መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ| eotc theology ✟


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


t.me/kidanameherat16

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።


ዐቢይ ትኩስ ዜና

ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

© የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

source: BookClub Telegram Channel




ብቻህን ማሰብ ስትጀምር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የብቻችን የሆነ ትምህርት የለም። በማኅበር እንማራለን ፤ በማኅበር እንጸልያለን ፤ አንድ ሆነን የተዘጋጀልንን ማዕድ ቅዱስ ቊርባን እንቀበላለን ፤ በመጨረሻም የተዘጋጀልንን የተስፋ አገር እንቀበላለን።

ክርስቶስ ያስተማረ በጉባኤ ነው ፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ጉባኤአዊት ሆና ትቀጥላለች እንጅ ማንም ምንም ቢሆን የራሱን ትምህርት አምጥቶ ሊያስተምር የሚችልበት ዕድል የለውም።

የብቻው የሆነ ክርስቶስ ስለሌለው የብቻው የሆነ ትምህርትም ሊኖረው አይችልም።

ብቻህን ማሰብ ከጀመርህ ከጉባኤው የተለየ አስተምህሮ ማምጣትህ ስለማይቀር “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚለውን የሃይማኖት መግለጫ አስቀድመን እንድናውቅ መደረጉ ስለዚህ ነው።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖር ማንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ካስተማረችው ትምህርት የወጣ እንደሆነ መዐርጉ ፣ የዕውቀት ደረጃው ፣ የወገኑ የሀብቱ ብዛት ሊያድነው አይችልም። በመጀመሪያ ከቃሉ የሰሙ ሰዎች “የተናገርኸውን ትምህርት አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ብለው ይመክሩታል። ምክራቸውን ሰምቶ በዚህ ካቆመ ይተዉታል፤ ምክራቸውን አልሰማ ብሎ ከቀጠለ ግን ወደ መምህራን ያደርሱታል፤ መምህራንንም አልሰማ ካለ ወደ ጉባኤ {ሲኖዶስ} ይቀርባል። ሲኖዶሱን ካልሰማ ተወግዞ ይለያል።

በሰሞኑ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡትን ትምህርት በቪዲዮ አንዲት ወዳጄ ልካልኝ ተመለከትሁት፤ ምናልባት ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተማክረውበት ከበታቾቻቸውም ጋር ተከራክረውበት የነበረ ጉዳይ ከሆነ “አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ሊሏቸው ይገባ ነበር።

አሁን ግን በሹክሹክታ ሳይሆን በሰገነት ላይ የተሰበከ የስሕተት ስብከት ስለሆነ ጉዳዩ ከዚህ ያለፈ ይመስለኛል። ከረፈደም ቢሆን ባየሁት መረጃ መሠረት ብዙ ሊቃውንት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፤ ይሄ ለብፁዕነታቸው መልካም ዕድል ነው ብየ አምናለሁ። ሀሳባቸውን የገለጹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በሊቅነታቸው የምታምንባቸው ሊቃውንት እንደመሆናቸው መጠን ምክሩን ይቀበሉታል ብየ ስለማምን ነው። ሀሳቡን ሳይንቁ በቶሎ በሰገነት ላይ ያጠፉትን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሰገነት ላይ ወጥተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። “አትደንግጡ” ብለውናል እንዳንደነግጥ ያድርጉን።
ይህንን ትምህርት አባቶቻችን አልነገሩንም መጻሕፍቶቻችን ላይ ተጽፎ አላገኘነውም።

ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መጻሕፍቶቻችንን አባቶቻችንን ተቃውመዋል።  ዛሬ መልስ አልጽፍም፤ ምክንያቱም መልሱን ከብፁዕነትዎ ስለምጠብቅ ነው።

ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ


Репост из: ዝማሬ ቲዩብ zemare tube
├───────────────
├ቤዛዊተዓለም ማርያም
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•


Репост из: ዝማሬ ቲዩብ zemare tube


Репост из: ዝማሬ ቲዩብ zemare tube
"ሰዎች ማን እንደሆኑ ሲያሳዩህ በመጀመሪያው ቀን እመናቸው" ትላለች ማያ አንጀሎ

ይህንን ጽሑፍ ከትናንት በስቲያ ጽፌው ስሜታዊ ሆኜ እንዳይሆን በሚል ትንሽ ቆይቼ ልመልከተው ብዬ አሳደርኩት:: በቆይታ ሃሳቤ ሊቀየር ስላልቻለ እንደወረደ ለጥፌዋለሁ:: የምናገረው ነገርም እሳቸው ስለ ድንግል ማርያም ከተናገሩት አይከፋም:: ነገረ ሃይማኖታዊ መልስ ከበቂ በአደባባይ ተሰጥቶበታል:: ጉዳዩ ላይ ግን የምለውን ልበል::

ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር:: ጌታ በወንጌል "ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል:: በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደኃ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል:: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ማኅበር ለማጥራት ጊዜው አሁን ነው::
"ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ…?" የሚል ኢያሱያዊ ጥያቄ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው::

ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን:: ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር::

ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን:: አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ ፣ በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ ፣ ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ::

ያሁኑ ጳጳስ ትንሽ የሚለዩት ምንም ፈሊጥ የሌለው ያልተለሳለሰ $@&@@ ስለሚናገሩ ብቻ ነው:: የሆነ ቪድዮ ላይ Faith Alone የሚለውን የሉተር ትምህርት የኦርቶዶክስ ቆብ ደፍተው ሲሰብኩ ትንሽ እንኩዋን አላፈሩም:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል:: በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው:: ቤተ ክርስቲያን መናፍቃንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም::

በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም:: ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም:: የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም:: እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም:: ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን:: "የበራላቸው" ለመባል የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም::

ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም:: ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን::

ርጉመ ይኩን ዘይረግመኪ
ወቡሩከ ይኩን ዘይባርከኪ
ነገራተ ክልዔ ኢይርሳዕ ልብኪ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ገሊላ ፳ኤል
ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም
.


ከ''ቤዛ'' ባሻገር....
ከብጹእ አባታችን አቡነ ገብርኤል ንግግሮች ውስጥ ተኩረት የተሰጠው ''ቤዛ'' ላይ የሰሩት ስህተት ብቻ ይመስለኛል፤ ሙሉውን ለተመለከተ ከፍ ያሉ የስህተት ንግግሮችን ያገኝበታል።
እኔ ሁለት ነገሮችን ላስቀምጥ፤ መምህራን አስፋፍታችሁ ጻፉበት።

የመጀመሪያው፥ የእምነት ብቻ "Faith alone" (sola fide) ስብከታቸው፦ ከጌታችን ጎን የተሰቀለውን ወንበዴ ድኅነት በተመለከተ በተናገሩበት አንቀጽ፤ ለወንበዴው የተደረገውን በዚህ ዘመን ላለነው አምጥተው የሰጡበት መንገድ ፈጽሞ ስህተት ነው። ''እንደ ፌያታዊ ዘየማ ተዘከረነ ማለት እንጂ ምንም መሰቃየት አያስፈልግም። መሰቃየት የምትለዋ ቃል እመነት+ ስራ የሚለውን ለመቃወም የገባች መሆኗ ነው። This is totally an antinomian!

ሁለተኛ አዋልድ ላይ ያላቸው አታያይ፦ አሁንም በዛው በወንበዴው የመዳን ሂደት ላይ በትውፊት እመቤታችን ጌታ ይዛ ወደ ግብጽ በምትሰደድበት ወቅት ወንበዴዎች አግኝተዋቸው (ፈያታዊ ዘየማንና አጋሩን) የሚለውን ለማጣጣል የሄዱበት ርቀት > > ። አቡኑ ታሪኩ ላይ ጥያቄ አለኝ ማለት ይችሉ ነበር። አልያም ታሪኩ ስህተት ነው ለማለት የሚያስችላቸውን ማስረጃ ባላቀረቡበት ሁኔታ ''ተረት'' ወሸት'' የሚሉ አገላለጾች ጤናማ አይደሉም። ይህን አይነት አገላለጽ በፕሮቴስታንቶቹና በተሀድሶዎቹ የለመድነው ስለሆነ አባታችን ከየት አገኟት የሚል ጥያቄ ፈጥሮብናል። የዱቄት ብናኝ ያለበት ወየ የዱቄቱ ባለቤት ነው አልያም ወፍጮ ቤት ገብቶ ነበር...።

ብጹእ አባታችን እንዲሁ ከስብከት አውዳቸው አየወጡ የነካኳቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ ቢጎዳ ራሳቸውን እንጂ በሱስ የሚስት የለም ተብሎ ስለታሰበ ይመስለኛል ችላ የተባለው። የተረዳሁት ነገር ቢኖር አባታችን ብዙ የታመቀ ነገር ውስጣቸው አለ ለዚህም ነው ብዙ ቦታ ሲረግጡ ያየነው።
...






ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ድንግል ማርያም ..!

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም መባል እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ቤዛ ሆና ተሰቅላ አድናናለች ለማለት ሳይሆን የቀዳማዊት ሔዋን ምትክ፤ ምክንያተ ድኂን ማለታችን ነው፡፡ ቤዛ ማለት ምትክም፣ ፈንታ ተብሎ ይተረጎማል፡፡

ቤዛ ማለት በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዐላፊ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣መድን፣ ተያዥ፣ ጫማ ጥላ፣ ጋሻ ብለው ይፈቱታል፡፡

[✍️ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ 1958 ገጽ.266]

የቤተክርስቲያናችን ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሔዋንንና እመቤታችንን በማነጻጸር እመቤታችንን ዳግማይት ሔዋን [second Eve ] የሚል ስያሜ በመስጠት ያነጻጽራል👇

"የሐሰትንና የሞት መልእክትን የያዘውን እባብንና፣ የእውነትና የሕይወት መልእክትን የያዘውን ቅዱስ ገብርኤልን፤ የሐሰት የዲያብሎስን መልእክት በደስታ በመቀበል ለሰው ኹሉ ውድቀት መነሻ የኾነችውን ሔዋንንና፤ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን መልእክት በፍጹም እምነት ተቀብላ ሕይወት የሰጠን ጌታን የወለደችው ድንግል ማርያምን ሲያነጻጽር "The evil time which had killed Adam was changed, another good time came………" (አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ክፉ ቀን ተለወጠች፤ እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች፤ እባቧ ሳትኾን ገብርኤል ሊናገር ተነሣ፤ ሔዋን ሳትኾን ድንግል ማርያም ቃሉን ልትቀበል ተዘጋጀች፤ በተንኰል ቃል የሚያሳስተው ሳይኾን ሕይወትን የሚያውጅ እውነተኛ ቃል ወጣ፤ በሞት ዛፍ መኻከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው እናት ፈንታ[ቤዛ]፤ ልጇ የአባቷን ዕዳ ኹሉ ከፈለች፤ ሔዋንና እባቡ በመልአኩና በድንግል ማርያም ተተኩ፤ ያ ከመጀመሪያው የተበላሸውም ጉዳይ እንደ ገና ተስተካከለ፤ የሔዋን ጆሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ ምን ያኽል እንዳዘነበለ አስተውል፤ ነገር ግን ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረ መልአክ አኹን በማርያም ዦሮ የድኅነት የተስፋ ቃል ሲያሠርጽ የእባቡን ክፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ እርሷንም ሲያጽናና ተመልከት፤ያንን እባብ ያፈረሰችውን ሕንጻ ገብርኤል ገነባው፤ በዔደን ሔዋን ያፈረሰችውን ድንግል ማርያም መሠረቱን ገነባች፤ ከኹለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ኹለት ደናግል ኹለት፤ ኹለት ኾነው ትውልዶችን ቀጠሉ፤ አንዱ የአንዱ ተቃራኒ ኾነ፤ በእባብ አማካኝነት ሰይጣን ምስጢርን ለሔዋን ላከ፤ በመልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምስራቹን ወደ እመቤታችን ማርያም ላከ፤ እባብ የሐሰትን ቃል ለሔዋን ስትናገር ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለድንግል ማርያም ተናገረ፤ እውነትን በሚናገር አንደበቱ መልአኩ ቃሉን አደሰው፤ እውነትን ተናገረ በዚኽም ሐሰትን ኹሉ አስወገደው፤ ተንኰልን ከራሱ ባወጣ በሰይጣን በዔዴን ገነት ድንግሊቷ ተታለለች፤ ታላቁ ስሕተት በዦሮዋ ዐልፎ እንዲሰማት ዐደረገች፤ በመዠመሪያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፤ በዚኽችም ድንግል ዦሮ ከአርያም የመጣ የእውነት ቃል ገባ፤ ሞት በገባበት በዚያው በር ደግሞ ሕይወት ገባ፤ ክፉው ያጠበቀውን ጽኑዕ የሞት ማሰሪያ ፈታ፤ ኀጢአትና ሞት ከመዠመሪያው እጅግ እንደሰለጠኑ ኹሉ፤ እንዲኹ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ በአዳም ታየ፤ እባብ ከሔዋን ጋር ስትነጋገር ሔዋን አልተንበረከከችም አልሰገደችም፤ ሞት በመላበት ጐዳና ሰላምና ትሕትና አይገኙምና፤ እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረ ሐሰትን ረጨባት፤ በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በኾነች ሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት ፈሰሱ፤ ለመግደል የኾነ ጠላትነትና ክፉ ምክር ደምን የተጠማ መርዙን በንግግሩ ውስጥ በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ፤ በወልድ የተላከው መልአክ እነዚኽን የክፋት ሰይፎች ለመቋቋም ኼደ፤ ለድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር የኾነውን የመዳን ብሥራትን ነገረ፤ ሰገደላት፤ ሕይወትን በውስጧ አሠረጸ፤ ሰላምን ዐወጀላት፤ በፍቅር ቀረባት፤ የቀደመውን የሞት ዳባ በጣጠሰ፤ እባብ የገነባው የማታለል ግንብ ዳግመኛ ላይገነባ በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ተናደ፤ በእባብ የታጠረው የሞት ቅጥር በወልድ መውረድ ተሰባበረ፤ በሰማያትና በምድር በሚኖሩ ኀይላት መኻከል ሰላም ይወርድ ዘንድ"
[✍️ Jacob of Serugh on the Virginity pp 29-34]

ስለሆነም መጋብያነ ምስጢር ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ፣ ከነገረ ድኅነት (Soteriology) አንፃር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ትባላለች ሲሉም አርቅቀውና አርቀው ነው፡፡

ስለዚህም ልክ እንደ አባታችን ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

"እንዘ ይብሉ ቅድስት ቅድስት ቅድስት ማርያም፣  ወላዲተ ክርስቶስ በአማን ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም"
      [ሰዓታት ኲሎሙ ዘቁስቋም]

ብለን እናመሰግናታለን። ለመናፍቃን እና በሁለት ማልያ ለሚጫወቱ ብለን የቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ አናመቻችም !!


ከትንሳኤ እስከ ዳግም ትንሳኤ የዕለታቱ ስያሜ መሰረት ትክክለኛው የቱነው?
Опрос
  •   ሰኞ ማዕዶት
  •   ማክሰኞ ቶማስ
  •   ረቡዕ አላዛር
  •   ሐሙስ አዳም
  •   አርብ ቅድስት ቤ/ክ
  •   ቅዳሜ ቅድሳት አንስት
  •   ሁሉም
20 голосов


💖        🍒        💖

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡


✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
💛
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
💛
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡


✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ
ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ
ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።



          ✝ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ✝




ውድ ዚህ ቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
የዕለቱን ሥርዓት እና ምስጋና ይዤ ቀርብያለዉ።

መልካም የአገልግሎት ጊዜ ይሁንላችሁ 🙏🙏🙏
መልካም በዓል 🙏🙏
🙏

🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
የትንሣኤ #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።


ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።
"ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ሥዕል አይባልም።


ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት ፫ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።
(ምልክቱን ከታች ካለዉ ግጻዌ ይመልከቱ)

አርያም
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
✝ ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

አንገርጋሪ
ሃሌ ሉያ ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን፤ ተንሥአ እምነ ሙታን።

ምልጣን
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን፤ ተንሥአ እምነ ሙታን።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/

ወረብ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/

እስመ ለዓለም፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።

አመላለስ
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/

ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ ሰላም ይፃፋል
ሰላም፦

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሩቱ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።

አመላለስ
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ/፬/

ኪዳንን ከተደረሰ በኋላ
👇👇👇👇👇
መዝሙር
ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይበውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

ምልጣን:-
ወይበውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

አመላለስ
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/

ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኰነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኰርዕዎ ርእሶ በህለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።

ምልጣን:-
ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።

✝✝✝✝✝✝✝✝
ከዚህ በኋላ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴ




ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ ስግደት


በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች እንመልከት

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታችንን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም ይኸውም ቆሎ ዳቦ ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13  ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ሕማማት_በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ.pdf
42.3Мб
.

📚ርዕስ:- ሕማማት
✍️ደራሲ:- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


📚 @dnzema

Показано 20 последних публикаций.