Репост из: 4-3-3 FAST SPORT™
የጥንቃቄ መልእክት!
ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አልተሰጠም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አለመስጠቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።
ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።
©4_3_3 Fast sport™
♨️ ♦️ @Fast_Sport4_3_3