የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ500 አባዋራዎች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ፡፡
***************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ በጅግጅጋ፣ ሐረር እና ሀሮማያ ከተሞች ለሚገኙና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 500 አባዋራዎች ከሰሞኑ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናውኗል፡፡
ባንኩ በሀሮማያ ከተማ ለ200፣ በሐረር ከተማ ለ150 እንዲሁም በጅግጅጋ ከተማ ለ150 ሰዎች በአጠቃላይ ለ500 አባዋራዎች ነው ማዕድ ያጋራው፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸውን ወገኖች በመለየት የሶስቱም ከተማ አስተዳደሮች በተሳተፉበት በዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ለእያንዳንዱ አባዋራ የዱቄትና ዘይት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተከታታይ ዓመታት በተለያዩ አከባቢዎች ዓመት በዓላትንና ልዩ ልዩ ሁነቶችን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሮችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ይመኛል፡፡