በርግጥ ከሳምንታት በፊት እንዲህ በእግዚአብሔር ላይ አላግጠው ከኾነ፣ ቅዱስ ቃሉ በግልጥ፣ “አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤”(ገላ. 6፥7) ይላል። በአዲስ ኪዳን እንደ ብሉይ ኪዳን ያለ፣ ቃልኪዳናዊ ታማኝነትን በማጓደል ምድራዊ የኪዳን ዕርግማን አለ ብዬ ባላምንም፣ እንዲህ ያለ ጸያፊ ስላቅና ሹፈት ግን ሳያስቀጣ አይቀርም ብዬ አምናለኹ። አኹንም ቢኾን እግዚአብሔር በመግቦቱ ለምድራችን ይራራ፤ አሜን።
የዩቱዩብ አድራሻ - https://youtube.com/shorts/x2yhDOJUAvg?si=soSPFy6tiBLJkN5n
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek
የዩቱዩብ አድራሻ - https://youtube.com/shorts/x2yhDOJUAvg?si=soSPFy6tiBLJkN5n
የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek