ህዳር ሲታጠን
አፍሪካን የጎዳው ከባዱ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በአገራችን ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 ቀን 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየ ነበረ ፤በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑ ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ጠራው :: ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት፤ ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጓል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡
በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ በቀኑ የጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው ፡፡
© ይድነቃቸው ከበደ