የተከዳው መሲሕ:የኢየሱስ የቅርብ ተከታይ ከነበሩት ከአሥራ ሁለቱ አንዱ አስቆሮቱ ይሁዳ ፣ ጌታውን በሠላሳ ብር አሳልፎ ሊሰጠው መረጠ። የኢየሱስን ትምህርቶች ሲማር የከረመ ፣ ተአምር አድራጊነቱን ያየ እና በርግጥ ይህ መሲሕ የእግዚያብሔር ልጅ መሆኑን የመመልከት ዕድል የነበረዉ ቢሆንም በስግብግብነት ኢየሱስን ሊገድሉት ለሚፈልጉት አሳልፎ ሊሰጥው መረጠ። ይህ ታሪክ ብዙዎቻችን የሚያጋጥመንን እውነታ ያንፀባርቃል።
የይሁዳ ድርጊት ወደ ኢየሱስ ቀርበው የነበሩ ሰዎች እንኳ ሊወድቁ እንደሚችሉ ያስታውሰናል። ይህ የሰው ልጅ የወደቀውን ተፈጥሮ ያሳያል። ሁላችንም እምነታችንን የምንክድበት ወይም በፍላጎታችን እና በህሊናችን መካከል በሚደረግ ትግል፣ ከታማኝነት ይልቅ የራስን ጥቅም የመምረጥ ፈተና ውስጥ የምንገባባቸው ጊዜያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
ይሁዳ ተስፋ መቁረጥን መርጦ በመጨረሻ የራሱን ሕይወት ቢያጠፋም ፣ ተስፋ ለሌላቸው እና ከአምላክ ሩቅ ነን ብለው ለሚያስቡ ሁሉ በንስሃ ቢመለሱ የእግዚአብሔር የይቅርታ ደጅ በልጁ በኢየሱስ በኩል ተከፍቷል። ስለሆነም በሰው ፍጹምነት ላይ ሳይሆን በክርስቶስ መስዋዕትነት ላይ የተመሰረተውን የዘላለም ድነት ስጦታ በዕምነት አሁኑኑ ይቀበሉ።
እርሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ እናንተስ ምን ትሰጡኛላችሁ? አላቸው። እነርሱም ሠላሳ ጥሬ ብር ቈጥረው ሰጡት።ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይሁዳ፣ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።(ማቴ 26:15-16)
#ያ_መሲሕ
#እነሆ_ያመሲሕ
#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ