የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፋስት ፔይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
• የፋስት ፔይ ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል፡፡
******************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ለመላክ አገልግሎት ከሚሰጥባቸው አማራጮች መካከል አንዱ የሆነው የፋስት ፔይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡
በኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የበለፀገው ይህ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ከውጭ ሀገራት በማንኛውም ቦታ እና ሰዓት በፍጥነት በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺ ዶላር ወደ ተጠቃሚ ሂሳብ በነፃ መላክ የሚያስችል እንደሆነ የፋስት ፔይ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ተስፋዬ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመርቻንት እና ኤጀንት ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ብሌን ኃ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞች ቀላል እና ፈጣን ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ አማራጭ መንገዶችን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የፋስት ፔይ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል መለስ በበኩላቸው ከግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መሥራታቸው ባንኩ ካለው ረዥም ልምድ እና የደንበኛ ብዛት አንፃር ስኬታማ ሥራ መሥራት እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡: