የሲቢኢ ብር ፕላስ ገና ባዛር በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከፈተ::
************
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስያሜ ስፖንሰርነት የተዘጋጀው የሲቢኢ ብር ፕላስ የገና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተመርቆ ለህብረተሰቡ ክፍት ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካስተመር ኤክስፔሪያንስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ባዛሩ በይፋ መከፈቱን አብስረዋል፡፡
አቶ ኃይለየሱስ በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ባዛሩ ባንኩ እጅግ አዘምኖ አገልግሎት ላይ ባዋለው የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ መሰየሙን ገልፀው፣ የባዛሩን የመግቢያ ትኬት ከመቁረጥ ጀምሮ ደንበኞች በባዛሩ በሚያደርጉት ግብይት ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልጋቸው መተግበሪያውን በመጠቀም ያለስጋት የተቀላጠፈ የክፍያ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
በርካታ ጎብኝዎችን እንደሚያስተናግድ በሚጠበቀው እና እስከ ገና ዋዜማ ድረስ በሚቆየው የሲቢኢ ብር ፕላስ ገና ባዛር ከ400 በላይ የንግድ ድርጅቶችና እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡