በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው ከሚገኙ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
***************
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች እና የነቀምቴ ዲስትሪክት አመራሮች በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን አወያይተዋል ።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ደንበኞች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች፣ የብድር አሠጣጥ፣ አዳዲስ ቅርንጫፎች በሚከፈቱበት ሁኔታ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ናስር ሱልጣን፣ የነቀምቴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ መሠረት አለማየሁ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሸሪዓ መማክርት ኮሚቴ አባል ዶር. መሀመድ ዘይን ለጥያቄዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ባንኩ የሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ መርሆዎችን የተከተለ ስለመሆኑ በማብራሪያ ወቅት የተገለፀ ሲሆን፣ የብድር አገልግሎትን ጨምሮ ደንበኞች ያነሷቸው ሌሎች ጉዳዮች በባንኩ አሠራር መሠረት ምላሽ እንደሚያገኙ ተብራርቷል፡፡
በወርቅ ማዕድን በበለፀገው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህብረተሰቡ የባንክ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ባንኩ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እንዲሁ በምላሹ ተነስቷል፡፡
የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በቅርንጫፎች እና በደንበኞች የሥራ ቦታ በመገኘት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ በቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።