በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ የስርቆት ወንጀል ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደረሰ
በቢሾፍቱ ከተማ ቦሮ ሆራ አርሰዴ ወረዳ በተለምዶ ሽንብራ ሜዳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ለውኃ አገልግሎት በሚሰጥ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት 672 ሺህ ብር የሚገመት ጉዳት ደርሷል፡፡
ወንጀለኞቹ የከፍተኛ ኃይል መስመር 5 ምሶሶዎችን በመጋዝ በመቁረጥ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን የወንጀሉ ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ ከህግ አካላት ጋር ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተቋርጦ የነበረውን የሃይል አቅርቦት ለመመለስ መስመሩን በአዲስ የመቀየር ስራ ተከናወኗል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው የሚፈፀመው የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆት ለኃይል መቆራረጥ ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ስርቆት የሚፈፅም ማንኛውም አካል በቴሌ ኮሚኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ተቋሙ ከሚወስደው ህጋዊ እርምጃ ባሻገር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሀብት የፈሰሰባቸውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ሁልግዜ በንቃት በመጠበቅ የዜግነት ኃላፊነታቸው ሊወጡ ይገባል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት