🌹እንኳን ለኅዳር ጽዮን ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!🌹
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።እንዲሁም አክሱም ጽዮን የእመቤታችን ጽላት የገባችበት ዓመታዊ ታላቅ በዓል ነው፤ በዚህች ዕለት ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት በተአምራት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኘች።
አሜን!
┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄
📖 @demesetewahedo

ገናናዋ ድንግል ሆይ! ከታላቅነት ሁሉ በላይ አንቺ ታላቅ ነሽ ፤ የእግዚአብሔር ቃል መኖሪያ የሆንሽው ሆይ! በታላቅነት የሚተካከልሽ ማን ነው? ድንግል ሆይ! ከፍጥረታት ሁሉ ከየትኛው ፍጥረት ጋር አንቺን አወዳድርሻለሁ? በወርቅ ፈንታ በንጽሕና የተለበጥሽ የ ቃል ኪዳኗ ታቦት ሆይ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ! እውነተኛው መና የተገኘበትን የወርቅ መሶብ የያዘችው ታቦት አንቺ ነሽ! ይኽውም መለኮት የተዋሐደው የአንቺ ሥጋ ነው!"የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ክብርት እመቤታችን ጽዮን ማርያም ከበዓሏ ረድኤት በረከት ትክፈለን፤ የዓሥራትን ሀገሯን ቅድስት ኢትዮጵያን ትጠብቅልን ሰላም ፍቅር ታድርግልን።
📖 ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
አሜን!
┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄
📖 @demesetewahedo
┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄