Фильтр публикаций


ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ያስፈልገናል!

ከዚህ ቀደም የጻፍኹትን ልጥቀስ፣

“ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣ “ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ አያመለክትም።” [1]

ወደ ርዕሳችን ስንመለስ፣ ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ማለት፣ በጌታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ተሰጡት ትምህርቶች፣ ወደ ተኖሩ ልምምዶችና ትውፊቶች በመመለስና ብሎም አሠረ ፍኖታቸውን በመከተል እውነተኛ የሕይወትና የኑሮ ተሐድሶ ማምጣት የሚል ፅንሰ ዐሳብ በውስጡ የያዘ ነው። ይህ የሚኾንበት ዋነኛ ምክንያቱ፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት፤ በተለያዩ ታሪኮችና በተለያዩ ኹኔታዎች ውስጥ በማለፍዋ ምክንያት፣ ለተለያዩ እንግዳ ትምህርቶችና ልምምዶች ልትጋለጥ ትችላለች ወይም ተጋልጣ ታይታለች።
በአዲስ ኪዳን ምንባባት ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ፣

“ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” (ማቴ. 16፥6)፣ “ምን ወይም እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ።” (ማር. 4፥24፤ ሉቃ. 8፥18)

እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ፣

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።” (ሐ.ሥ. 20፥28-30)

ብለው ሲናገሩ፣ ቤተ ክርስቲያን ባለመጠንቀቅዋ ምክንያት ለተለያዩ እንግዳና ልዩ ልዩ ትምህርቶች ልትጋለጥ እንደምትችል አመልካች ናቸው።

ለዚህም ነው ለተለያዩ እንግዳና ልዩ ልዩ ትምህርቶች ከተጋለጡት አብያተ ክርስቲያናት መካከል ገላትያን እንዲህ በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የሚናገረው፤

“በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።” (ገላ. 1፥6-7 ዐመት)።
በዚህ ክፍል ላይ የገላትያ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ባለ ውድቀት ውስጥ መግባትዋን እናስተውላለን። ብዙዎች እንዲህ ስንናገር፣ “ቤተ ክርስቲያን አትሳሳትም፤ ሰዎች እንጂ” የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ። ይህን በሌላ ርዕስ እመለስበታለሁ።

ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ፣ እውነት ኾኖ በብዙዎች ልብ ያለ ቢኾንም፣ ነገር ግን ለመቀበልና ለመተግበር ብዙዎች ፈቃደኞች የኾኑ አይመስሉም። እንዲያውም፣ ተሐድሶ ሲባል በብዙዎች ልብ ያለው፣ “ኦርቶዶክስን ወደ ወንጌላውያን የመውሰድ ወይም ፕሮቴስታንት የማድረግ ዝንባሌ” እንደ ኾነ ተደርጐ ሲወሰድ ይስተዋላል፤ በርግጥ ይህ ስህተት አልተፈጸመም ማለት አይቻልም። ነገር ግን እውነተኛውና ወደ አዲስ ኪዳናዊ ወይም ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት የመመለስ ተሐድሶ፣ ተቋም የመለወጥ አልያም ስፍራ የማቀያየር ተግባር ነው ማለት አንደፍርም።

የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን፣ ባለፉት ኹለት ሺህ አመታት አልፋ በመጣችባቸው ልዩ ልዩ ጎዳናዎች፣ ወድቃም፤ ተሳስታም አሳስታም ኖራ፣ ነገር ግን በጌታ ምሕረትና ጥበቃ፤ በትድግናውና በሉዓላዊ መግቦቱ ግን እስከ አኹን አለች። ስለዚህ ባለፉት ዘመናት በውስጧ የገቡና የሰረጉ፤ በዘመን ርዝመት እውነት የመሰሉ አያሌ ስህተቶችና እንከኖችን አስወግዳ፣ ስትመሠረት በነበረችውና ለመሲሑ ቃልና ሕይወት፤ ትምህርትና ልምምድ በመገዛት በቄሣርና በአላውያን ነገሥታት ፊት ተፈርታና ታፍራ እንደ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ትኾን ዘንድ መመለስ ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ስለዚህም ደፍረን በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ የኾነው ኹሉ ይንጸባረቅ ዘንድ እንመለስ እንላለን!

በአጭር ቃል፣ የክርስቶስ ሕይወት ሕይወታችን፤ ኑሮው ኑሮአችን፤ ትምህርቱ ትምህርታችን፤ ልምምዱ ልምምዳችን፤ ሥራው ሥራችን ኾኖልን፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉን በመመለስና ርሱን በመከተል ሕይወት በመኖር የመንፈሳዊ እውነተኛ የሕይወት ተሐድሶ እናመጣ ዘንድ ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶን በእውነት እንድርግ እንላለን!
[1] http://abenezerteklu.blogspot.com/2021/09/blog-post_29.html

My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/2025/01/blog-post_31.html


ተሐድሶ የቀደመውንና የተቀበረውን የጌታና የሐዋርያትን ትምህርት ማውጣትና ማሳየት እንጂ፣ አዲስ ትምህርት ማስተማር አይደለም።


አስተርዕዮ መንፈስ ቅዱስ፣ ወደ አብ ልጅ ወደ ክርስቶስ ያደርሳል። "አስተርዕዮ ማርያም" ግን ከታቦት ንግሥ በቀር ሌላ ምን ትርፍ አለው?! ወደ ክርስቶስ አለመድረስ አለመታደል ነው!


ጤናማና ትክክለኛ የቤተክርስቲያን መሪ ስትኾን እንዲህ ታስባለህ፤ ትጨነቃለህም።
በCordova ግዛት የTrinity Baptist Church ቄስ ወይም መጋቢ የኾነው  Matt Crawford እንዲህ ይላል፦

" ... ቤተክርስቲያን ለሰዎች የእምነት ቦታ ከአምላካቸው ጋር በጋራ በአምልኮ የሚያሳልፉባት ቦታ መኾንዋ ቀርቶ፣ በአዲሱ የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ወረራ እየተደረገባትና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና የአገሪቱን የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ውሳኔ እየተጠባበቁ ያሉትን ሰዎች ማፈሻ ቦታ ኾናለች። እኔም የቤተክርስቲያን መሪ እንደ መኾኔ፣ ልቤን ክፉኛ አስጨንቆታል። የወሰድኩትን ትንሽ የእረፍት ጊዜ በአግባቡ እንዳልጠቀም አእምሮዬን እረፍት ነስቶታል። ለእነዚህ በአገራቸው በሰላምና በመልካም ኹኔታ መኖር አቅቷቸው ወይም የተሻለ ኑሮ ለልጆቻቸው ፍለጋ ለተሰደዱትና በፍርሃት ላሉት አምላኬን እለምናለሁ። ብርቱ ጸሎት ያሻናል።
እኔም ስደተኛ ነኝ። ..."

“በስደተኛው ግፍ አታድርጉ፤ እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ የስደተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች አውቃችኋልና።”(ዘጸ. 23፥9)

“እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ዓይነት ሕግ ይሁንላችሁ።”(ዘሌዋ. 24፥22)

ይህን የተገለጠ ቅዱስ ቃል፣ ኹል ጊዜ ዓለማውያንና አረማውያን ከሚሠሩት የግፍ ሥራ ጋራ "ሰባኪና አገልጋይ ነን" የሚሉ ሰዎች ሲተባበሩ ሳይ፤ ጨውነትና ብርሃንነትን ሲሸሽጉ ስመለከት እተክዛለኹ፤ እጨነቃለኹ።

ይህ ወንድማችን ግን እጅግ የተወደደ ነው። ከግፉአን ጎን በመቆም ብርሃንነቱን ገልጦአል። ጌታ አብዜቶ ይባርከው።

ጌታ ሆይ የክፋት ቀናትን አሳጥርልን፤ አሜን። (የቄሱን ሙሉ መልእክት - https://churchleaders.com/news/)

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ድኻ ጠሉ በጋሻው ደሳለኝ!

"የድኾችን ጩኸት ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እርሱም ተቸግሮ በሚጮኽበት ጊዜ የሚረዳው አያገኝም።" (ምሳ. 21፥13)

በተቸገርን ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታችንን ይሰማን ዘንድ፣ የወገኖቻችንን ችግር በመስማት በፍቅር ልንደርስላቸው ይገባል። ጌታችን ኢየሱስ የታረዘውን ስናለብስ ርሱን እንዳለበስን እንደሚቆጥር በግልጥ ተናግሮአል፤ (ማቴ. 25፥40)። በአዲስ ኪዳን የጥበብ መጽሐፍም እንዲህ ይላል፣ “የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።”(ያዕ. 2፥13)።

እግዚአብሔር ምሕረት የሚያደርገው፣ ለሚምሩና ለሚራሩ ነው። የሚምሩ ምስጉኖች ናቸው ፍጹም ይማራሉና እንዲል። ስለ ድኾች የጌታ ትምህርት አጭርና ግልጽ ነው። ለኹል ጊዜ ከእኛ ጋር አብረውን እንዳሉ፤ ደግሞም ይኖራሉ።“ድሆችስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና”(ዮሐ. 12፥8) እንዲል። ድኾች ቤት ፈርሶባቸው ቢጮኹና ቢያለቅሱ ቅንጦት ወይም አዚም ተደርጎባቸው አይደለም። አልያ ድኾች መሻሻል የሚጠሉ፤ ድህነት ወይም ችጋር ወይም ሰቆቃ እንደ ዕጣ ፈንታ የተጣባቸው አይደሉም። ማንም ልማት የሚጠላ ጤነኛ ሰው የለም፤ ቁስ ግን የቱንም ያህል ቢጌጥና ቢያምር፣ ሰውን ካልጠቀመ፤ ለእግዚአብሔር ክብር ካልኾነ፤ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው!

ስለ አንዳንድ "ወንጌላውያን" ነን ስለሚሉ አገልጋዮች አዝናለኹ። ከኦርቶዶክስ ያልተማሩ "አዚማሞች" ናቸው። ትላንት ኦርቶዶክስ መንግሥትን ተጠግታ የሠራችውን ስህተት እነርሱ ዛሬ በአደባባይ በብዙ ማስረጃ ፊት ይፈጽሙታል። ለምን መከራ ታጎመሩልናላችኹ? እንደ ከረመ ወይን ለምን መከራ ታሰነብቱልናችሁ? ለተጣለላችኹ ቅልጥም እዚያው ለፍልፉ እንጂ በወንጌል ታክካችኹ መጥታችኹ ወንጌሉን በማያምኑ ዘንድ አታሰድቡ፤ ለደካሞችም የማሰናከያ ዐለት አታኑሩ!


ተሐድሶ ለኦርቶዶክስ እንዲኾን ዘወትር በቅንነት የምንመኘው፣ ሕዝቡ የእግዚአብሔር ገንዘብ ስለኾነና "የሞቱና ያሉ ቅዱሳንን" ተስፋ ማድረግ ስለሌ*ለበት ነው! የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ብቻ ይገባል!


ተሐድሶም አብሮ እንዳይገፋ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ የቤተክርስቲያ መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየሠራች መኾኑን በራሷ የትስስር ገጾች አመልክታለች። ቤተክርስቲያኒቱ በተለይም፣
" ... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ
* በአስተምህሮቿ
* በዕምነቷ
* በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል ..." በማለት ገልጻለች።

ከዚህም የተነሳ፣ " ...ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።" ብላለች።
 
ከዚህ በዘለለም ጉዳዩ ወደ ክስ ጭምር ሊያመራ እንደሚችል ጠቁማለች።
ይህ አቋሟን በተወሰነ መንገድ ከሚደግፉት መካከል ነኝ። ምንም እንኳ ቤተ ክርስቲያኒቱ ኹለንተናዊ ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት ባምንም፣ በጥላቻ፣ በማናናቅ፣ ርኅራኄ በራቀውና በመሳለቅ ሊኾን ይገባል ብዬ አላምንም። አያሌ ስህተቶች፤ እልፍ እንከ*ኖች፤ የታጨ*ቁ ግድፈቶች በሌላ የስህ*ተት መንገድና የግዴለሽነት ተግባር ይስተካከላሉ የሚል አቋም የለኝም።

እንዲህ የሚያደርጉ አካላት አንዳንዶቹ፣ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በግል እስከ መካሰስ የደረሱ ናቸው፤ ውስጣቸው ንቀትና ጥላቻ የተመላ ከመኾኑም ባሻገር፣ ርኅራኄ አልባ ናቸው። በትክክል የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት የማያውቁም አሉ፤ እኒህን ማስተካከልና መግራት የሚቻል ይመስለኛል። ሌሎች ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን በግልጥ ቃል "ጋለሞታ፤ የሞተች ..." በማለት የሚጠሩም አሉ። በልዩነት ደግሞ የቤተክርስቲያኑን መመለስና መታደስ ናፍቀው፤ ልብዋን ወደ ወንጌል እንድታቀና የሚተጉላት፤ ተስፋና ዕድል አላት ብለው ሳይሰለቹ ስህተቷንና እንከኖቿን በሙግት፣ ብርታትዋን ደግሞ በማጽናት፤ በጸሎትም ከልብ በማሰብ የሚሠሩ ጥቂቶችም አሉ።

ፍርሃቴ ወይም ስጋቴ

ቤተክርስቲያኒቱ በሚደረግባት አሉታዊ ጫናዎች ተሐድሶን ጨርሶ እንዳትገፋ ፍርሃትም፤ ስጋትም አለኝ። ቤተክርስቲያኒቱ ተሐድሶን ከመግፋት ይልቅ ከዚህ በፊት ተቀብለው እንደ ጀመሩት አበው፣ ብታስቀጥል ትጠቀማለች እንጂ አንዳች አትጎዳም። ለሲኖዶስ በቀረቡት ተደጋጋሚ ጥቆማዎች የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ቁጥር መቀነስ ኹነኛ ምክንያቱ የወንጌል በትክክል አለመሰበክና ብሎም የወደቀ "የጽድቅ ሕይወት" መኖር መኾኑ ተጠቅሶአል።

እናም ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ክስና ሕጋዊ እርምጃ የምታመራውን ያህል ለተሐድሶም እጇን ብትዘረጋ መልካም ነው የሚል እምነት አለኝ።

ጌታ እግዚአብሔር በመግቦቱና በትድግናው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በወንጌልና በማይለወጠው የጽድቅ ቃሉ በተሐድሶ ይጎብኝ፤ አሜን።


የጡመራ መድረክ አድራሻ - https://abenezerteklu.blogspot.com/2025/01/blog-post_27.html?m=1


"በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል ዐሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፣ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፣ አንተንም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።" (ዘዳ. 14፥28-29)

አሜሪካ ከሰሞኑ መጻተኞችን ከምድሯ ነቅላ እያሳደደችና ወደ "አገራቸው" እየሰደደች ነው። የእግዚአብሔር ቃል መጻተኛን መቀበል የእጅ ሥራ መባረክ ምክንያት እንደ ኾነ ይነግረናል። በርግጥ ኢትዮጵያ በምድርዋ ላይ እንኳን መጻተኞችን ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ለሚሄዱ ቀጋ መኾንዋ የታወቀ ነው። ጌታ ለመሪዎች አስተዋይ ልብ ይስጥ፤ አሜን።

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek


ጥበብ ልቆ ታየ!

የጠቢባን ምክር የአስተዋዮች ጥበብ
የኀያላንና ባላባቶች መዝገብ
የብርቱዎች ትምክህት የብዙዎች ክብር
ዝናና ጀግንነት ልዕልና ወንበር
ውበት ብልጥግና የዚህ ዓለም ነገር ...
መሲሑ ሲመጣ
ረብና ጥቅም አጣ
ሥጋ የለበሰ ኹሉ እንዳይመካ
የኾነውን ነገር መሲሑ አጠፋ።

ከዚህ የተነሳ!
የተናቀው ከብሮ ምናምንቴው ቆመ
ደካማው ተመርጦ ምርጡ ግን ደከመ
የዓለምን ጥበብ ሊያሳፍር ብሎ
ጥበብ ልቆ ታየ በሕፃናት አእምሮ!


ምንም ሠርቼልህ አይደለም፤ እንዲኹ ወደድኸኝ፤ ተባረክ ኢየሱስ!


ተቃርኖ!

በእውነት ለመናገር በዚህ "ሰባኪ" ንግግር ውስጥ በግልጥ አምልኮተ ማርያም አለ። ወደ ማርያም መጸለይና ወደርስዋ ልመና ማቅረብ "አምላክ ናት" ብሎ የማመን ያህል ከባድ ጥፋት ነው።

እኛስ እንደ ቅዱስ ቃሉ፣

“... ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ ...”(2ቆሮ. 1፥9) ደግሞም፦ “... በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።”(ኤር. 17፥5) ይላልና፣ ፈጽሞ ወደ ፍጡር አንጸልይም። ምናልባት አንዳንዶች ድንግል ማርያምን መለመን እንዴት ያስረግማል? ቢሉ፣ ማርያም ቅድስትና ብጽዕት ብትኾንም፣ ነገር ግን እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ የሞተች ደግሞም እንደ ኹሉም አማኞች የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ እንደምታደርግ መዘንጋት አይገባም።

ጸሎትን ወደሚሰማውና ወደሚመልሰው ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ጸልዩ፤ ከዚህ ውጭ ግን ወደ ሞቱ ቅዱሳን መጸለይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ የኾነ እንግዳ ልምምድ ነው።

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek

የዩቲዩብ አድራሻ - https://youtube.com/shorts/IwYHr-9KgpQ?si=PEt8kJjuh7dtt5-V


በስድስት ወር ብቻ 3769 የጋብቻ ፍቺ በአዲስ አበባ! ከአምናው በ38% ጨምሮአል! ኢትዮጵያ ይህች ናት፤ ትውልድ እያፈረሰች ለሕንጻ ግንባታ የምትራኮት!


“ከዛሬ ጀምሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጾታን በተመለከተ የሚኖረው ይፋዊ ፖሊሲ ወንድ እና ሴት ብቻ ይሆናል።”

ይህን የተናገሩት የአሜሪካው አዲሱ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

ኀጢአት በኹሉ ዘንድ ሲገንንና የኑሮ ዘይቤ ሲኾን፣ ተፈጥሮ ወንድና ሴት ብቻ ናት ብሎ መናገር ብርቅ ይኾናል። እኛም በአገራችን ሳይታወቀንም ይኹን እየታወቀን ወደ መላመድ የመጣናቸው አያሌ ዐመጽና ክፋቶችም አሉና ጌታ ይራራልን፤ የአሜሪካውንም ፕረዘዳንት ነገ እንዳይለወጥ፤ ብዙ በጎ እንዲያበዛለት ጌታ ብርሃኑን ያብዛለት፤ አሜን።

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek


በደርባ ከተማ ከታቦት ማደርያው ላይ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና ሌሎችንም ወስዶ መግደል ነውርም፤ ግፍም ነው!


እንዲህ ያሉ ድርሳናት፣ "ለሃይማኖት መከራከሪያነት አልዋሉም" በሚል ቀላልና ተልካሻ ምክንያት የሚታለፉ አይደሉም። ይልቁን እንደሚደፋው አተላ ሊወ*ገዱ፤ በወንጌል እውነት ተጠ*ርገው ሊወ*ገዱ ይገባቸዋል። እንዲወገዱ የምንሻው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በእውነተኛ ተሐድሶ ወደ ሞተላት ቅዱስ መሲሕ ፊቷን ፍጹም ትመልስ ዘንድ ነው!

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek


የእግዚአብሔር መልክና አምሳል ያለበትን ማናቸውንም ሰው በማናቸውም ኹኔታ መግደል ነውርም፤ ርኩሰትም ነው። በእናት በአባት ፊት ልጅን መግደል ደግሞ መራር ሐዘንን በልብ መትከልና ከጭካኔ የከፋ ጭካኔ ነው።


የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት
 
መግቢያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ዋና ከሚባሉት ትምህርቶችና አማኞች ሊጠመቁት ከሚገባው ጥምቀት አንዱ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው። የብዙዎች ትኵረትና መሻት ያለው የውኃ ጥምቀትና በየዓመቱ ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ የሚከበረውን የከተራ በዓልን እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እምብዛም ግንዛቤው ያላቸው አይመስልም። ነገር ግን አስገዳጅ ከኾኑ መንፈሳዊ እውነቶች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ያልተጠመቀ እርሱ እውነተኛ አማኝ ወይም መንፈሳዊ አይደለም።



በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ ማን ነው?

ቅዱሳት ወንጌላት፣ “እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ[ክርስቶስ] ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።” (ማቴ. 3፥11፤ ማር. 1፥8፤ ሉቃ. 3፥16፤ ዮሐ. 1፥33) በማለት የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የሚያጠምቀው ክርስቶስ እንደ ኾነ ይመሰክራሉ።

ይህም ጥምቀት በበዓለ ኀምሳ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ላይ ተፈጸመ፤ (ሐ.ሥ. 1፥5፤ 2፥1-4)። አማኞችም መንፈስ ቅዱሳዊ ጥምቀትን በክርስቶስ ሥራ የክርስቶስ አካል ከኾነችው ከቤተ ክርስቲያን ጋር አንድ በመኾናቸው በቤተ ክርስቲያን የወረደውን መንፈስ ቅዱስን ይካፈላሉ፤ (1ቆሮ. 12፥13፤ ቲቶ 3፥3-5)።

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን እነማን ይጠመቃሉ?

የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የሚጠመቁት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑና በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ዳግመኛ የተወለዱት ናቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማያት ከማረጉ በፊትና ወደ ምድር ዳርቻ በመሄድ ወንጌልን ከመመስከራቸው በፊት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፣ “ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ።” (ሉቃ. 24፥49፤ ሐ.ሥ. 1፥5)። ስለዚህም በክርስቶስ በስሙ የሚያምኑ ኹሉ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ይጠመቃሉ።
እንዲሁም ኀጢአትን ፈጽመው የሚጠየፉ፣ መንፈስ ቅዱስን በብዙ የሚናፍቁና የሚራቡ መንፈስ ቅዱስን ይመላሉ፤ መንፈስ ቅዱስን መራባችንን የምንገልጠው፣ እጅግ በጸሎት በመትጋት፣ በማምለክ፣ ቃሉን በመመስከርና በማወጅ ከቶውን ያላቋረጥን እንደ ኾን ነው።

መቼ ይፈጸማል?

በደቀ መዛሙርቱ ሕይወት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚከናወነው፣ ጌታችን ወደ ሰማያት ካረገ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደ ኾነ ተናግሮአል (ሐ.ሥ. 1፥5)። አስቀድሞ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ነበር (ዮሐ. 20፥22)፤ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ እንደ ገና የመንፈስ ቅዱስን ኀይል ሊለብሱ እንደሚገባቸውም ነገራቸው። ቆርነሌዎስም፣ ካመነና ዳግም ከተወለደ በኋላ ልክ እንደ ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቀ (ሐ.ሥ. 11፥16-17)።

በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ

ለመኾኑ ግን “በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ማለት ምን ማለት ነው?” ብለን ብንጠይቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ማለት በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እንደ ኾነ ይነግረናል፤ ስለዚህም ደቀ መዛሙርትና ሌሎችም ከጌታችን ኢየሱስ ዕርገት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ ወይም በግልጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። እንኪያስ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ ወይም ሲሞሉ ምን ያደርጋሉ? ብለን በድጋሚ ብንጠይቅ፣መጽሐፍ ቅዱስ እኒህን እውነቶች ይነግረናል፣ 
1.   ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ሲሞሉ በኀይልና በድፍረት የመዳንና የትንሣኤውን ወንጌል ይመሰክራሉ፤ “በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።” (ሐ.ሥ. 4፥31) እንዲል፣ በተጨማሪም (ሐ.ሥ. 4፥8፤ 9፥17-20 ይመልከቱ)። መንፈስ ቅዱስ ቅዱስን ያልተሞላ ሰው የመዳንን ወንጌል በድፍረት ይናገር ዘንድ አይችልም።
2.   አማኞች መንፈስ ቅዱስን ሲሞሉ ልሳንን ይናገራሉ፤(ሐ.ሥ. 2፥4፤)። ልሳን በሌላ ቋንቋ መናገር ነው፤ ይህም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽና አማኙን ለማነጽ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ሊነጋገር ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲሰጥ ሁከትና ነውጥን መፍጠር አይገባም፤ እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነውና ኹሉ በሥርዓት ሊኾን ይገባል።
3.   መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ሰው ኀጢአትንና ኀጢአተኝነትን ፈጽሞ ይጠየፋል። በተለይም መንፈስ ቅዱስን ከሚያሳዝንና ከፈቃዱ ተቃራኒ ከኾነ ከማናቸውም ኀጢአታዊ ተግባር ይርቃል። እግዚአብሔር በመጨረሻ በክፋትና በርኩሰት ላይ የሚፈርደውን ፍርድ በትክክል ከማወቁም በዘለለ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አብዝቶ ይሻል፣
4.   ክርስቶስን እጅግ በሚያከብር ሕይወት ይመላለሳል፤ (ዮሐ. 16፥13፤ ሐ.ሥ. 4፥33)። ክርስቶስን በሚያከብር ሕይወት ለመመላለስ ግለ ብቃት አያስመካም፤ ሰው በግለ ብቃቱ እግዚአብሔርን ማርካትና ማስደሰት አይችልምና፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ሲመላ ክርስቶስን ፍጹም በሚያስከብር ሕይወት ይመላለሳል። እንዲሁም አንድ አማኝ መንፈስ ቅዱስ ሲመላ አያሌ ስጦታዎች በሕይወቱ ይፈስሳሉ።

ማጠቃለያ

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ መንፈስ ቅዱስ እኛን ክርስቶስ ራስ ወደ ኾነበት አካሉ የሚከትትበት እጅግ አስደናቂ ሥራ ነው። አንድ አማኝ ወደዚህ አካል ሲገባ፣ ኹለንተናው ፍጹም በኾነ መንገድ መሠራትና መዋብ፤ መቀደስ ይጀምራል። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በማያቋርጥ ግንኙነትና ዕለት ዕለት በሚታደስ ሕይወትም ይመላለሳል፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ያለውን ሕይወት ያብዛልን፤ አሜን።
 
የብሎግ አድራሻ - https://abenezerteklu.blogspot.com/2021/01/blog-post_18.html?m=1


የቁስ ብልጥግና ስናመልክ፣ እንኳን ከመንፈሳዊነት፤ ጤናማ ሰው ሊኖረው ከሚገባ ከሞራል፤ ከሥነ ምግባርም መሠላል ላይ የተፈጠፈጠ ትውልድ ይፈለፈላል። ከቁሳዊ ድህነት ይልቅ፣ የአእምሮ ድህነት እንዴት ይሰቀጥጣል?!

“በሰነፍ እጅ የጥበብ መግዣ ገንዘብ መኖሩ ስለ ምንድር ነው? ጥበብን ይገዛ ዘንድ አእምሮ የለውምና።”(ምሳ. 17፥16)

የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek


ምናልባት ኢትዮጵያና አሜሪካ እጃቸውን ወደ እግዚአብሔር ይዘረጉ ይኾን? ይመለሱ፤ ይጸጸቱ ይኾን?! አፈር በአፈር አይስቅም፤ አይኮራምም፤ እንመለስ!


"ንብረት የማስመለስ" ሕጓ፣ ቱጃር አጥማቂያንን፣ ንጥጥ ያሉ መነኮሳትን፣ ከቅምጥልነታቸው የተነሳ አፈር አይንካኝ የሚሉ "ነቢይና ሐዋርያትን" ቢነካካ ሸጋ ነበር!

Показано 20 последних публикаций.