የቆጣሪ ውል ለማደስ ምንም አይነት ክፍያ አያስከፍልም
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያሉትን ደንበኞች አውቆ ለሚጠይቋቸው የትኛውም አይነት የመብት ጥያቄዎች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት እንዲችል ውል ከፈፀሙ5 አመት እና ከዚያ በላይ የሞላቸው ደንበኞች የቆጣሪ ውል ዕድሳት እንዲፈፅሙ እያደረገ ይገኛል፡፡
ደንበኛች ውል ለማደስ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃ ፍቃድ፣ አንድ ወቅታዊ 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣ የኪራይ ቤት ከሆነ ቤቶቹን ለማስተዳደር ስልጣን ከተሰጠው አካል ወይም የባለቤትነት ኃላፊነት በመውሰድ የተፃፈ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
በተጨማሪም ያልተከፈለ እዳ ካለ ከአከራይ የተፈረመ የውል ግዴታ ሰነድ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ሰነድ በመያዝ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ማዕከል በመሄድ ውል መፈፀም ይኖርባችዋል፡፡
ይሁን እንጂ ደንበኛች የቆጣሪ ውል ለማደስ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሲሄዱ ገንዘብ ክፈሉና የሚሉ ደላሎች እንዳሉ መረዳት ችለናል፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን የቆጣሪ ውል ለማደስ ምንም አይነት ክፍያ የማይከፈል መሆኑን እናሳውቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት