700 ሚልየን ብር ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ታገደ!!
የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2 ሺሕ 483 የገንዘብ ዝውውሮችን በማጣራት ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በቁጥጥር ማሳገዱን አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ከፍተኛ የሆነ ግኝቶችን ለህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች በማቅረቡ በንቃት እየመረመረ እና ሪፖርት እያደረገ መሆኑም ለአሐዱ ገልጿል።
በዚህም መሠረት ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 2 ሺሕ 483 በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ ሪፖርቶችን የተቀበለ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 120 መዝገቦች ለተጨማሪ አሰርምጃ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላት ማቅረቡን አመላክቷል።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ ለአሃዱ እንደተናገሩት፤ እነዚህን ሪፖርቶች ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በሕ-ገወጥ መንገድ የተያዘ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
"ይህ ገንዘብ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሙስና እና ሌሎች ሕገ-ወጥ ተግባራትን ጨምሮ ከከባድ የወንጀል ድርጊቶች ጋር የተገናኘ ነው" ብለዋል።
"ከተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የሚቀርቡ ሪፖርቶችና የድጋፍ ጥያቄዎች እየተበራከቱ መጥተዋል" ያሉት አቶ እንዳለ፤ አገልግሎቱ እነዚህን የእርዳታዎች ጥሪዎች በተገቢው መልኩ እንደሚቀበልና በቀጣይም በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ከባንክና ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበርና አጠራጣሪ የፋይናንስ ግብይቶችን በማጣራት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ከፍተኛ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዳይዘዋወር ማድረጉንም አስረድተዋል።
"ባንኮች አጠራጣሪ ግብይቶችን ሲኖሩ ሪፖርቶችን በማቅረብ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ" ያሉት ሥራ አስፈፃሚው፤ "ከዚያም አልፎ በጥልቀት በመመርመር የሽርክና የገንዘብ ማጭበርበር ዘዴዎችን ለመለየት እና ለማስቆም ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል" ብለዋል።(አሐዱ)