👉በአዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም!!
"በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደለም" - ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡
👉በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የነበረ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡
👉" ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ። መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም። ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።"ብለዋል።
ሰሞኑን በአፋር ክልል እየተከሰተ የነበረው የመሬት መንቀሳቀስ ዛሬም የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 4.9 የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለኢቢሲ ገልፀዋል።
👉ፕሮፌሰር አታላይ በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመከሰቱን ገልጸው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) መሆኑን አረጋግጠዋል።
ኢትዮ-መረጃ