በኤሌክትሪክ በአንድ ቀን ንቅናቄ የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት “በኤሌክትሪክ በአንድ ቀን ንቅናቄ” ኤሌክትሪክ አገኝተው የማያውቁ የገጠር ከተሞች ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድርግ ተችሏል፡፡
በሃዲያ ዞን አመካ ወረዳ የጌጃ ሳተላይት ጣቢያ በትልንትናው እለት ብቻ 130 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ቀድሞ የጌጃ አካባቢ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ቢኖርም ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ታውቋል፡፡ ነዋሪዎቹ አገልግሎቱን ለማግኘት በማህበር ተደራጅተው በመምጣት ኤሌክትሪክ ለማግኘት 7 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ በሆሳና ሪጅንን በዶዮገና አገልግሎት መስጫ ማዕከል የዋግብታ ሳተላይት ጣቢያ በበኩሉ ታሕሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ ለ66 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
በባሌ ሮቤ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በታሕሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም 75 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የማዕከሉ ሰራተኞች ደንበኛችን ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን መስጠት ለማስተናገድ እስከ ምሽት 4 ሰዓት ድረስ ሲያስተናግዱ አምሽተዋል፡፡
“ኤሌክትሪክ በአንድ ቀን” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ ንቅናቄ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ሪጅኖችም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት