ይህም እመቤታችንን እግዚአብሔር ለእናትነት እንደመረጣት እና በንፅሐ ሥጋ፣ በንፅሐ ነፍስ፣ በንፅሐ ልቦና እንዳስጌጣት የሚያስረዳ ኃይለ ቃል ነው።
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፫, #ድንግልናዋ
...ከሊቃውንት መካከልም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ስለ እመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና እንዲህ ሲል ተናግሯል። “ሥጋ የሌለው እርሱ ሥጋዋን ተዋሕዶ እንደ ሰው ሁሉ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በጌትነቱ ሳለ በማኅፀኗ ተወሰነ። ከዚያ በኋላም የሚወለድበት ቀን ሲደርስ በማይመረመር ግብር በኅቱም ድንግልና ተወለደ ማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተወለደ እንጂ። ”ብሏል (ሃ.አ ገፅ 212)
“አምላክን የወለደች ማርያም ለዘለዓለሙ ድንግል እንደሆነች መውለዷም የማይመረመር ድንቅ እንደሆነ ከወለደችም በኋላ በድንግልና ፀንታ እንደኖረች አስረዳ” ሲል የተናገረው ደግሞ አባታችን የአንፆኪያው ሊቅ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ነው። (ሃ.አ.ገፅ 375)
ቅድስት ድንግል ማርያም መድኃኒታችንን ከወለደች በኋላ ድንግል አይደለችም ለሚሉ መናፍቃን መልስ በሰጠበት ድርሳኑ ቅዱስ ጀሮም “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዘጋው በር እንዴት እንደገባ ይንገሩኝና ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን እነግራችኋለሁ” ብሏል። (St.mary in the orthodox concept by
Tadros malaty).
ስለዚህ የእርሷ የድንግልና ምስጢር በሥጋዊ አዕምሮ ሊደርስባት የማይቻል ድንቅ ነው። ቅዱስ ኤፍሬምም ነቢዩ ሕዝቅኤል የተናገረውን ትንቢት ሲተረጉም እንዲህ ብሏል “ነቢዩ ሕዝቅኤል የመሰከረለት ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ከኃያላኑ ጌታ በቀር ማንም ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም በምሥራቅ ያያት ደጅ የተባለች መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞው በድንግልና ኑራለችና መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለድሽ ሆይ የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው። አንቺ ፍፅምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖሩ ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ላንቺ ይገባል። ”በማለት በረቡዕ ውዳሴው አመስግኗታል።
እኛም የድንግልናዋን ነገር በአንክሮ እያሰብን ለምኝልን ልንላት ያስፈልጋል።
፪.፪, #ክብረ_ድንግል
፪.፪.፬, #የክብረ_ድንግል_መገለጫዎች
ክብር የሚለው ቃል ጌትነትንና ከፍተኛነትን የሚያሳይ ነው። ከሁሉ በላይ ክብር ያለው እግዚአብሔር ነው። ክብሩም በሥራው ይታያል። (መዝ 18፥1 / ዘፀ 16፥7 / ኢሳ 6፥3) እግዚአብሔር ክቡር በመሆኑ የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ቅድስት ድንግል ማርያም አንዳች ያልጎደለባት ምልዕተ ጸጋ ስለሆነች እግዚአብሔርም ከእርሷ ጋር ስለሆነ ክብርት ናት። እንኳን መልዕልተ ፍጡራን የሆነች እርሷ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ክቡር ነው። (ሉቃ 2፥9 / 1ኛ ቆሮ 11፥7 / 1ኛ ቆሮ 15፥41)
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩን በተአምራቱ በደብረ ታቦር በትንሣኤውና በዕርገቱ ገልጧል። ዮሐ 2፥11 / ማቴ 17፥1 / 1ኛ ጴጥ 1፥20 በኋላም በዳግም ምጽአቱ ይገለጣል። (ማር 8፥38) የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ደግሞ የተገለጠው አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ ነው። ይህ ክብር ልዩ ነው። ምክንያቱም ከእርሷ በቀር የአምላክ እናት የሆነ የለምና ወደ ፊትም አይኖርም።
እመቤታችንን አስቀድሞ ያከበራት ልዑል እግዚአብሔር ነው። ነቢያትም እግዚአብሔር በገለጠላቸው መንገድ በትንቢት መነጽር እያዩዋት ክብሯን ተናግረውላታል። የምሥራቹን ይነግራት ዘንድ ወደ እርሷ የተላከ ቅዱስ ገብርኤልም አብስሯታል። ቅድስት ኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ አነቃቅቷት የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ አይገባኝም ብላ አክብራታለች፤ ዮሐንስም በራዕዩ “ፀሐይን ተጎናፅፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋ ላይ አሥራ ሁለት ከዋክብት የሆነላት”። በማለት ክብሯን በሰማይ ከፍ ብሎ በማየቱ አክብሯታል። ከነቢያት ለመጥቀስ ያህል ቅዱስ ዳዊት "ንግሥቲቱ በወርቅ ልብስ ተጎናፅፋና ተሸፋፍና በቀኝህ ትቆማለች" ያለው የእመቤታችንን ክብሯን ሲገልጥ ነው። (ራዕ 12፥1 / መዝ 44፥9) ቤተ ክርስቲያናችን የእመቤታችንን ክብር ስለምታውቅና ስለምታምን ለምዕመናን ሁሉ የድንግል ማርያምን ክብር ታስተምራለች ምዕመናንም ይህንን አውቀው ያከብሯታል።
አባታችን ቅዱስ ኤፍሬምም በረቡዕ ውዳሴው “ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማህፀኗ ተሸክማዋለች እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ከሱራፌልም ትበልጣለች ከቅድስት ሥላሴ ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህቺ ናት። ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት ሲል የተሰጣትን ክብር ገልጧል። እኛም ቅዱስ ኤፍሬምን አብነት አድርገን እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናከብራታለን።
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->ስግደት ለእመቤታችን
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!💐
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯