ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ በከዋክብት ሠማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።
ትርጓሜእንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ፥
እንዳንተ ከቶ መሐሪ ማነው? ከኖኅ ጋር ቃልኪዳንን ገባህ ፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ከኖኅ ጋር ቃልኪዳንን ገባህ ለእስራኤል ልጆች መናን አወረድህ፤
እንዳንተ ከቶ መሐሪ ማነው? ለእስራኤል ልጆች መናን አወረድህ ምድርንም በአበቦች አስጌጥህ፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ምድርንም በአበቦች አስጌጥህ ምድረ በዳውንም ከቅዱሳንህ ጋር አስዋብህ፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ጉንጩ የወጣት ዋልያ፤ ጉሮሮው የሚጣፍጥ፤ መልኩም የወይጠል (ድኩላ) ነው፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ሰማይና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤ ፀሐይና ጨረቃንም ያስማማህ፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ሰማይን በከዋክብት የጋረድህ ምድርንም በአበቦች ያስገጥህ፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ሰንበትን ቀደሳት፣ አከበራት ከዕለታት ኹሉም ከፍ ከፍ አደረጋት፤
እንዳንተ መሐሪ ከቶ ማነው? ኹሉም አንተን ተስፋ ያደርጋል።┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄
📖
@demesetewahedo┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄