ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ድንግል ማርያም ..!
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም መባል እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ቤዛ ሆና ተሰቅላ አድናናለች ለማለት ሳይሆን የቀዳማዊት ሔዋን ምትክ፤ ምክንያተ ድኂን ማለታችን ነው፡፡ ቤዛ ማለት ምትክም፣ ፈንታ ተብሎ ይተረጎማል፡፡
ቤዛ ማለት በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዐላፊ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣መድን፣ ተያዥ፣ ጫማ ጥላ፣ ጋሻ ብለው ይፈቱታል፡፡
[✍️ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ 1958 ገጽ.266]
የቤተክርስቲያናችን ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሔዋንንና እመቤታችንን በማነጻጸር እመቤታችንን ዳግማይት ሔዋን [second Eve ] የሚል ስያሜ በመስጠት ያነጻጽራል👇
"የሐሰትንና የሞት መልእክትን የያዘውን እባብንና፣ የእውነትና የሕይወት መልእክትን የያዘውን ቅዱስ ገብርኤልን፤ የሐሰት የዲያብሎስን መልእክት በደስታ በመቀበል ለሰው ኹሉ ውድቀት መነሻ የኾነችውን ሔዋንንና፤ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን መልእክት በፍጹም እምነት ተቀብላ ሕይወት የሰጠን ጌታን የወለደችው ድንግል ማርያምን ሲያነጻጽር "The evil time which had killed Adam was changed, another good time came………" (አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ክፉ ቀን ተለወጠች፤ እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች፤ እባቧ ሳትኾን ገብርኤል ሊናገር ተነሣ፤ ሔዋን ሳትኾን ድንግል ማርያም ቃሉን ልትቀበል ተዘጋጀች፤ በተንኰል ቃል የሚያሳስተው ሳይኾን ሕይወትን የሚያውጅ እውነተኛ ቃል ወጣ፤ በሞት ዛፍ መኻከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው እናት ፈንታ[ቤዛ]፤ ልጇ የአባቷን ዕዳ ኹሉ ከፈለች፤ ሔዋንና እባቡ በመልአኩና በድንግል ማርያም ተተኩ፤ ያ ከመጀመሪያው የተበላሸውም ጉዳይ እንደ ገና ተስተካከለ፤ የሔዋን ጆሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ ምን ያኽል እንዳዘነበለ አስተውል፤ ነገር ግን ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረ መልአክ አኹን በማርያም ዦሮ የድኅነት የተስፋ ቃል ሲያሠርጽ የእባቡን ክፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ እርሷንም ሲያጽናና ተመልከት፤ያንን እባብ ያፈረሰችውን ሕንጻ ገብርኤል ገነባው፤ በዔደን ሔዋን ያፈረሰችውን ድንግል ማርያም መሠረቱን ገነባች፤ ከኹለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ኹለት ደናግል ኹለት፤ ኹለት ኾነው ትውልዶችን ቀጠሉ፤ አንዱ የአንዱ ተቃራኒ ኾነ፤ በእባብ አማካኝነት ሰይጣን ምስጢርን ለሔዋን ላከ፤ በመልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምስራቹን ወደ እመቤታችን ማርያም ላከ፤ እባብ የሐሰትን ቃል ለሔዋን ስትናገር ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለድንግል ማርያም ተናገረ፤ እውነትን በሚናገር አንደበቱ መልአኩ ቃሉን አደሰው፤ እውነትን ተናገረ በዚኽም ሐሰትን ኹሉ አስወገደው፤ ተንኰልን ከራሱ ባወጣ በሰይጣን በዔዴን ገነት ድንግሊቷ ተታለለች፤ ታላቁ ስሕተት በዦሮዋ ዐልፎ እንዲሰማት ዐደረገች፤ በመዠመሪያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፤ በዚኽችም ድንግል ዦሮ ከአርያም የመጣ የእውነት ቃል ገባ፤ ሞት በገባበት በዚያው በር ደግሞ ሕይወት ገባ፤ ክፉው ያጠበቀውን ጽኑዕ የሞት ማሰሪያ ፈታ፤ ኀጢአትና ሞት ከመዠመሪያው እጅግ እንደሰለጠኑ ኹሉ፤ እንዲኹ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ በአዳም ታየ፤ እባብ ከሔዋን ጋር ስትነጋገር ሔዋን አልተንበረከከችም አልሰገደችም፤ ሞት በመላበት ጐዳና ሰላምና ትሕትና አይገኙምና፤ እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረ ሐሰትን ረጨባት፤ በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በኾነች ሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት ፈሰሱ፤ ለመግደል የኾነ ጠላትነትና ክፉ ምክር ደምን የተጠማ መርዙን በንግግሩ ውስጥ በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ፤ በወልድ የተላከው መልአክ እነዚኽን የክፋት ሰይፎች ለመቋቋም ኼደ፤ ለድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር የኾነውን የመዳን ብሥራትን ነገረ፤ ሰገደላት፤ ሕይወትን በውስጧ አሠረጸ፤ ሰላምን ዐወጀላት፤ በፍቅር ቀረባት፤ የቀደመውን የሞት ዳባ በጣጠሰ፤ እባብ የገነባው የማታለል ግንብ ዳግመኛ ላይገነባ በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ተናደ፤ በእባብ የታጠረው የሞት ቅጥር በወልድ መውረድ ተሰባበረ፤ በሰማያትና በምድር በሚኖሩ ኀይላት መኻከል ሰላም ይወርድ ዘንድ"
[✍️ Jacob of Serugh on the Virginity pp 29-34]
ስለሆነም መጋብያነ ምስጢር ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ፣ ከነገረ ድኅነት (Soteriology) አንፃር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ትባላለች ሲሉም አርቅቀውና አርቀው ነው፡፡
ስለዚህም ልክ እንደ አባታችን ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
"እንዘ ይብሉ ቅድስት ቅድስት ቅድስት ማርያም፣ ወላዲተ ክርስቶስ በአማን ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም"
[ሰዓታት ኲሎሙ ዘቁስቋም]
ብለን እናመሰግናታለን። ለመናፍቃን እና በሁለት ማልያ ለሚጫወቱ ብለን የቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ አናመቻችም !!