ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰጠ ማሳሰቢያ
4ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ባለ ሁለት ከቅጣጫ የነበረው መንገድ ባለአንድ አቅጣጫ እንዲሆን መደረጉን ባለማወቅ አንዳንድ አሽከርካሪዎች አሁንም ለደምብ መተላለፍ ቅጣት እየተዳረጉ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ።
4ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች አንድ አቅጣጫ ብቻ ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጋቸው ቢታወቅም፤ ነገር ግን አንዳንድ አሽከርካሪዎች አሁንም የተተከሉ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እየጣሱና ለቅጣት እየተዳረጉ መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።
መረጃው ቀደም ሲል ለአሽከርካሪዎች በተለያዩ ሚዲያዎች የተገለፀ ቢሆንም አሁንም አንዳንዶች ክልከላውን እየተገበሩት ባለመሆኑ መረጃውን ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
በዚህም መሠረት፦
👉 ከጥይት ቤት መስቀለኛ እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት ድረስ፣
👉 ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ቅዱስ ገብርኤል (ሳይንስ ሙዚየም) ድረስ እንዲሁም
👉 ከቅዱስ ገብርኤል መስቀለኛ እስከ ጥይት ቤት ድረስ ቀድሞ የነበረው ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ (Two way) ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ (One way) የተቀየሩ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች አውቀው የትራፊክ ምልክትና ማመልከቻዎችን በጥንቃቄ እያከበሩ እንዲያሽከረክሩ፤ እንዲሁም በአካባቢው የተመደቡትን የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ ጠይቀው በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ