ፀጥታ ነጋሢ
ይኼ አብዛኛው የምንኖርበት ዓለም ፀጥታ ነው ያልተነገረለት ነው ሆሄ ፣ ቃል ፣ አንቀፅ ፣ ምዕራፎች ፣ ቅዳሴና ዘፈን ፣ እንጉርጉሮና ምንትስ አልተነዳበትም፡፡ የሚባል ምድር ላይ ከተሰሩና ከተደረጉ ከታሰቡና ከታለሙ ነገሮች የተመዘገበው ስንቱ ነው ? የአዳም የመጀመሪያ ሳቁ ተመዝግቧል? የመጀመሪያው የአዳም ወይ የሔዋን እንጉርጉሮ ይታወሳል? የሐጢያት መጀመሪያ የተባለችው በለስ የተበላችበትን ጊዜ ሰዓትና ደቂቃ የሚያውቅ አለ?...ያ ይሄ ፀጥ ያለ ህዋ ነው ሕዋው ድንቁርና ነው የታቀደም ያልታቀደም ….እህቴ ሆይ ሐሙስ በተባለ ቀን ዕድሜሽ ሁለት ወር እያለ እናትሽ ጡጦ ስትነጥቅሽ ምን እንዳልሽ አንቺም እናትሽም ትዝ ይላችኋልን?....ታላቁ አብዮት ይዘነጉታል እንጂ መርሳትን የመቀናቀን ነው ታላቁ አብዮት ይናቃል እንጂ ሰፊ አባባሎችን አጠቃላይ መደምደሚያዎችን ዘንግቶ ወደ ረቂቆቹ መውረድ ይሆን? ጀግንነት ትንሽ የመሰሉ ነገሮችን የማስታወስ የመርሳትንም ተራራ ማፍረስ ይሆን? ያን ያን ታሪክ ማድረግ ይሆን አዋቂነት?...
ከአዳም ረታ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ መጽሐፍ የተወሰደ