Day 9
የዳዊት ቤት ሰዎች ኹሉ ወደ ቤተልሔም ስለተጓዙ ቤተልሔም የተሠኘችው አነስተኛ ከተማ የነበሯት የእንግዳ ማረፍያ ስፍራዎች በሙሉ በእንግዶች ተይዘው ነበር፡፡ ለትንሽ ጊዜ እንኳ ማረፊያ የሚኾን ስፍራ አልነበረም፡፡ ማርያም ልጇን ልትወልድ የምትችልበት ብቸኛ ስፍራ የከብቶች በረት ነበር፡፡ በከተማዪቱ ውስጥ ለታላቁ ንጉሥ፣ ለዓለም መድኀኒት መወለጃ የሚኾን ስፍራ ጠፋ።
ዛሬስ?
ሰው ለኾነው የእግዚአብሔር ልጅ፦ ለርሱ የሚኾን ስፍራ አላችሁን? ኀጢአታችኹን ኹሉ ይቅር ማለት ለሚችለው ለመድኀኔ ዓለም የሚኾን ቦታ አላችሁን? ከአስከፊ ጉድጓድ አዘቅትና ረግረግ ማጥ ውስጥ ማውጣት ለሚችለው የዓለም ጌታ፥ ለርሱ የሚኾን ስፍራ አላችሁን? አንዴ ከመጣ ጥሏችሁ ለማይኼደው ይልቁን ልባችሁን በሰማያዊ ደስታ ለሚሞላትና እስከ ፍጻሜው ዐብሯችሁ ለሚዘልቀው አፍቃሪ አምላክ የሚኾን ስፍራ አላችሁን?
ወንድሜና እኅቴ ሆይ ለንጉሡ ኤየሱስ የሚኾን ስፍራ በልባችሁ ውስጥ ካለ ዛሬ በነፍሳችሁ ውስጥ እንዲወለድ
ፍቀዱለት፡፡ “ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ ፤ በምድረበዳ በፈተና ቀን እንዳደረጋችሁት ፤ ልባችሁን አታደንድኑ” (ዕብራውያን 3፥7-8)፤ “ዕንኾ፤ ትክክለኛው ሰዓት አኹን ነው የመዳንም ቀን አኹን ነው” (2 ቆሮንቶስ 6፥2)
በልባችሁ በረት እንዲወለድ ለኢየሱስ ስፍራ ስጡት! አሁኑኑ ለኢየሱስ ስፍራ ስጡት!
ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!
#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ
Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest