🤔እናንተ ኦርቶዶክሶች?
🤔እናንተ ኦርቶዶክሶች ግን ቆይ እርሱን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት አርጋችሁ እንደው ምን ብላችሁ ነው ምታመልኩት
😊እኛማኢየሱስ ክርስቶስን እንዲህ እናምናለን እንታመንማለን
👉እርሱ የአለም ብርሀን ነው ዮሐ ፰፡፲፪
👉እርሱ ሕይወታችን እውነታችንና መንገዳችን ነው ዮሐ ፲፬፡፮
👉እርሱ ሰላማችን ነው ዮሐ ፲፬፡፳፯
👉እርሱ ትንሳኤያችን ነው ዮሐ ፲፩፡፳፭
👉እርሱ የህወታችን ውሀ ነው ዮሐ ፯፡፴፯
👉እርሱ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራችን ነው ዮሐ ፮፡፶፩
👉እርሱ የጽድቅ በራችን ነው ዮሐ ፲፩፡፱
👉እርሱ ቸር እረኛችን ነው ዮሐ ፲፡፲፩
👉እርሱ የወይን ግንድ ነው ዮሐ ፲፭፡፭
👉እርሱ የጌቶች ጌታ የንጉሶችም ንጉሥ ነው ራዕይ ፲፯፡፲፬
👉እርሱ የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ ነው ሉቃ ፳፡፴፯
👉እርሱ እረፍታችን ነው ማቴ ፲፩፡፳፰
👉እርሱ ፍቅር ነው ፩ዮሐ ፬፡፰--
👉እርሱ የዋህ ነው ማቴ ፲፩፡፳፱
👉እርሱ ትሁት ነው ማቴ ፲፩፡፳፱
👉እርሱ የዓለምን ሀጢዓት ያስወገደ በግ ነው ዮሐ ፩፡፳፱
👉እርሱ የእኛ የበጎቹ በር ነው ዮሐ ፲፡፯
👉እርሱ ህማማችንን የተሸከመ አምላክ ነው ኢሳ ፶፫፡፭
👉እርሱ ስለብዙዎች ኃጢአት የተሰዋው ፍሪዳ ነው፤እርሱ መሥዋዕትን የሚያቀርብ፤መሥዋዕት ተቀባይም ነው ዕብ ፫፡፩
👉እርሱ ስለኛ መከራን የተቀበለ ስለኛም የራራልን ነው ፩ጴጥ ፬፡፩-፪
👉እርሱ ሙሽራ ነው፤እርሱ ራሱ ሙሽሪትም ነው ሉቃ ፭፡፴፬
👉እርሱ የሰርጉ ቤት ነው፤እርሱ ራሱ የሰርግ ቤቱ አሳላፊ ነው ማቴ ፱፡፲፭
👉እርሱ ገነት ነው፤እርሱ ራሱ የሕይወት ዛፍ ነው ራዕ ፲፪፡፲፬
👉እርሱ ሰማያዊ ኢየሩሳሌም ነው፤እርሱ ራሱ መቅደሳችንና ቅድስተ ቅዱሳናችን ነው
👉እርሱ ምግባችን ነው፤እርሱ ራሱ የሚመግበን መጋቢያችን ነው
👉እርሱ ሕያው የሆነ ህብስት ነው፤እርሱ ራሱ የደስታ ወይናችን ነው
👉እርሱ ዕንቋችን ነው፤እርሱ ራሱ መዛግብታችን ነው
👉እርሱ የጦር መሣሪያችን ነው፤እርሱ ራሱ ድል የሚነሣ ነው
👉እርሱ የቅዱሳን ህብረት ለሆነችው ቤተክርስቲያን ራስ ነው፤እርሱ መልካም የስንዴ ቅንጣት ነው
👉እርሱ የወይን እርሻችን ነው፤እርሱ ራሱ የእርሻው ባለቤት ነው
👉እርሱ ግርማችን ነው፤እርሱ እምነታችን ነው
👉እርሱ ሰርጋችን ነው፤እርሱ ራሱ የሰርግ ልብሳችን ነው
👉እርሱ የሕይወት መንገዳችን ነው፤እርሱ ራሱ በራችን ነው
👉እርሱ የጽድቅ ፀሐያችን ነው፤እርሱ ራሱ የነፍሳችን ብርሃን ነው
👉እርሱ ሞታችንን በሞቱ የገደለ ንጹህና ሀያል አምላክ ነው
👉እርሱ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ኦሜጋ ነው
📖ኧረ እርሱ እግዚአብሔር ነው!
ምንተብሎ በየትኛው ቃል ይገላጻል?እርሱ ሁሉ ነገራችን ነው!እንደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ትምህርት ከሄድን ገና ስለክርስቶስ ጫፉንም አልገለጽኩም!ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምረው ገና አንዱንም ገጽ ሙሉ አልገለጽኩም!
አንዳንድምስኪኖች እኛ
ሮሜ ፰፡፴፬ን
ዮሐ ፲፬፡፮ን
ዕብ ፯፡፳፬ን
፩ጢሞ ፪፡፭ን....ማንቀበልናማናምን ይመስላቸዋል!እኛ ከትርጉማቸው እንጂ ከቃሉ ችግር የለብንም!ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማያምነው ቃል የለም!እኛ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው የምናምነውን ለመፈለግ ሳይሆን የምናነበውን ለማመን ነው!ስለዚህ ከየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር የምስኪኖች አተረጓጎም እንጂ ቃሉ አያጣላንም!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema @dnzema @dnzema╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯