኑን ሞክሬ አይቼዋለሁ። የተሻለ ወጥ የሚያሰማው ግን ያበሻው ሽንኩርት ነው ይባላል።

ቃሪያውም፣ ሽንኩርቱም፣ ሰዉም ለምን ያበሻው እንደሚያቃጥል አላውቅም። እስከመሀሉ ልጠን መመርመሩ ምናልባት ምስጢሩን ያሳውቀን ይሆን?

ከዶ/ር ምህረት ደበበ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት እያደረገ ነው 🤩

ቴሌግራም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገር መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል።

1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ ⭐️⭐️

ስራውን ለመጀመር ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ስታርት በሉት 👇🏻👇🏻

https://t.me/major/start?startapp=709140036

https://t.me/major/start?startapp=709140036


ወንድ በራሱ መንገድ.pdf
1.2Мб
✦ወንድ በራሱ መንገድ ✦በpdf ✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢
@Daniel_bewketu ~ @Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት

ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር

ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት

ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል።


ከኤፍሬም ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Репост из: በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​ወይ እንጀራ ወይ ሞት

ታሪክ ፀሀፊዎች “ዘመነ መሳፍንት “ ብለው በሚጠሩት ፤ እኔ ደሞ “ ዘመነ የጁ “ በምለው ዘመን ውስጥ አንዲት አረሆ የሚከተለውን ግጥም አንጎራጉራ ነበር፤
"እሄዳለሁ ሜጫ እሄዳለሁ ዳሞት
ሳላገኝ አልቀርም ወይ እንጀራ ወይ ሞት "
በነገራችን ላይ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ባላገሮችንና ጌቶችን በፈጠራ በማዝናናት
የሚተዳደሩ የግጥምና የዜማ ባለፀጋ ሴቶች ና አረሆ ተብለው ይጠሩ ነበር::

ያኔ ካንዱ አውራጃ ወደ አንዱ አውራጃ
የሚኬደው በባዶ እግር፤ ግፋ ቢልም በበቅሎ ነው ! ሲመሽ በሸማ ድንኩዋን ስር ወይም ዛፍ ስር ይታደራል ! አባይን መሻገርማ አይጣል ነበር ፤ ካዞ ብታመልጥ ሽፍታ አይምርህም ! አቶ ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት አባይ “ ብዙ ሞቶች ተሰብስበው የሚገኙበት ቦታ” ነበር፤

በዚያ ላይ በየቦታው መሳፍንቱ ጎራ ለይተው በየቦታው ይከሳከሳሉ ፤ በግርግር መሀል በራሪ ጥይት መሞት መደፈርና መጠለፍ ሊያጋጥም ይችላል!
የጠቀስኩት ግጥም ዝምብሎ የድሮ ግጥም አይደለም! ዛሬም የብዙሀኑን የኢትዮጵያዊ ህይወት የሚገልፅ ይመስለኛል ! “ሜጫንና ዳሞትን “ በሌሎች ቦታዎች ተክቶ ማንበብ ብቻ ነው እሚጠበቅብን ! ከጥቂት አመታት በፊት በሰደት ወጥቶ መሞትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው አረብ አገር ወይም ደቡብ አፍሪካ ነበር ፤ ብዙ ሰው ወቅቱን ያልጠበቀ ሞት ሸሽቶ ነበር ወደ አሜሪካ የሚሰደደው ሞት አሜሪካ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረበ ብርቅየ አውሬ ሆኖ ቆይቷል ፤ ዘንድሮ ይሄ ቀርቷል ! ከሁለት ቀናት በፊት ባንድ ቀን ብቻ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ሰዎች እንደ ጥቢ ቅጠል ረግፈዋል! አሜሪካ እንጀራ አምሮት ለመጣ ስደተኛ ሞትን በሰፌድ ማቅረብ ጀምራለች::

ይህ ብቻ አይደለም ! አሜሪካኖች ምርጫ ላይ ናቸው! የትራምፕ ደጋፊዎች እንደ ጌታቸው መጋጣነታቸውን -ወይም ባዲስባ አራዳ አማርኛ " ሰገጤነታቸውን " መደበቅ እሚችሉ አይደሉም ! ሰውየውም ሽንፈቴን በፀጋ አልቀበልም ብሏል ! ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሊላመጡ
ይችላሉ! እዚህ አገር ድብድቡ ከተጀመረ እንደ ሸገር በድንጊያ ወይም እንደ
ፍልስጤም በወንጭፍ አይደለም! ሁሉም " ነጣ ዘለግ ያለ ስናይፐር ታጣቂ" ነው!
አሁን ሳስበው መሞቴ ካልቀረ እዛው ባገር በቀል ዱላ መሞት ይሻለኝ ነበር፤
ደግነቱ በሜክስኮ ድንበር ግንብ ታጥሮ አለማለቁ ጠቀመኝ! የፈራሁት ከደረሰ፤ በቅርቡ “ የበውቄ ኩብለላ-ከማንኩሳ እከጉዋታማላ “ የሚል ማስታወሻ ጠብቁ፤

➮ በእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛ይድረስ ላብሮ አደጌ➛➛

●●◦ግጥም በጃዝ◦●●

✰አቅራቢ፦አበባው መላኩ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


የዘር ማጥፋት ዳርዳርታ ስም ማጥፋት ነው።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━

እጅግ በጣም ገራሚ እና አስተማር ወግ ናት አድምጧት!

➮ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟

Показано 20 последних публикаций.