Репост из: Hiwot Melese
የዘንድሮው የሜሪ ጆይ እግር ጉዞ አረጋዊያንን አከብራለሁ! በምርቃታቸውም እባረካለሁ! በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ህዳር 30 ዕለተ ዕሁድ የሚካሄድ ሲሆን፣
የጉዞው መነሻና መድረሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት ሱሙዳ አደባባይ ነው።
የጉዞው መስመር ከሱሙዳ አደባባይ ወደ ፍቅር ሀይቅ በሚወስደው መንገድ በሴንትራል ሆቴል ታጥፎ ተመልሶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ቤተ ክርስትያን ፊት ለፊት ያበቃና በአረጋዊያን ምርቃት የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ይሆናል።
👉የተጓዦች ከጉዞ ስፍራ መድረሻ ሰአት ማለዳ 12:30
👉በጉዞው መነሻ ስፍራ የሰውነት ማማሟቂያ እና በዕለቱ የክብር እንግዳ መክፈቻ ንግግርና ጉዞውን ማስጀመር ይካሄዳል።
👉 በጉዞው መሀል የሰርከስ ና የስካውት አባላት ትርኢት ይኖራል እንዲሁም የንጉስ ማልት ቅምሻም ተካቷል
🙏ማሳሰቢያ
👉 ማንኛውም ስለትእና የጦር መሳሪያ መያዝ አይቻልም
👉 ከበጎ አድራጎቱ አላማ እና ከማዝናናት ውጭ የሆኑ ንግግሮችና ሌላም ማንፀባረቅ አይፈቀድም
👉 አደንዛዥ ዕጾችንና አልኮል መጠቀምም ሆነ ተጠቅሞ መጓዝ አይፈቀድም
በመጨረሻም ሁላችንም አረጋውያኖቻችንን በማክበርና በመደገፍ ከምርቃታቸው በረከት ተንበሽብሸን እንድንመለስ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏