Ethiopian grade 9-12 students ®


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Join our educational Telegram channel for daily insights, tips, and resources to enhance your learning journey. Stay updated on the latest trends, tools, and techniques in education to help you succeed academically and professionally.ሁሉንም በአንድ ከኛ ያገኛሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: BEST ቪዲዮ
🎧ሙዚቃ እና 🎬ፊልም በነፃ ከፈለጉ ከታች ያለውን ⚫ BUTTON 🔵 ይጫኑ ‼


Репост из: Private
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ✅

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!🏆

10+10×0+10=🗯




በ2017 ዓ.ም 12ኛ፣ 11ኛ ወይም 10ኛ ክፍል ተማሪ ለሆኑ ተማሪዎች wing one Academy YouTube channel ለማህበራዊ ሳይንስም ለተፈጥሮ ሳይንስም ተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በዩቲዩብ ቻናል ይዞላችሁ ቀርቦዋል፤ ትምህርቱን በነፃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ "Wing one academy " YouTube channel ለተማሪዎች @WingOneAcademy' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@WingOneAcademy




physics g11 unit 1.pdf
1.6Мб
📚Physics Best Short Note

💡Grade :- 11(Unit 1)

🔥For Entrance Preparation

 🔻 በቀሰም Tutorial የተዘጋጀ!!


አሁንስ እንዴት አገኛቹት




ቤተሰቦች እና ያለኝን ማቴሪያል ሼር አደርግላቸዋለሁ እናንተም ለሰዎች ይጠቅማሉ ብላቹ የምታስቡትን Text book , guide እና ጥያቄዎችን ካላቹ inbox አድርጉልኝ

👇
@estf3


biology g11 unit 1.pdf
1.5Мб
📚Biology Best Short Note

💡Grade :- 11(Unit 1)

🔥For Entrance Preparation

 🔻 በቀሰም Tutorial የተዘጋጀ!!

📱 ለመመዝገብ👇


📢 የ Remedial የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

በያዝነው አመት በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር የ12ኛ ክፍል ውጤት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የትምህርት ሚኒስትር ለተማሪኮም እንዳስታወቀው የ2016 የሪሚዲያል መግቢያ ነጥብ ለወንዶች 204 ለሴቶች ደግሞ 192 ሆኗል

ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,|


qesemacademy-105-english-questions-with-answer.pdf
11.2Мб
✔️For Entrance Preparation

🎚️ English 105 Question with Answer

✅ Year :- 2016 E.C

✈️


👉በአዲስ አበባ ዛሬ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም!!

"በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደለም" - ዶ/ር ኤሊያስ ሌ


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቲቪ እንደገለፁት፤ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ አልፎ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ተናግረዋል፡፡ 

👉በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የነበረ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡

👉" ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ። መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም። ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።"ብለዋል።

ሰሞኑን በአፋር ክልል እየተከሰተ የነበረው የመሬት መንቀሳቀስ ዛሬም የተከሰተ ሲሆን ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 4.9 የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለኢቢሲ ገልፀዋል።

👉ፕሮፌሰር አታላይ በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመከሰቱን ገልጸው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) መሆኑን አረጋግጠዋል።

    
             ኢትዮ-መ
ረጃ


የጥንቃቄ መልዕክት ‼️

የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ ርምጃዎች፦

📌  ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሰሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እንዲሁም ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

📌  በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

📌  በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ - ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

📌  መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ - የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሰሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽከርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።









Показано 19 последних публикаций.