ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በመገናኛ ብዙኃን የምሥጋና መርሐ ግብር ተገኝተው የሥራ መመሪያና መልዕክት አስተላለፉ።
"ዛሬ በብዙ ሺሕ ከሚቆጠሩ ሰባክያን ከሚያስተላልፉት መልእክት ይልቅ ይህ ሚዲያ ርቀት ሳይወስነው፣ቦታ ሳይገድበው በየትኛውም ዓለም ላሉት ሁሉ እኩል መረጃ የምንሰማበት ልዩ ልሣን ነው" ብፁዕ አቡነ አብርሃም
" ይህ ሚዲያ የቤተክርስቲያን ብቸኛ ሚዲያ በመሆኑ፤ ስብከተ ወንጌልን ከማስፋፋትና ልማታዊ ተግባርን ለማሳየት አህጉረ ስብከት የአየር ሰዓት ወስደው እንዲሠሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።" ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ
ዘጋቢ መ/ር ጌታቸው በቀለ
(#EOTCTV ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም አዲስ አበባ)
++++++++++++++++++++++++++++++++
ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የፕሮዳክሽን መሣሪያዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የቀጥታ ሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ለመጀመር ለተሳተፉ ግለሰቦችና ተቋማት ባዘጋጀው የምስጋና መርሐ ግብር ላይ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዶክተር መዝገቡ ካሣ እንደተናገሩት “የቤተክርስቲያናችን መገናኛ ብዙኃን ከተቋቋመ በኋላ ሕዝበ ክርስቲያኑን እያስተማረ፣ መረጃ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑን” ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱም የቀጥታ ሥርጭት እንዲጀምር ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ በጎ አድራጊዎች 160 ሺሕ ዶላር በማውጣት ለቀጥታ ሥርጭት የሚያግዝ የተለያዩ መሣሪያዎችን አስተባብረው በመግዛት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረጋቸው አመስግነው፤ ድርጅቱም በቀጣይ ተቋሙን ለማስፋፋት፣ አገልግሎቱንም ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ “ለቴክኖሎጂ ዘመን ሚዲያ አማኞች ባሉበት ሁሉ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ረገድ ተደራሽነቱ ሰፊ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ሚዲያ የቤተክርስቲያን ብቸኛ ሚዲያ በመሆኑ፤ ስብከተ ወንጌልን ከማስፋፋት አንጻር አህጉረ ስብከቶችም የአየር ሰዓት ወስደው እንዲሠሩ፣ ሌሎችም ሚዲያውን በተቻላቸው መንገድ እንዲያግዙ ጥሪያቸውን አስተላልፈው፤ ለሚዲያው አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡”
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “ዛሬ በብዙ ሺሕ ከሚቆጠሩ ሰባክያን ከሚያስተላልፉት መልእክት ይልቅ ይህ ሚዲያ ርቀት ሳይወስነው፣ቦታ ሳይገድበው በየትኛውም ዓለም ላሉት ሁሉ እኩል መረጃ የምንሰማበት ልዩ ልሣን ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ተደራሽነቱም ሰፊ ነው፡፡ ለዚህ ሚዲያ አሁን ላለበት ደረጃ የደረሰው በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሳል አመራር በመሆኑ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ስም ምስጋዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አያይዘውም ለሚዲያው አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እና ለድርጅቱ ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ሚዲያው ወደፊት ዘመኑን ለመዋጀት ተግቶ መሥራት እንደሚገባው በመግለጽ ቅዱስ ሲኖዶስም በማናኛውም መልኩ ሚዲያውን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዕለቱም ከአሥራ ሰባት በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የየመምሪያ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ለሚዲያው የቀጥታ ሥርጭት እንዲጀምር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ኢኦቴቤ ቴቪ ( EOTC TV ) ማሳስቢያ
በቤተክርስቲያናን በመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት እና EOTC TV በሚሉ ስሞች በተከፈቱ ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች አሳሳች መረጃዎች እየተላለፉ ይገኛሉ። ትክክለኞቹ የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (# EOTCTV ) የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ከዚህ በታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች (ሊንኮች) ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽ የመዝሙር ዩቲዩብ ገጽ
@eotctvmezmur' rel='nofollow'>https://youtube.com/@eotctvmezmur
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=